Theology of the Church, Amharic Mentor Guide

5 2 /

የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት

ጥምቀታዊ ዳግም ውልደት የጥምቀት ተግባር ስለተፈፀመ ብቻ ጥምቀት በራሱ ሰውን ያድናል የሚለው የተሳሳተ እምነት ነው። ቀደም ባሉት ጊዜያት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለዚህ በጣም ቅርብ የሆነ ነገር የምታስተምር ትመስል ነበር፣ ዛሬ ግን የካቶሊክም ሆነ የፕሮቴስታንት አስተምህሮ የጥምቀት ዋናው ነገር እምነት እንደሆነ ይስማማሉ። የኒሳ ቤተ ክርስቲያን አባት ጎርጎርዮስ አጽንዖት የሰጠው አንድ ሰው ከተጠመቀ ነገር ግን ከእውነተኛ ንስሐ ጋር ካላዋሃደው፣ “በእነዚህ ሁኔታዎች ውሃው ውሃ ብቻ ነው፣ ምክንያቱም የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ በጥምቀት ውስጥ በምንም መንገድ አይታይምና።” የሚለውን ሃሳብ ነው።

ለ. ጥምቀትን እንደ ሥርዓት የሚመለከቱት አንድ ሰው ራሱን ከክርስቶስ እና ከቤተክርስቲያን ጋር መወገኑን የሚገልጽበት ምልክት አድርገው ይመለከቱታል። ጥምቀት በቤተክርስቲያን ውስጥ ለመካተት አስፈላጊ ነገር ነው።

2

1. ለጥምቀት እንደ ሥርዓት ወይም እንደ ምልክት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ፡-

ሀ. የሐዋርያት ሥራ 10፡47

ለ. 1 ቆሮ. 1.14-17

2. ለጥምቀት ዋናው ማበረታቻ መታዘዝ ነው

የባፕቲስትን ወግ የሚወክለው ሆልማን ባይብል ዲክሽነሪ እንዲህ ይላል:- “ጥምቀት የመዳን መስፈርት አይደለም፣ ነገር ግን የመታዘዝ ቅድመ ሁኔታ ነው። ጥምቀት የደቀመዝሙርነት የመጀመሪያ እርምጃ ነው። ምንም እንኳን ሁሉም የጥምቀት ትርጉሞች አስፈላጊ ቢሆኑም ክርስቶስን እንደ ጌታ እና አዳኝ የማወቃችን ምስል ሆኖ አብዛኛውን ጊዜ ወደ አእምሯችን የሚመጣው የውሃ ጥምቀት ነው። ጥምቀት የክስተቱ ምስል እንጂ ክስተቱ ራሱ አይደለም። ስለዚህ የመታዘዝ መንገድ በእምነት ወደ ክርስቶስ መምጣት እና ያንን ደግሞ በጥምቀት ምልክት ማሳየት ነው። ~ Trent C. Butler, Gen. ed. Holman Bible Dictionary (electronic ed.). Nashville: Holman Bible Publishers, 1991.

Made with FlippingBook Ebook Creator