Theology of the Church, Amharic Mentor Guide

/ 6 1

የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት

• እኛ እግዚአብሔርን የምናመልከው በምስጋና እና በውዳሴ እና ቃሉንና ምስጢራትን በሚያጎላ በስርዓተ ቅዳሴ፣ እንዲሁም እንደ ቃል ኪዳን ማህበረሰብ በመታዘዝ እና በአኗኗር ዘይቤአችን መሆኑን ነው።

I. ቤተ ክርስቲያን የምታመልክበት ማዕከላዊ ምክንያት አንድ፣ እውነተኛ እና ሁሉን ቻይ የሆነውን ያህዌን የማክበር ዓላማ ነው። እንደ ጥንቷ እስራኤል፣ ቤተክርስቲያን ለእግዚአብሔር የመጨረሻ ክብር እና ደስታ ትኖራለች፣ የምትሆነውና የምታደርገው ነገር ሁሉ በሁሉም መልኩ እርሱን ለማክበር መደረግ አለበት። ጳውሎስ ይህንን ነጥብ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ብዙ ጊዜ ተናግሮታል፣ ለምሳሌ፡- “እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት። ( ቆላ. 3.17 ) “በስሜ የተጠራውን ሁሉ፣ ለክብሬ የፈጠርሁትን፣ ያበጀሁትንና የሠራሁትን አምጡ።” እና እንደገና ቁጥር 21 ላይ “21ለራሴ ያበጀሁት ሕዝብ ምስጋናዬን ያውጅ ዘንድ ይህን አደርጋለሁ።” ይላል። (ኢሳ. 43፡7) “እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤ እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።” (1 ጴጥ. 2፡ 9-10) በተለይ ታላቁን እና የከበረውን አምላካችንን ለምን ማምለክ ይገባናል? መልሱ የተመሰረተው በብቸኛ ቅድስናው፣ ወሰን በሌለው ውበቱ፣ ወደር በሌለው ክብሩ እና አቻ በሌለው ስራው ላይ ነው።

የቪዲዮ ሴግመንት 2 ዝርዝር

ገጽ 216  20

2

ሀ. እግዚአብሔርን የምናመልከው ስለ ብቸኛ ቅድስናው ነው።

1. ኢሳ. 6.3

2. ራእ. 4.8-9

3. ራእ.15.3-4

Made with FlippingBook Ebook Creator