Theology of the Church, Amharic Mentor Guide

/ 6 9

የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት

7. በቤተክርስቲያንውስጥያለውየፍቅርና የመተሳሰብመገለጫቤተክርስቲያን ለእግዚአብሔር የምታቀርበው አምልኮ ላይ ተጽዕኖ የሚኖረው እንዴት ነው? ቤተ ክርስቲያን በአባሎቿ መካከል ያለው ግንኙነት ቢበላሸ እግዚአብሔርን ማምለክ ትችላለች? መልስህን አብራራ።

ግንኙነት

የቁልፍ ጽንሰ ሐሳቦች ማጠቃለያ

ይህ ትምህርት የሚያተኩረው እኛ እንደ ቤተክርስትያን አባላት ከእግዚአብሔር ጋር ባለን መሰረታዊ አቀራረብ ማለትም በክርስቶስ በማመን በሆነ ጸጋ ብቻ እና የዚህ ጸጋ ልምምድ እራሱን በእውነተኛ ውዳሴ፣ አምልኮ፣ ምስጋና እና አድናቆት በሚገልጥበት ሁኔታ ላይ ያተኩራል። በአንድ በኩል እነዚህን መሠረታዊ ፅንሰ-ሀሳቦች መረዳታችን ቤተክርስቲያንን እንደ መሪ ማገልገል ምን ማለት እንደሆነ ለመገንዘብ ዋና ነገሮች ናቸው፣ አንድ ጉባኤ ጤናማ መሆን አለመሆኑን እንድንገነዘብ ይረዳናል፤ ይህም የእግዚአብሔርን የማይገባንን ሞገስ እና ፀጋ ባገኘንበት ልምምድ ላይ በመመስረት ነው። ከዚህ በታች የቤተክርስቲያን እውነተኛ ጥሪ ከሆነው ከአምልኮ ጋር የተያያዙ አንዳንድ መሰረታዊ ፅንሰ-ሀሳቦች ቀርበዋል፦ ³ መዳን በእምነት የምንቀበለው የእግዚአብሔር ነፃ ስጦታ እንጂ በስራ ሊገኝ ወይም የሚገባን አይደለም። ³ የሰው ልጆች በኃጢአት ባርነት ውስጥ ስለሆኑ የእግዚአብሔር ጸጋ አስቀድሞ በውስጣቸው ካልሠራ በስተቀር ትክክለኛውን ነገር መመኘት አይችልም። ³ አንድን ሰው ወደ መዳን ለማምጣት ምንጊዜም የመጀመሪያውን እርምጃ የሚወስደው እግዚአብሔር ራሱ ነው። “እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ ደግሞ እንወደዋለን።” ³ ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔርን ጸጋ የተለማመዱ ሰዎች ህብረት በመሆኗ አምልኮ የቤተ ክርስቲያን ግዴታዋም ደስታዋም ነው። ³ “ምግቡና ውሃው” (የጌታ እራት እና ጥምቀት) የእግዚአብሔርን ጸጋ የምንለማመድበት እና የምናስታውስበት መንገድ አካል ናቸው። የክርስቲያናዊ አምልኮ ቁልፍ ነገሮች ናቸው። ³ ቅዱስ ቁርባን የእግዚአብሔር ጸጋ ለእኛ የተሰጠበት መንገድ ሲሆን ሥርዓት አምልኮ ደግሞ ይህን ጸጋ በመታዘዝ እና በማስታወስ እውቅና የሚሰጥ ተግባር ነው። ሁለቱም የነገረ መለኮት ዓይነቶች በጌታ እራት እና በጥምቀት መሳተፍ ጠቃሚ የሚሆነው ከንስሐ እና ከእምነት ጋር ከተጣመረ ብቻ እንደሆነ ያሳያሉ። ³ የክርስቲያን መሪዎች ቅዱሳት መጻሕፍትን በማጥናት የጌታን እራት እና ጥምቀትን እንደ ቅዱስ ቁርባን ወይም እንደ ሥርዓተ አምልኮ መረዳቱ የትኛው የተሻለ እንደሆነ መወሰን አለባቸው። ³ የቤተ ክርስቲያን ማዕከላዊ ጥሪ እግዚአብሔርን ማምለክ ነው፤ ቤተክርስቲያን የምታመልክበት ቁልፍ ምክንያት ደግሞ አንድ፣ እውነተኛ እና ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ያህዌን ለማክበር ነው።

ገጽ 219  24

2

Made with FlippingBook Ebook Creator