Theology of the Church, Amharic Mentor Guide

/ 7 1

የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት

* በቤተክርስቲያናችሁ ያለው የአምልኮ ቡድን ምን ያህል ከአምልኮ ጋር የተያያዙትን እውነታዎች እና አንድምታዎች እንደ ቤተክርስቲያን ጥሪነት ተረድቷል? * በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተመከሩት አካላዊና ሥነ ልቦናዊ አገላለጾች አንጻር የቤተ ክርስቲያናችሁ የአምልኮ ነጻነት ምን ድረስ ነው? “ባህላዊ መግለጫዎች” የሆኑት ጩኸት፣ ጭብጨባ እና ሽብሸባ ምን ያህል ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው የአምልኮ ትዕዛዛት ጋር አብረው ይሄዳሉ? መልስህን በዝርዝር አስረዳ። * የቤተ ክርስቲያናችሁ “ሥርዓተ ቅዳሴ” ምን ዓይነት ባሕርይ አለው? በሌላ አነጋገር ቤተ ክርስቲያናችሁ በአምልኮ ሥርዓቷ ውስጥ “ታሪኩን ለመንገር” አገልግሎቶቿን እና በአላቶቿን እንዴት ነው የምታዘጋጀው? ይህ በቤተክርስቲያንህ ውስጥ የበለጠ ውጤታማ እንዳይሆን የሚከለክለው ምንድን ነው? * አንድ ሰው የጉባኤውን የአምልኮ ባሕል ከደረቀና ከተለመደው የአምልኮ አይነት ወደ አዲስና ሕይወት ሰጪ አምልኮ የሚለውጠው እንዴት ነው? እንዲህ ላለው ሁኔታ ምን አይነት እርምጃዎችስ አሉ? አላስፈላጊ ልታይ ባይነት በአንድ ባለ ተሰጥኦ ሙዚቀኞችና ዘማሪዎች ባሉባት አጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ በአዳዲስና በሚያስደንቅ የአምልኮ አገልግሎት ማደግ ጀምራለች። ነገር ግን አንዳንዶች የሙዚቃ አገልግሎት መሪው “ተራ” ለሚባሉት አይነት አምላኪዎች በአምልኮ ቡድኑ ውስጥ የመሳተፍ እድላቸውን የበለጠ አስቸጋሪ እንዳደረገባቸው ቅሬታ ማሰማት ጀምረዋል። ሁሉም ዘማሪዎች የድምጽ ብቃታቸውንና ኖታ የማንበብ ችሎታቸውን መፈተን ይጠበቅባቸዋል፤ ሙዚቀኞችም ቢሆኑ የሙዚቃ ኖታ ማንበብ የማይችሉና ለመዝሙሮቹ የተመረጡትን ውብ (ነገር ግን አስቸጋሪ) ቅንብሮችን መጫወት የማይችሉ ከሆነ እንዲሳተፉ አይፈቀድላቸውም። የሙዚቃ አገልግሎት መሪው በያዘው አቋም ጠንካራ ነው፣ እግዚአብሔር የላቀ ስለሆነ አምልኮአችንም በተቻለ መጠን የላቀ መሆን አለበት የሚል ነው። የሙዚቃ አገልግሎት መሪው በዚህ ጉባኤ ውስጥ አምልኮው እየተጓዘ ባለበት አቅጣጫ ላይ ሐሳብ እንድትሰጠው ቢጠይቅህ ምን ምክር ትሰጠዋለህ? እኔን እንዳመልክ ልታደርገኝ አትችልም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለው አዲሱ የአምልኮ መሪ በአምልኮ ወቅት ስለሚታዩ አካላዊ መገለጫዎች አስፈላጊነት አጽንዖት ይሰጣል። ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር ከመግለጽ አንጻር ማጨብጨብ፣ እጅ ማንሳትና ማወዛወዝ፣ መጮህ፣ ማሸብሸብ፣ መንበርከክ፣ ዝምታ፣ በመዘርጋት፣ በደስታ ጩኸት ቅዱሳት መጻሕፍት የሚናገሯቸውን የተለያዩ መንገዶች ሁሉ ልንጠቀምበት እንደሚገባ የያዘው አቋም በጣም ጠንካራ ነው። ፍቅራችንን በሥጋችን ለእግዚአብሔር ልናሳይ ይገባናል። በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ቁጥራቸው ትንሽ ነገር ግን ቁርጠኛ የሆነ ቡድን ከዚህ ሁሉ እንቅስቃሴና ግርግር የተነሳ ቁርጥ

2

ጥናቶች

1

ገጽ 220  26

2

Made with FlippingBook Ebook Creator