Theology of the Church, Amharic Mentor Guide
/ 7 3
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
በዚህ በአምልኮ ላይ ያለች ቤተክርስቲያን የተሰኘው ትምህርት ላይ ተጨማሪ ሀሳቦችን ለመከታተል ፍላጎት ካለህ እነዚህን መጻሕፍት መመልከት ይረዳህ ይሆናል፡- Boschman, Lamar. The Rebirth of Music . Shippensburg: Destiny Image, 2000. Bridges, Jerry. Transforming Grace: Living Confidently in God’s Unfailing Love . Colorado Springs, CO: NavPress, 1993. Engle, Paul E. Baker’s Worship Handbook . Grand Rapids: Baker Book House, 1998. Hill, Andrew E. Enter His Courts With Praise! Grand Rapids: Baker Book House, 1993. Oden, Thomas C. The Transforming Power of Grace . Nashville: Abingdon Press, 1993. Webber, Robert. Planning Blended Worship . Nashville: Abingdon, 1998. የዚህ ትምህርት የትኞቹ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሥነ-መለኮት ገጽታዎች በግል ሕይወትህ ላይ እንደሚተገበሩ ለማወቅ ጊዜው አሁን ነው። እነዚህን የእግዚአብሔርን ፀጋ ትምህርቶች እና የጸጋውን ሙሉ ግንዛቤ በግል እና በቤተክርስትያን ህይወታችን ውስጥ የሚመራውን አምልኮ አሁን ባለህ የአገልግሎት ሁኔታ ውስጥ ተግባራዊ ታደርገው ዘንድ መንፈስ ቅዱስ የሚጠራህ የት ነው? ግልጽ እና ተለዋዋጭ የአገልግሎት ግንኙነቶችን ማድረግ የማንኛውም ብቁ መሪ ዋና ክህሎት ነው፣ አሁን ደግሞ ይህን ችሎታ በተለይም ከራስህ ህይወት ጋር በተገናኘ መልኩ ለመለማመድ እድሉ አለህ። በእነዚህ እውነቶች ላይ አሰላስለህ በዚህ በሚቀጥለው ሳምንት ስለ የትኛው(ዎች) ማሰብ እና መጸለይ እንዳለብህ ተመልከት። በዚህ ሳምንት በአንተ አደራ ስር ያሉትን ስታገለግል መንፈስ ቅዱስ ለእነዚህ እውነቶች እንዴት አፅንዖት እንድትሰጥ እንደሚፈልግና እነዚህን እውነቶች በተለየ ሁኔታህ ላይ ስትጠቀም ጥበብ እንዲሰጥህ ጠይቀው። በአንተና በምታስተምራቸው ሰዎች ህይወት ውስጥ ይህን የሚለውጠውን የእግዚአብሔርን ጸጋ ትረዱና ታደንቁ ዘንድ ለራስህ እና ለምታገለግላቸው ወደ እግዚአብሔር ጸልይ። የክርስቶስን ፍቅር በግል ህይወታችሁ የበለጠ እውን እንዲያደርገው መንፈስ ቅዱስን ለምኑት፤ ስለማንነቱና በህይወታችሁ ስላደረገው ነገር ሁሉ ለእግዚአብሔር ያለህን ውዳሴና ምስጋና በነጻነት መግለጽ እንድትችሉ ኃይሉን ፈልጉ። በተለይም ለእግዚአብሔር ከፍተኛ ደስታን እና ክብርን ከማቅረብ ከጥሪያችን ጋር የሚጣጣሙ ለእግዚአብሔር የላቀ እና የተሻለ ምስጋናን ለመስጠት እንቅፋት ሊሆኑ ስለሚችሉ በህይወታችሁ ውስጥ ስላሉት ነገሮች፣ ሁኔታዎች፣ ልምዶች ወይም ልምምዶች እይታን እንዲሰጣችሁ ጌታን ጠይቁ።
ማጣቀሻዎች
2
የአገልግሎት ግንኙነቶች
ምክር እና ጸሎት
ገጽ 220 27
Made with FlippingBook Ebook Creator