Theology of the Church, Amharic Mentor Guide
9 2 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
የዚህ የቤተክርስቲያን ሁለተኛ ክፍል እንደ ምስክር አላማችን የሚከተሉትን እንድታዩ ለማስቻል ነው፡- • ቤተክርስቲያኑ የእርሱ ምስክር እንድትሆን ከኢየሱስ የተሰጠው ትእዛዝ በታላቁ ተልእኮ ውስጥ ተጠቃሏል። • ይህ ተልእኮ በሦስት ወሳኝ ነገሮችመሰረት በቀላሉ ሊገለጽ ይችላል፣ እነዚህም የቤተክርስቲያን ተልእኮ ዛሬ በዓለም ላይ ነው። • የመጀመርያው አካል ቤተክርስቲያን ስትሄድ ትመሰክራለች፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የጠፉትን ወንጌል እንድትሰብክ ተጠርታለች። • ሁለተኛው አካል ቤተክርስቲያን በጥምቀት ትመሰክራለች፡ ቤተክርስቲያን የተጠራችው አዲስ አማኞችን በክርስቶስ ለማጥመቅ ማለትም እነርሱን በቤተክርስቲያን አባልነት ለማካተት ነው። • ሦስተኛው አካል ቤተክርስቲያን በትምህርቷ ትመሰክራለች፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባሎቿ ክርስቶስ ያዘዘውን ሁሉ እንዲጠብቁ እና በእርሱ ወደ ብስለት እንዲያድጉ ታስተምራለች።
3
የቪዲዮ ሴግመንት 2 ዝርዝር
I. የታላቁ ተልእኮ የመጀመሪያ አካል የኢየሱስ የመሄድ ትእዛዝ ነው። እኛ እንደ ቤተ ክርስቲያን ወደ ዓለም በመግባት ኢየሱስን እንመሰክራለን። ለወንጌል መስበክ ጥሪ ምላሽ ስንሰጥ እንመሰክራለን።
ገጽ 227 11
ሀ. የምሥክርነት ጥሪ ምሥራቹን እንድንሰብክ ጥሪ፣ የወንጌል ጥሪ፣ ወደ ዓለም ሁሉ ገብተን ወንጌልን እንድንሰብክ የቀረበ ጥሪ ነው።
1. በኢየሱስ ተልእኮ ውስጥ ያለው የግሪክ ግስ ጊዜ ‘ያለማቋረጥ መሄድ’ የሚለውን ፍቺ ይሰጣል። ኢየሱስ እንዳለው፣ ቤተክርስቲያን ‘ወደ ዓለም ልትሄድ’ ነው፣ ወንጌላዊነት የቤተክርስቲያን ጉዳይ ነው።
2. ወደ ዓለም ሁሉ ሄደን ወንጌልን ለሰው ሁሉ እንሰብካለን፣ ማር 16፡15-16
3. የዚህ የምሥክርነት ጥሪ ዓለም አቀፋዊ ተፈጥሮ በክርስቶስ ራሱ በሐዋርያት ሥራ 1.8 (ማለትም፣ ኢየሩሳሌም፣ ይሁዳ፣ ሰማርያ እና እስከ ምድር ዳር ድረስ) እንደገና በግልጽ ታይቷል።
Made with FlippingBook Ebook Creator