Theology of the Church, Amharic Student Workbook
Animated publication
ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ
T H E U R B A N M I N I S T RY I N S T I T U T E ሚኒ ስቴር WO R L D I M PA C T, I N C .
የቤተ ክርስቲያን ሥነ-መለኮት
ሪ
ማ
ው
ተ
የ
መ
ፍ
ል
ሐ
መ
ጽ
ጃ
መ
ሞጁል 3 ስነመለኮት እና ስነምግባር
AMHARIC
የ ተ ማ ሪ ው መ ል መ ጃ መ ጽ ሐ ፍ
የቤተ ክርስቲያን ሥነ-መለኮት
ሞጁል 3
ክርስቲያናዊ አገልግሎት
በእግዚአብሔር እቅድ ጥላ ውስጥ ያለች ቤተክርስቲያን
በአምልኮ ላይ ያለች ቤተክርስቲያን
ቤተክርስቲያን እንደ ምስክር
በሥራ ላይ ያለች ቤተክርስቲያን
ይህ ሥርዓተ-ትምህርት የThe Urban Ministry Institute (TUMI) የሺዎች ሰዓታት የሥራ ውጤት በመሆኑ ያለ ፈቃድ ማባዛት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ TUMI እነዚህን መማሪያዎች ለእግዚአብሔር መንግሥት እድገት ለመጠቀም ለሚፈልጉ ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል፤ በተጨማሪም ለማባዛት በተመጣጣኝ ዋጋ ፈቃድ ይሰጣል ፡፡ እባክህ ይህ መጽሐፍ በትክክል ፈቃድ ያገኘ መሆኑን ከመምህርህ ጋር በመሆን አረጋግጥ፡ ፡ በ TUMI እና በፈቃድ አሰጣጥ ፕሮግራማችን ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት Www.site.org እና Www.tumi.org/license ን ጎብኝ፡፡
ካፕስቶን ሞጁል 3፡ የቤተክርስቲያን ስነ መለኮት የተማሪው መልመጃ መጽሐፍ ISBN: 978-1-62932-397-8
© 2005, 2011, 2013, 2015. The Urban Ministry Institute. መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው. የመጀመሪያ እትም 2005 ፣ ሁለተኛ እትም 2011 ፣ ሦስተኛው እትም 2013 ፣ አራተኛ እትም 2015 ፡፡
በ 1976 የቅጂ መብት ሕግ ወይም ከአሳታሚው በፅሁፍ ከሚፈቀደው በስተቀር የእነዚህን መማሪያ ቁሳቁሶች መቅዳት፣ እንደገና ማሰራጨት እና / ወይም መሸጥ ወይም በማንኛውንም ያልተፈቀደ መንገድ ማስተላለፍ የተከለከለ ነው ፡፡ የፍቃድ ጥያቄዎች በሚከተለው አድራሻ መቅረብ አለባቸው፥ The Urban Ministry Institute ፣ 3701 E. 13th Street, Wichita, KS 67208.
The Urban Ministry Institute የWorld Impact አገልግሎት ነው የሚተረጉምበት ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱስ እዚህ ላይ ተለይቶ ይታወቃል።
ይዘት
የኮርሱ አጠቃላይ እይታ
3 5 7
ስለ ጸሐፊው
የሞጁሉ (የትምህርቱ) መግቢያ
የኮርሱ መስፈርቶች
13 ትምህርት 1
1
በእግዚአብሔር እቅድ ጥላ ስር ያለች ቤተክርስቲያን
43 ትምህርት 2
2
በአምልኮ ላይ ያለች ቤተክርስቲያን
77 ትምህርት 3
3
ቤተክርስቲያን እንደ ምስክር
109 ትምህርት 4
4
በሥራ ላይ ያለች ቤተክርስቲያን
141
አባሪዎች
/ 3
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ስለ ጸሐፊው
ቄስ ዶ/ር ዶን ኤል ዴቪስ የዘ አርባን ሚኒስትሪ ኢንስቲትዩት ሥራ አስፈፃሚ እና የዎርልድ ኢምፓክት ከፍተኛ ምክትል ፕሬዚዳንት ናቸው ፡፡ ትምህርታቸውን በዊተን ኮሌጅ እና በዊተን ድህረ ምረቃ ትምህርት ቤት የተከታተሉ ሲሆን በቢብሊካል ስተዲስ የቢ.ኤ. (1988) እና በሲስተማቲክ ቲዎሎጂ የኤም.ኤ (1989) ዲግሪዎችን በቅደም ተከተል ማግኘት ችለዋል ፡፡ በተጨማሪም ከአዮዋ ስኩል ኦፍ ሪሊጅን በሃይማኖት ጥናት (ሥነ-መለኮት እና ሥነ-ምግባር) ፒኤችዲ አግኝተዋል ፡፡ የተቋሙ ሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር እና የዎርልድ ኢምፓክት ዋና ሥራ አስፈፃሚ እንደመሆናቸው መጠን የከተማ ሚስዮናውያንን ፣ የቤተ ክርስቲያን ተካዮችን እና የከተማ መጋቢያን ሥልጠናን በበላይነት የሚቆጣጠሩና የሚመሩ ሲሆን ለከተሞች ክርስቲያን ሠራተኞች በስብከተ ወንጌል ፣ በቤተ ክርስቲያን እድገት እና በተቀዳሚ ተልእኮዎች የሥልጠና ዕድሎችን ያስተባብራሉ ፡፡ በተጨማሪም የተቋሙን ሰፊ የርቀት ትምህርት መርሃግብሮች ይመራሉ እንዲሁም እንደ ፕሪዝን ፌሎውሺፕ ፣ ኢቫንጀሊካል ፍሪ ቸርች ኦፍ አሜሪካ ላሉት ድርጅቶች እና ቤተ እምነቶች የአመራር ልማት ኢድሎችን ያመቻቻሉ ፡፡ የበርካታ የማስተማር እና የአካዳሚክ ሽልማቶች ባለቤቱ ዶ/ር ዴቪስ በበርካታ ዕውቅ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሮፌሰር እና የፋኩልቲ አባል ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በሃይማኖት ትምህርቶች፣ ሥነ መለኮት ፣ ፍልስፍና እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥናቶች (ቢብሊካል ስተዲስ ) እንደ ዊተን ኮሌጅ ፣ ሴንት አምብሮስ ዩኒቨርሲቲ ፣ ሂዩስተን ድህረ ምረቃ የሥነ-መለኮት ትምህርት ቤት ፣ በአዮዋ ዩኒቨርሲቲ ስኩል ኦፍ ሪሊጅን ፣ በሮበርት ኢ ዌበር ኢንስቲትዩት ኦፍ ዎርሺፕ ስተዲስ ባሉ የትምህርት ተቋማት ሲያስተምሩ ቆይተዋል፡፡ የከተማ መሪዎችን ለማስታጠቅ በርካታ መጻሕፍትን ፣ ሥርዓተ-ትምህርቶችን እና የጥናት ጽሑፎችን አዘጋጅተዋል ፣ ከነዚህም ውስጥ የ ‹ካፕስቶን› ሥርዓተ ትምህርት ፣ የ TUMI ፕሪሚየር ሲክስቲን ሞጁል ዲስታንስ ኤጁኬሽን ሴሚናሪ ኢንስትራክሽን፥ የከተሞች አብያተ ክርስቲያናት ታሪካዊቷን የኦርቶዶክስ እምነት እንደገና በማደስ ራሳቸው እንዴት ሊታደሱ እንደሚችሉ የሚያትተው ሴክርድ ሩትስ፡ ኤ ፕሪሚየር ኦን ሪትራይቪንግ ዘ ግሬት ትራዲሽን እና ብላክ ኤንድ ሂዩማን፡ ሪዲስከቨሪንግ ኪንግ አስ ኤ ሪሶርስ ፎር ብላክ ትዎሎጂ ኤንድ ኤቲክስ ተጠቃሾች ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ዶ/ር ዴቪስ እንደ ስታሊ ሌክቸር ሲሪስ ባሉ ትምህርታዊ ጉባኤዎች፣ እንደ ፕሮሚስ ኪፐርስ ራሊስ ባሉ የተሃድሶ ኮንፈረንሶች እና እንደ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቨርጂኒያ ሊቭድ ቲዎሎጂ ፕሮጄክት ሲሪስ ባሉ ሥነ-መለኮታዊ ጥምረቶች ተሳትፈዋል ፡፡ ዶ/ር ዴቪስ በ 2009 ከአዮዋ ዩኒቨርስቲ የሊበራል አርትስ እና ሳይንስ ኮሌጅ የአልሙናይ የክብር ሽልማት ያገኙ ሲሆን በተጨማሪም የዘ ሶሳይቲ ኦፍ ቢብሊካል ሊትሬቸር እና ዘ አሜሪካን አካዳሚ ኦፍ ሪሊጅን አባል ናቸው ፡፡
4 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ቴሪ ኮርኔት (B.S., M. A., M.A.R.) በዊቺታ፣ ካንሳስ የሚገኘው The Urban Ministry Institute አካዳሚክ ዲን ኤምሪተስ ነው። በኦስቲን ካለው የቴክሳስ ዩኒቨርሲቲ፣ ከዊተን ኮሌጅ ምረቃ ትምህርት ቤት፣ እና በአዙሳ ፓሲፊክ ዩኒቨርሲቲ የሲ.ፒ. ሃጋርድ የስነመለኮት ትምህርት ቤት ዲግሪዎችን አግኝተዋል። ቴሪ እ.ኤ.አ. በ2005 ጡረታ ከመውጣታቸው በፊት World Impact ለ23 ዓመታት የከተማ ሚስዮናዊ በመሆን አገልግለዋል። በዚያን ጊዜ በኦማሃ፣ ሎስ አንጀለስ እና ዊቺታ በቤተክርስቲያን ተከላ፣ ትምህርት እና የአመራር ማሰልጠኛ ሚኒስትሪዎች ውስጥ አገልግለዋል።
/ 5
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
የሞጁሉ (የትምህርቱ) መግቢያ
ኃያል በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን፥
በኢየሱስ ክርስቶስ ያለችው የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ከቅዱሳት መጻህፍት በጣም አስፈላጊ መሪ ሃሳቦች አንዷ ነች። የናዝሬቱ ኢየሱስ በሞቱ፣ በመቀበሩ እና በትንሳኤው በምድር ላይ እሱን እንዲወክሉ እና የመጣውን/ደግሞም የሚመጣውን መንግስቱን እንዲመሰክሩ በተጠሩት በአዲሶቹ ህዝቡ ላይ ራስ ሆኖ ከፍ ከፍ ብሏል። ቤተክርስቲያኑ በእግዚአብሔር መንግሥት ፕሮግራም ውስጥ ያላትን ሚና ለመረዳት ለእያንዳንዱ የግል እና የጋራ ደቀመዝሙርነት ገጽታ ወሳኝ ነው። በቤተክርስቲያን ውስጥ ከእግዚአብሔር የማዳን ተግባር ውጭ ደቀመዝሙርነት ወይም ድነት የለም። እግዚአብሔር በህዝቡ አማካኝነት እና በህዝቡ በኩል የሚያደርገውን መረዳቱ አንድን መሪ እግዚአብሔርን በጥበብ እና በክብር እንዲወክል ኃይል ይሰጠዋል። ዛሬ በአለም ያለውን የአገልግሎት ባህሪ ሙሉ በሙሉ እንድታደንቁ ቤተክርስቲያንን በሚገባ እንድታጠኑ እንጋብዛችኋለን። በእግዚአብሔር እቅድ ጥላ ውስጥ ያለች ቤተክርስቲያን የተሰኘው የመጀመሪያው ትምህርት ቤተክርስቲያን ከአብርሃም ጋር በገባው ቃል ኪዳን አዲስ ሰውን በማዳን ለራሱ ክብርን ለማምጣት በእግዚአብሔር የላቀ አላማ እንዴት እንደምትገለፅ ላይ ያተኩራል። አህዛብን በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ስራው ውስጥ ለማካተት እና የእግዚአብሔርን ላኦስ ለራሱ ልዩ የሆነን ህዝብ ለመፍጠር ባለው ሀሳብ ቤተክርስቲያን ለጸጋው የድነት እቅዱ መገለጥ እንዴት ጥላ እንደምትሆን ትመለከታለህ። በተጨማሪም የድነትን ብልጽግና እና ትርጉም፣ በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር ከመለየትና መጥፋት ያለ መታደግ ምን ማለት እንደሆነ ትገነዘባለህ። ከክርስቶስ ጋር ባለን አንድነት ተስፋ የገባልንን መንግሥት ከሚወርሱት “የእግዚአብሔር ሕዝቦች” ጋር እንተባበራለን። ከክርስቶስ ጋር መተባበር በእግዚአብሔር ላይ ተስፋ ካላቸው ሰዎች ጋር አንድ መሆን ሲሆን ይህም በእግዚአብሔር አገዛዝ ሥር አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር በመፍጠር ኃጢአትና ሞት በዓለም ላይ ያስከተሉትን ውጤት ሙሉ በሙሉ የሚሽር ይሆናል። በአምልኮ ላይ ያለች ቤተክርስቲያን በተሰኘው በሁለተኛው ትምህርታችን ድነትን እንደ ቤተክርስትያን የአምልኮ መሰረት እንቆጥረዋለን። መዳን በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ እንደሚመጣ እና የሰው ልጅ በምንም መንገድ ሊያገኘው ወይም ሊገባው እንደማይችል እናያለን። ስለዚህ አምልኮ ለእግዚአብሔር ጸጋ ትክክለኛ ምላሽ ነው። እንዲሁም ስለ ቤተክርስትያን አምልኮ ከክርስቲያናዊ ነጸብራቅ የተገኙትን አንዳንድ ግንዛቤዎችን እንመረምራለን፣ ይህም “ምስጢረ ቁርባን” እና “ሥርዓት” የሚሉትን ቃላት አጭር ጥናት እንዲሁም ስለ ጥምቀት እና የጌታ ራት በቤተክርስቲያን አምልኮ ላይ ስለሚተገበሩ የተለያዩ አመለካከቶች ጭምር እንመለከታለን። በተጨማሪም የቤተክርስቲያንን አምልኮ ሥነ-መለኮታዊ ዓላማ እናገኘዋለን፣ እርሱም በብቸኝነት ቅድስናው፣ ወሰን በሌለው ውበቱ፣ ተወዳዳሪ በሌለው ክብሩ እና አቻ በሌለው ስራዎቹ የተነሳ እግዚአብሔርን ማክበር ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ወደ አምላከ ስላሴ በመቅረብ፣ ቤተክርስቲያን በምስጋና እና በውዳሴ፣ እና በሥርዓተ ቅዳሴ ለቃሉና ለምስጢራት አጽንዖት ይሰጣል። ቤተክርስቲያንም እንደ ቃል ኪዳን ማህበረሰብ እግዚአብሔርን በመታዘዟ እና በአኗኗሯ ታመልካለች።
6 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ቤተክርስቲያን እንደ ምስክር የተሰኘው ሶስተኛው ትምህርት ደግሞ በቤተክርስቲያን ተልዕኮ ላይ ያተኩራል። በዚህ ትምህርት ውስጥ ለኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ምርጦች የሚለውን ሃሳብ ለተመረጠው ሕዝብ ለእስራኤል እና ለቤተክርስቲያን፣ እንዲሁም ለግለሰብ አማኞች የሚሠራበትን የመመረጥ ትምህርት በጣም አስፈላጊ የሆኑትን ገጽታዎችን እንሸፍናለን። ኢየሱስ ክርስቶስን እግዚአብሔር ከዓለም ሕዝብን ለራሱ እንዳዳነበት እንደ እግዚአብሔር ምርጥ እናገኘዋለን። በተጨማሪም በእግዚአብሔር አስቀድሞ ስለመመረጥ ጽንሰ ሐሳብ ከእስራኤል እንደ እግዚአብሔር ህዝብ እና እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን መሰየም አንጻር የጽንሰ ሃሳቡን ስፋትና ፍቺ በአጭሩ እንቃኛለን። እንደ እግዚአብሔር የታላቁ ተልእኮ መሣሪያ በውስጡ ያሉትን ሦስት ወሳኝ ነገሮች እንመረምራለን፡ እነዚህም ቤተክርስቲያን ለጠፉት ወንጌልን ስትሰብክ፣ አዳዲስ አማኞችን በክርስቶስ ስታጠምቅ፣ ማለትም እነርሱን ወደ ቤተክርስቲያን አባልነት ስታካትት፣ እና ብልቶቿ ክርስቶስ ያዘዘውን ሁሉ እንዲጠብቁ ስታስተምር ናቸው። በመጨረሻም በሥራ ላይ ያለች ቤተክርስቲያን በተሰኘው በትምህርት አራት የቤተክርስቲያንን የተለያዩ ገጽታዎች እና አካላትን እንመለከታለን። የቤተክርስቲያን ድርጊቶች እና የአኗኗር ዘይቤዎች እውነተኛ ምልክቶች በሆኑት የተወሰኑ ምልክቶች ላይ በማተኮር እውነተኛውን የክርስቲያን ማህበረሰብ እንዴት ልንለይ እንደምንችል ልዩ ትኩረት ይሰጣል። የቤተክርስቲያን ምልክቶችን ከኒቂያው የእምነት መግለጫ እና እንዲሁም ከተሐድሶ ትምህርት አንጻር እንቃኛለን። እንዲሁም በክርስቲያኖች ላይ አስገዳጅ ናቸው የሚባሉ ወጎችን እና ትምህርቶችን ለመረዳት እና ለመገምገም አጋዥ መመሪያ በሆነው በቪንሴንሺያን ደንብ መነፅር ቤተክርስቲያንን እንመለከታለን። ይህን ጥናት በአዲስ ኪዳን በተጠቀሱት የእግዚአብሔር ቤተ ክርስትያን ምስሎች (የእግዚአብሔር ቤተሰብ)፣ በክርስቶስ አካል እና በመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ (የእግዚአብሔር መንግሥት ወኪል) ምስሎች ውስጥ በሚኖረው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ በማተኮር ጥናታችንን እንቋጫለን። ቤተክርስቲያንን በበጉ ጦርነት ውስጥ እንደምትዋጋ የእግዚአብሔርን ሰራዊት እንመለከታለን። እነዚህ ምስሎች ዛሬ በአለም ላይ የቤተክርስቲያንን ማንነት እና ስራ እንዴት ልንረዳ እንደሚገባን ትልቅ ግንዛቤን ይሰጣሉ። ያለ ጥርጥር፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር የመንግሥቱ እና የመገኘቱ ሰዎች ወኪል ናት። የዚህን ትምህርት እና የእግዚአብሔር ቃል ጥናት በውስጥህ የእግዚአብሔር ህዝብ ለሆኑት ለቅዱሳን ጥቅም ለመኖር እና ለማነጽ ጥልቅ ፍቅርን ይጨምርልህ!
እግዚአብሔር ቅዱስ ቃሉን በትጋት ስለምታጠና አብዝቶ ይባርክህ።
- ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ
/ 7
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
የኮርሱ መስፈርቶች
• መጽሐፍ ቅዱስ (ለዚህ ትምህርት ዓላማ ሲባል የአንተ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም መሆን አለበት [ለምሳሌ NIV, NASB, RSV, KJV, NKJV, ወዘተ] እና የትርጓሜ ሐረግ መሆን የለበትም [ለምሳሌ The Living Bible, The Message] • እያንዳንዱ የካፕስቶን ሞጁል በሙሉ ትምህርቱ የሚነበቡ እና የሚያወያዩ የመማሪያ መጽሀፎችን አካትቷል ፡፡ እነዚህን ከመምህርህ እና አብረው ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር በመሆን እንድታነብ፣ እንድታሰላስል እና እንድትመልስ እናበረታታሃለን ፡፡ እነዚህ ጽሑፎች በበቂ ሁነታ መገኘት ባለመቻላቸው ምክንያት (ለምሳሌ ፣ በቂ የመጻሕፍቱ ሕትመት ካለመኖሩ የተነሳ) የካፕስቶን አስፈላጊ የመማሪያ መጽሐፍ ዝርዝራችንን በድረ-ገፃችን ላይ እናስቀምጣለን። የዚህን መጽሐፍ (ሞጁል) ጽሑፎች ወቅታዊ ዝርዝር ለማግኘት እባክህን www.tumi.org/booksን ጎብኝ። • የክፍል ውስጥ ሥራዎችን ለመስራት እና ማስታወሻዎችን ለመውሰድ ወረቀት እና ብዕር ፡፡ • Allen, Roland. The Spontaneous Expansion of the Church . Grand Rapids: Eerdmans, 1962. • Costas, Orlando. The Church and Its Mission: A Shattering Critique from the Third World . Wheaton: Tyndale Press, 1974. • Green, Michael. Evangelism in the Early Church . Grand Rapids: Eerdmans, 1970. • Richards, Lawrence. A New Face for the Church . Grand Rapids: Zondervan, 1970.
አስፈላጊ መጻሕፍት እና ቁሳቁሶች
የተጠቆሙ ንባቦች
8 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
የግምገማዎች እና የምዘናዎች ድምር ውጤት በክፍል መገኘት እና የክፍል ውስጥ ተሳትፎ
የኮርሱ መስፈርቶች
30% 90 ነጥቦች
ፈተናዎች
10% 30 ነጥቦች
የቃል ጥናት ጥቅሶች
15% 45 ነጥቦች
የእክሴጀሲስ ፕሮጀክት
15% 45 ነጥቦች
የሚኒስትሪ ፕሮጀክት
10% 30 ነጥቦች
ንባቦች እና የቤት ስራዎች
10% 30 ነጥቦች
የማጠቃለያ ፈተና
10% 30 ነጥቦች
ጠቅላላ ድምር: 100% 300 ነጥቦች
አጠቃላይ ውጤት መመዘኛ መስፈርቶች በእያንዳንዱ የትምህርት ክፍለ ጊዜ መገኘት የኮርሱ ቅድመ ሁኔታ ነው ፡፡ መቅረት በውጤትህ ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል። በአስገዳጅ ምክንያት መቅረት ግድ በሚሆንበት ጊዜ እባክህ አስቀድመህ ለመምህርህ አሳውቅ ፡፡ ያመለጠህ ክፍለ ጊዜ ሲያጋጥም ያመለጠህን የቤት ሥራ መስራት እና ስለዘገየህበት ሁኔታ ከመምህሩ ጋር መነጋገር የአንተ ኃላፊነት ነው። ይህ ኮርስ ባብዛኛው በውይይት መልክ የሚካሄድ እንደመሆኑ መጠን የአንተ ንቁ ተሳትፎ በእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ ውስጥ የሚፈለግና የሚጠበቅ ይሆናል። እያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ የሚጀምረው ካለፈው ትምህርት መሠረታዊ በሆኑት ሀሳቦች ላይ በተመሰረተ በአጭር ፈተና ይሆናል። ለፈተናው ለመዘጋጀት ደግሞ የተሻለው መንገድ ባለፈው ትምህርት ወቅት የተወሰዱ የተማሪውን መልመጃ (Student Workbook) እና የክፍል ማስታወሻዎችን መከለስ ነው ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ አማኝ እና መሪ እንደመሆንህ መጠን በቃልህ ያጠናኸው ጥቅስ(ቃል) ለህይወትህ እና ለአገልግሎትህ መሰረት ነው ፡፡ በአንጻራዊነት ጥቅሶቹ ከቁጥር አንጻር ጥቂት ቢሆኑም በይዘታቸው ግን ጠቀሜታቸው የጎላ ነው፡፡ በእያንዳንዱ የትምህርት ክፍለ ጊዜ የተሰጡትን ጥቅሶች (በቃል ወይም በፅሁፍ) ለመምህርህ እንድትናገር ወይም እንድታነብብ ይጠበቅብሃል ፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር ወንድ እና ሴት ልጆች ለተጠሩበት የአገልግሎት ድርሻ ሁሉ ለማስታጠቅ የእግዚአብሔር ልዩ መሳሪያ ናቸው (2 ጢሞ. 3.16-17) ፡፡ ለዚህ ኮርስ የሚያስፈልጉትን መመዘኛዎች ለማጠናቀቅ አንድ መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በመምረጥ በንባቡ ላይ ተግባራዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት (ማለትም ፣ የትርጓሜ ጥናት) ማድረግ አለብህ ፡፡ ጥናቱ አምስት ገጾች ርዝመት ሊኖረው ይገባል (በድርብ የተከፋፈለ ፣ ታይፕ የተደረገ ወይም በጥሩ ሁኔታ በእጅ የተፃፈ) እና በዚህ ትምህርት ውስጥ ጎላ ብለው ከተነሱት የክርስቲያን ሚሽን መሠረተ-ትምህርቶች እና መርሆዎች
በክፍል መገኘት እና የክፍል ውስጥ ተሳትፎ
ፈተናዎች
የቃል ጥናት ጥቅስ
የእክሴጀሲስ ፕሮጀክት
/ 9
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ውስጥ አንዱ ላይ ያተኮረ መሆን ይኖርበታል፡፡ ፍላጎታችን እና ተስፋችን ቅዱሳት መጻሕፍት የአንተን እና የምታገለግላቸውን ሰዎች ሕይወት በተጨባጭ ለመለወጥ ያላቸውን አቅም እንዲረዱ ነው። ኮርሱን በምትወስድበት ጊዜ የበለጠ ለማጥናት በምትፈልገው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ የንባብ ክፍል (በግምት ከ4-9 ቁጥሮች) ለማጥናት አታመንታ፡፡ የፕሮጀክቱ ዝርዝሮች በገጽ 10-11 ላይ የተካተቱ ሲሆን በዚህ ትምህርት መግቢያ ክፍል ውስጥ ይብራራሉ ፡፡ እኛ የምንጠብቀው ሁሉም ተማሪዎች ትምህርታቸውን በሕይወታቸው ውስጥ እና በአገልግሎት ድርሻቸው ላይ በተጨባጭ እንዲተገብሩት ነው ፡፡ ተማሪው የተማራቸውን መርሆዎች ከተግባራዊ አገልግሎት ጋር አጣምሮ የሚኒስትሪ ኘሮጀክት የማዘጋጀት ኃላፊነት አለበት ፡፡ የዚህ ፕሮጀክት ዝርዝሮች በገጽ 12 ላይ የተሸፈኑ ሲሆን በትምህርቱ መግቢያ ክፍል ውስጥ ይብራራሉ ፡፡ የክፍል ሥራ እና የተለያዩ ዓይነት የቤት ሥራዎች በክፍል ትምህርት ወቅት በመምህርህ ሊሰጡህ ወይም በተማሪው መልመጃ (Student Workbook) ውስጥ ሊጻፉ ይችላሉ፡፡ ስለሚፈለገው ነገርም ሆነ የቤት ስራ ስለ ማስረከቢያው ጊዜ ጥያቄ ካለህ መምህርህን ጠይቅ። ለክፍል ውይይት ለመዘጋጀት ተማሪው የተመደበውን ንባብ ከጽሑፉ እና ከቅዱሳት መጻሕፍት ማንበቡ አስፈላጊ ነው ፡፡ እባክህ በየሳምንቱ ከአንተ የተማሪው የመልመጃ መጽሐፍ ውስጥ “የንባብ ማጠናቀቂያ ቅጽ” ን ተመልከት። ለሚደረጉ ተጨማሪ ንባቦች ተጨማሪ ዋጋ/ነጥብ የማግኘት እድል ይኖራል ፡፡ በትምህርቱ መጨረሻ ላይ መምህርህ በቤት ውስጥ የሚጠናቀቅ የመጨረሻ ፈተና (የተዘጋ መጽሐፍ) ይሰጥሃል። በትምህርቱ ውስጥ የተማርከውን እና በአገልግሎትህ ላይ ያለህን አስተሳሰብ ወይም አሠራር እንዴት እንደሚነካው እንድታንጸባርቅ የሚረዳ ጥያቄ ትጠየቃለህ፡፡ ስለ መጨረሻው ፈተና እና ሌሎች ጉዳዮች መምህርህ አስፈላጊውን መረጃዎች ይሰጥሃል።
የሚኒስትሪ ፕሮጀክት
የክፍል እና የቤት ሥራ ምደባዎች
ንባቦች
ከቤት-የሚሰራ የማጠቃለያ ፈተና
ውጤት አሰጥጥ የሚከተሉት ውጤቶች በክፍለ-ጊዜው መጨረሻ ላይ በዚህ ክፍል ውስጥ ይሰጣሉ እናም በእያንዳንዱ ተማሪ መዝገብ ላይ ይቀመጣሉ።
A - የላቀ ሥራ
D - የማለፊያ ሥራ
B - በጣም ጥሩ ሥራ
F - አጥጋቢ ያልሆነ ሥራ
C - አጥጋቢ ሥራ
I - ያልተሟላ
ለእያንዳንዱ የመጨረሻ ክፍል አግባብነት ያላቸው ውጤቶች ይሰጣቸዋል ፣ ለእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ የሚሰጠው የክፍል ነጥብ በጠቅላላው አማካይነት ውጤት ላይ የሚታሰብ ይሆናል። ያልተፈቀደ የስራ መዘግየት ወይም ሥራዎችን አለማስረከብ በውጤትህ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ፣ ስለሆነም እባክህ አስቀድመህ አቅደህ ከመምህርህ ጋር ተነጋገር።
1 0 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
የኤክሴጄሲስ ፕሮጀክት በካፕስቶን ፋውንዴሽን የቤተየክርስቲያን ስነ መለኮት የጥናት ሞጁል ተሳታፊ እንደመሆንህ መጠን ከሚከተሉት ንባቦች በአንዱ ላይ የክርስቲያን ሚሽን እና የከተማ አገልግሎት ምንነት ላይ ኤክሴጄሲስ (ኢንደክቲቭ ጥናት) እንድትሰራ ትጠየቃለህ። ሮሜ 12:3-8 ገላትያ 3:22-29 1 ቆሮንቶስ 12.1-27 ኤፌሶን 2.11-22 ኤፌሶን 4.1-16 1 ጴጥሮስ 2:9-10 የዚህ ፕሮጀክት አላማ ስለ ቤተክርስቲያን ዋና ምንባብ በዝርዝር እንድታጠና እድል ለመስጠት ነው። ከእነዚህ ንባቦች ውስጥ አንዱን ስታጠናና ስታሰላስል ተስፋችን ይህ ክፍል እንዴት የእግዚአብሔርን ለህዝቡ ያለውን ራእይ አንዳንድ ገፅታዎች እንደሚያበራ ትረዳ እና ታሳይ ዘንድ ነው። እናም በእርግጥ ጸሎታችን አንተ ቤተክርስቲያንን በተሻለ መንገድ በመረዳት፣ እነዚህን እውነቶች ከራስህ የግል የደቀመዝሙርነት ጉዞ፣ በቤተክርስቲያንህ ውስጥ ካለው አመራር እና ከከተማ አገልግሎት ጋር በማዛመድ የበለጠ ውጤታማ እንድትሆን ነው። ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮጀክት እንደመሆኑ የትርጓሜ ጥናት (ኤክሴጄሲስ) ለመስራት የጥናት ክፍሉን በአውዱ ውስጥ መረዳት ያስፈልጋል። በመቀጠልም ዋናውን ትርጉም ከተረዳህ በኋላ ለሁላችንም ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል መርህ ማውጣትና ይህንም በተጨባጭ ከህይወት ጋር ማዛመድ ይኖርብሃል። ይህን የግል የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጥናት በምታደርግበት ወቅት እነዚህ ሶስት ደረጃዎች ሊያግዙህ ይችላሉ:- 1. በተሰጠው ምንባብ ውስጥ ለተጠቀሱት ዋና አድማጮች እግዚአብሔር መናገር የፈለገው ምንድነው? 2. ከዚህ ምንባብ ልንማረው የምንችለውና ለሁሉም ዘመንና በየትኛውም ቦታ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ ልንወስደው የምንችለው መርህ ምንድነው? 3. ዛሬምመንፈስ ቅዱስ እኔን ከተማርኩት መርህ በመነሳት ምን እንዳደርግ ነው የሚፈልግብኝ? እንግዲህ እነዚህን ጥያቄዎች በተገቢው መንገድ ከመለስክ በቀጣይ ለወረቀት ስራህ የግልህን መረዳት ለማቅረብ ዝግጁ ነህ ማለት ነው። ለወረቀት ስራህ ይህን ቅደም ተከተል ተከትሎ መስራት ይረዳሃል፥ 1. የመረጥከው የንባብ ክፍል ዋና ጭብጥ ወይም ሃሳብ ምን እንደሆነ ለይተህ አስቀምጥ። 2. የምንባቡን ዋና ትርጉም በአጭሩ ግለጽ (ይህን በሁለት ወይም በሶስት አንቀጽ ልታስቀምጠው ትችላለህ ወይም ደግሞ በእያንዳንዱ ቁጥር አጫጭር ማጣቀሻ ወይም ማመሳከሪያ እየተጠቀምክ መሄድ ትችላለህ።) 3. ይህ የምንባብ ክፍል ሊሰጠን የሚችሉ ከአንድ እስከ ሶስት የሚደርሱ የክርስቲያን ሚሽን መርሆዎችን ዘርዝር።
ዓላማ
ዝርዝር መግለጫ እና አወቃቀር
/ 1 1
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
4. ከመርሆዎቹ ውስጥ አንዱ፣ የተወሰኑት ወይም በጠቅላላው ከሚከተሉት ነጥቦች ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ አሳይ፥ ሀ. ከአንተ የግል መንፈሳዊ ህይወት እና ከጌታ ጋር ካለህ ጉዞ ጋር
ለ. በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ካለህ አገልግሎት ጋር
ሐ. ባለህበት ማህበረሰብም ሆነ በጠቅላላው ህብረተሰብ ውስጥ ከሚንጸባረቁ ሁኔታዎችና ችግሮች ጋር የዚህን ትምህርት (ሞጁል) መጽሐፍ እና ማጣቀሻዎችን እንደ መመሪያና እንደ መርጃ ለመጠቀም ነጻነት ይኑርህ፤ ይህን በምታደርግበት ወቅት ግን የሌላን ሰው ምልከታ ከተዋስክ ወይም በዛ ምልከታ ላይ የራስህን ከመሰረትክ ለባለሃሳቡ ዕውቅና መስጠትን መዘንጋት የለብህም። ለዚህም የጽሁፍ ውስጥ ማጣቀሻዎችን፣ የግርጌ ማስታወሻዎችን፣ ወይም የመጨረሻ ማስታወሻዎችን ተጠቀም። የተጠቀምከው የማስታወሻ ዘዴ ተቀባይነት የሚኖረው 1) በጠቅላላው የጽሁፍ ስራህ ውስጥ ወጥነት ያለው ሲሆንና 2) የተጠቀምከውን የሌላን ሰው ሃሳብ በትክክል የሚያመለክት ሲሆንና ተገቢውን እውቅና ሲሰጥ ብቻ ነው ፡፡(ለተጨማሪ መረጃ ከአባሪዎች ገጽ ላይ Documenting Your Work : A guide to Help You Give Credit Where Credit is Due ተመልከት ፡፡) የትርጓሜ ጥናቱ (ኤክሴጄቲካል ፕሮጀክቱ) የሚከተሉትን መመዘኛዎች የሚያሟላ መሆኑን አረጋግጥ:- • በአግባቡ መጻፉን(ታይፕ መደረጉን) • ከላይ ከተሰጡት ምንባቦች የአንዱ ጥናት መሆኑን • ሳይዘገይ በቀኑና በሰኣቱ ገቢ መደረጉን • ርዘመቱ 5 ገጽ መሆኑን • ከላይ የተሰጠውን መመሪያ ተከትሎ መሰራቱንና አንባቢው በቀላሉ ተከትሎ ሊረዳው የሚችል መሆኑን • ምንባቡ ከህይወትና ከአገልግሎት ጋር ያላቸውን ዝምድና የሚያሳይ መሆኑን እነዚህን መመሪያዎች አይተህ አትደናገጥ፤ ይህ የመጽሀፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮጀክት ነው፤ ማድረግ የሚያስፈልግህ ምንባቡን በደንብ ማጥናት፤ ከምንባቡ ውስጥ ትርጉም መፈለግ፤ ከዚያም ቁልፍ የሆኑ መርሆዎችን ከምነባቡ ማውጣት እና መርሆዎቹንም ከህይወትና ከአገልግሎት ጋር ማዛመድ ናቸው፡፡ ይህ የትርጓሜ ጥናት (ኤክሴጄቲካል ፕሮጀክት) የ45 ነጥቦች ዋጋ ያለው ሲሆን ከጠቅላላው የዚህ ኮርስ ውጤት 15% ይይዛል፡፡ ስለዚህ በተቻለህ መጠን ስራህን የላቀና አስተማሪ አድርገሀ ለማቅረብ ሞክር፡፡
ምዘና
1 2 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
የሚኒስትሪ ፕሮጀክት የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤” (ዕብራውያን 4፡12)፡፡ ሐዋሪያው ያዕቆብ ሰሚዎች ብቻ ሳይሆን አድራጊዎችም ጭምር እንድንሆን አጽንኦት ሰጥቶ ይናገራል፡፡ ቃሉን በተግባር ላይ እንድናውለውም ይመክረናል፡ ፡ ይህን ልምምድ መዘንጋት የተፈጥሮ ፊታችንን በመስታውት ውስጥ ተመልክተን ወዲያው ማንነታችንን ከመርሳት ጋር ያመሳስለዋል፡፡ በማንኛውም ሁኔታ የእግዚአብሔርን ቃል የሚያደርግ ሰው በነገር ሁሉ ይባረካል (ያዕቆብ 1፡22-25)፡፡ እኛም መሻታችን የምንቀስመውን ትምህርት በግል ህይወትህ፣ በአገልግሎትህና በቤተክርስቲያንህ ውስት ካሉ ተጨባጭ ሁኔታዎችና ፍላጎቶች ጋር በማዛመድ በተግባር ስታውለው መመልከት ነው፡ ፡ በመሆኑም የዚህ ትምህርት (ኮርስ) ዋና ዓላማ ከዚህ ኮርስ የተማርካቸውን ነገሮች ከሌሎች ጋር ልትከፋፈልበት የምትችልበት የሚኒስትሪ ፕሮጀክት መቅረጽ እንድትችል ነው፡፡ 1 Peter 2:9-10 describes the Church as a race, a nation, an order of priests, and a people. None of these terms allow us to understand our salvation as a purely individual idea. The focus of this ministry project is to help you sharpen your skills in explaining the relationship between salvation and the Church. Please complete each of the following steps: Identify and briefly describe in writing a situation in your past or current experience where a person you know is giving evidence that they do not consider the Church an important part of their spiritual life. (You can use a fictitious name for this person if you would like to keep their identity confidential.) This neglect of the Church may be expressed in their words; “I don’t feel like I have to go to church in order to worship God!” Or it may be expressed in their behavior; they claim to have a vital Christian experience but rarely, if ever, attend church. Write a sample letter to this person laying out simply in your own words the reasons that you believe they have misunderstood what the Bible teaches about salvation and the Church. The content of this letter should draw from, and demonstrate familiarity with, the theology which you have learned in this course. The point of this letter is to move the theological ideas into practical experience. It is not a “theology paper” but the communication of sound biblical teaching to a person who either misunderstands or deliberately disobeys the Scriptures. Turn in a copy of the letter to your instructor. Then, prayerfully consider whether God might have you approach the person you wrote about (if it is a current situation) and either send them the letter or talk to them in person about their salvation and church life. The Ministry Project is worth 30 points and represents 10% of your overall grade, so make certain to share your insights with confidence and make your summary clear.
ዓላማ
እቅድ እና ማጠቃለያ
Step One
Step Two
Step Three
Grading
/ 1 3
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
በእግዚአብሔር እቅድ ጥላ ውስጥ ያለች ቤተክርስቲያን
ት ም ህ ር ት 1
የትምህርቱ ዓላማዎች
ሃያል በሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን ! የዚህን ትምህርት መጽሐፍ ካነበብክ፥ ካጠናህ፥ ውይይት ካካሄድክና ወደ ተግባር ከቀየርከው በኋላ የሚከተሉትን ማድረግ ትችላለህ:- • ቤተክርስቲያን እንዴት በእግዚአብሔር ከፍ ባለ አላማ እንደምትታይ ማብራራት ትችላለህ: ማለትም እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር በገባው ቃል ኪዳን አማካኝነት በአዲሱ ሰው በኩል ክብርን ለማምጣት መወሰኑን ትረዳለህ። • ለጸጋው የድነት እቅዱ መገለጥ፣ አህዛብ በክርስቶስ ኢየሱስ የተካተቱበትን ታላቅ ምስጢር ለመግለፅ ከቤተክርስቲያን ጋር የተገናኙ ተዛማጅ መፅሃፍቶችን እና ፅንሰ-ሀሳቦችን ትገነዘባለህ። • ቤተክርስቲያን በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በተገለጠው የእግዚአብሔር እቅድ ጥላ ውስጥ እንዴት እንደምትገለጽ በዝርዝር መናገር ትችላለህ፣ ከመጀመሪያ ጀምሮ የእግዚአብሔር ሃሳብ ለራሱ የተለየ እና ምርጥ የሆነ የእግዚአብሔርን ህዝብ መፍጠር ነበር፣ ይህም የእግዚአብሔር ላኦስ ነው። • መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነን የመዳን ትርጓሜ መስጠት እና ይህም በቤተክርስቲያን ውስጥ ከሚኖር ተሳትፎ ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ትረዳለህ። • ቤተክርስቲያን ከብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ህዝቦች ጋር ስላላት ግንኙነት የሚገልጽ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ማሰላሰል ትችላለህ። ቅዱስ ህዝብ 1ኛ ጴጥሮስ 2፡9-10 አንብብ። “ቤተክርስቲያን” የሚለው ቃል ብዙ ምስሎችን ወደ አእምሯችን ያመጣል። ለብዙ ሰዎች “ቤተ ክርስቲያን” የሚለውን ቃል ሲሰሙ በመጀመሪያ የሚያስቡት ነገር ከላይ መስቀል ያለበት ሕንፃ ነው። ነገር ግን ሐዋርያው ጴጥሮስ ስለ ቤተክርስቲያን የሚያስበው እንደዛ አይደለም። ለጴጥሮስ ቤተክርስትያን እግዚአብሔር እርሱን እንዲያገለግሉት እና ስሙን በምድር ላይ እንዲወክሉ የመረጣቸው ሰዎች ልዩ የሆነ ስብስብ ነው። በእነዚህ ጥቅሶች ላይ ጴጥሮስ በዘፀአት 19.5-6 ላይ እግዚአብሔር ለእስራኤል የተናገረበትን ቋንቋ ተጠቅሟል፡- “አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ፤ እናንተም የካህናት መንግሥት የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ። ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ቃል ይህ ነው።” ጴጥሮስም ደግሞ አሕዛብን አካትታ ለያዘች ቤተ ክርስቲያን እየተናገረ መሆኑን እያወቀ፣ “እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን
1
ጥሞና
1 4 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።” ይላቸዋል። ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር የተመረጠ ሕዝብ ናት፣ እርሱን የሚያመልኩት ካህናት። ስለዚህም ቤተክርስቲያን አሁን በአሕዛብ ሁሉ መካከል በእግዚአብሔር መንግሥት እሴቶች በዓለም ውስጥ የምትኖር የእግዚአብሔር ሕዝብ ነች። እንግዲህ የእኛ ተግባር በእግዚአብሔር የሚመራ ዓለም ምን እንደሚመስል ለማወቅ የሚፈልግ ሰው ቤተክርስቲያንን በማየት ብቻ ሊያውቅ በሚችልበት መንገድ መኖር ነው። እንዴት ያለ ታላቅ ዕድል እና ክቡር ጥሪ ነው። የኒቂያን የእምነት መግለጫ (በአባሪው ውስጥ ይገኛል) ካነበብክ እና/ወይም ከዘመርክ በኋላ የሚከተለውን ጸሎት ጸልይ፥ የአብርሃም፣ የይስሐቅ እና የያዕቆብ አምላክ፣ በኢየሱስ ያመንነውን የአብርሃም ልጆች እና ለእርሱ የገባኸውን የተስፋ ቃል ወራሾች አድርገህ ስላካተትከን በጣም አድርገን እናመሰግንሃለን። አባት ሆይ፣ በዚህ በኃጢአተኛ ዓለም ውስጥ አንተን በትክክል እንድንወክል እርዳን። በተራራ ላይ እንዳለች ከተማ እንድንደምቅ በዙሪያችን ካሉ አሕዛብ እንድንለይ እርዳን። ሰዎች ያንተን ልብ እንዲገነዘቡ እና በሰማያት የምትኖር አባታችን ለአንተ ክብር የሚያመጡበትን መልካም ሥራ እንሰራ ዘንድ እርዳን። ከሁሉም በላይ ደግሞ ሰዎች ሁሉ ከመረጥከው ሕዝብህ ጋር የመካተት ዕድል ያገኙ ዘንድ የኢየሱስን ወንጌል በድፍረት እንድንሰብክ እርዳን። ይህንም ከአንተና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ለዘላለም በሚነግስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጸልያለን። አሜን።
የኒቂያ የእምነት መግለጫ እና ጸሎት
1
ይህ ትምህርት ፈተና የለውም
ፈተና
የቃል ጥናት ጥቅስ ምዘና
ይህ ትምህርት የቃል ጥናት ጥቅስ የለውም
የቤት ስራ/መልመጃ ማስረከቢያ
ይህ ትምህርት የቤት ስራ/መልመጃ የለውም
እውቂያ
ስለወደፊቱ የባከነ በጣም ብዙ ጊዜ
መጋቢው ስለመጨረሻው ዘመን ሲሰጥ ከነበረው ሴሚናር በኋላ፣ ከምእመናን አንዱ በመኪና ማቆሚያው ቦታ ላይ አስተያየት ሰጥቷል፣ “በትልልቅ ምስል ጉዳዮች ላይ ብዙ ጊዜ ማጥፋታችን ለምን እንደሚያስፈልገን በትክክል አልገባኝም። ለዛም ነው ቤተክርስቲያን ለአብዛኞቹ ሰዎች በጣም አሰልቺ የሆነችው - ዛሬ በሚከሰቱ ነገሮች ላይ እንዴት ማተኮር እንዳለብን አናውቅም። ሁሉም ነገር ላም አለኝ በሰማይ ነው፣ ስለ አንዳንድ የወደፊት ገነት፣ እግዚአብሔር አንድ ቀን ስለሚያደርገው ነገር
1
/ 1 5
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
አንዳንድ የጠፈር ዓላማ ነው። ስለ ‘ትልቅ ምስል’ ነገሮች ሁልጊዜ ማውራት ለምን እንደሚያስፈልገን በእውነት አልገባኝም። ዛሬ ማድረግ ያለብኝ ነገር ላይ ማተኮር አለብኝ!” በዚህ መንገድ ጫና ውስጥ ላለው ምእመን ምላሽህ ምን ይሆን?”
ማንነት አንድ ወረቀት አውጥተህ የማያውቅህ ሰው ማን እንደሆንክ እና ለአንተ አስፈላጊ የሆነውን ነገር እንዲገነዘብ የሚረዱ ምልክቶችን ወይም ትናንሽ ምስሎችን አስቀምጥ። ከዚያም እነዚህን ስዕሎች ስለማጋራት መምህርህ የሚሰጠውን መመሪያ ተከተል። የዳኑ እና የጠፉ ቅዱሳት መጻሕፍት ስለ “ዳኑ” እና “ስለጠፉ” ሰዎች መናገር ይችላሉ፣ ብዙ ጊዜም ይናገራሉ። ወንጌልን ሰምቶ ለማያውቅ ሰው ይህ ለመረዳት አስቸጋሪ ቋንቋ ሊሆን ይችላል። ወደ አእምሯችን የሚመጡት የተፈጥሮ ጥያቄዎች “ከምን የዳኑ ናቸው?” እና “እኔ ‘የጠፋሁ ነኝ’ ስትል ምን ማለትህ ነው?” እነዚህን ጥያቄዎች ለጠየቀህ ሰው እንዴት ትመልሳለህ?
2
1
3
በእግዚአብሔር እቅድ ጥላ ውስጥ ያለች ቤተክርስቲያን ክፍል 1
ይዘት
ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ
ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር ከፍ ባለ አላማ ጥላ ውስጥ ትታያለች። እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር በገባው ቃል ኪዳን አማካኝነት በአዲሱ የሰው ዘር በኩል ክብርን ለራሱ ለማምጣት ወስኗል። እንዲሁም አሕዛብን በመንግሥቱ ዓላማ ውስጥ የማካተት አስደናቂ ሐሳብን በሚያካትት ለጸጋው የደኅንነት ዕቅዱ መገለጥ በምሳሌነት ተንጸባርቋል። በመጨረሻም፣ ቤተክርስቲያን ለራሱ ልዩ እና ምርጥ የሆነን የእግዚአብሔር ላኦስ ህዝብ ለመፍጠር በእግዚአብሔር በተገለጠው የቅዱሳት መጻህፍት ሥዕላዊ መግለጫ ትታያለች። የዚህ በእግዚአብሔር እቅድ ጥላ ውስጥ ያለች ቤተክርስቲያን የተሰኘ ትምህርት የመጀመሪያ ክፍል አላማችን የሚከተሉትን ነጥቦች እንድትመለከት ለማስቻል ነው፡- • ቤተክርስቲያን ከእርሱ ጋር ለዘላለም በሚኖረው በአዲሱ የሰው ዘር በኩል ክብርን ለእግዚአብሔር ለማምጣት በእግዚአብሔር ከፍ ባለ አላማ ጥላ ውስጥ ትታያለች። • ቤተክርስቲያን አሕዛብን ለዓለም ባለው ቤዛነት ዓላማ ውስጥ ለማካተት በገባው የተስፋ ቃል ጥላ ውስጥ ነች።
የክፍል 1 ማጠቃለያ
1 6 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
• ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር ለራሱ የተለየ ሕዝብ ሆኖ የሚኖረውን ሕዝብ (ላኦስ) ለማስነሳት በሚያደርገው ጥረት የእግዚአብሔር ጥላ ውስጥ ነች። • እግዚአብሔር ከምድር አሕዛብ ሁሉ ለራሱ የሚሆንን ሕዝብ ለማውጣት በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ እየሠራ ነው።
I. የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር የላቀ ዓላማ ውስጥ ተጠልላለች፡ እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር በገባው ቃል ኪዳን አማካኝነት በአዲሱ የሰው ዘር በኩል ክብርን ለራሱ ለማምጣት።
የቪዲዮ ሴግመንት 1 ዝርዝር
1
ሀ. የእግዚአብሔር ከፍተኛ ዓላማ ለስሙ ክብር ማምጣት ነው።
1. ፍጥረት ሁሉ በፈቃዱና በኃይሉ ለክብሩም ተፈጽሟል።
ሀ. ዘጸ. 20.11
ለ. ኢሳ. 40፡26-28
ሐ. ኤር. 32.17
2. መዝሙረኛው እግዚአብሔር የመረጠውና የማዳን እቅዱን ለሕዝቡ ለእስራኤል የሠራውና ጠላቶቹን በእቅዱ ያሸነፈው ለክብሩ እንደሆነ ተናግሯል፣ መዝ. 135.8-12.
ለ. እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር የገባው ቃል ኪዳን፡ በእርሱ በኩል የምድር ወገኖች ሁሉ ይባረኩ ዘንድ ነው፣ ዘፍ. 12.1-3.
ይህ ጽሑፍ በግልጽ እንደሚያሳየው፡-
1. በአብርሃም ዘር በኩል የምድር አህዛብ ሁሉ ይባረካሉ።
/ 1 7
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
2. የተስፋው ቃል በአብርሃም የዘር ሐረግ የእግዚአብሔር መለኮታዊ ሥራ ይሆናል።
ሐ. ይህ ቃል ኪዳን አሕዛብን ጨምሮ፣ ሁሉም በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ የተዋጁትን ሕዝብን ለራሱ ለማውጣት የእግዚአብሔርን የላቀ ዓላማ ገልጧል፣ ገላ. 3.6-9. ይህ ጽሑፍ በአብርሃም ቃል ኪዳን በኩል ለቤተክርስቲያን ጥላነት በርካታ ጠቃሚ እንድምታዎች አሉት።
1. የአብርሃም እምነት እንደ ጽድቅ ተቆጠረ።
1
2. አማኞች እግዚአብሔር ለአብርሃም ከገባው የተስፋ ቃል ጋር ተዛመዱ።
3. እግዚአብሔር በአብርሃም ቃል ኪዳን በማመን አሕዛብን እንደሚያጸድቅ ቅዱሳት መጻሕፍት አስቀድመው አመላክተዋል።
II. ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር የማይታጠፍ እቅድ ተጠልላለች፡ በኢየሱስ ክርስቶስ፣ እግዚአብሔር ለዓለም ሁሉ የራሱን ክብር በአይሁድ እና በአህዛብ መካከል ለመመስረት ያለውን ምሥጢሩን ገልጧል። በአብርሃም የተስፋ ቃል አሕዛብን ለመቤዠት የእግዚአብሔር ምሥጢር መገለጡን ሦስት ግልጽ ጽሑፎች ያመለክታሉ።
ሀ. ጽሑፍ አንድ፡- ከጥንት ጀምሮ የተሰወረው ምሥጢር አሁን በነቢያትና በሐዋርያት ተገልጧል፣ ሮሜ. 16፡25-27።
ይህ ጽሑፍ በርካታ ወሳኝ ነጥቦችን ይጠቁማል፡-
1. ይህ ምስጢር፡ የኢየሱስ ክርስቶስ የወንጌል ስብከት
2. ይህ የኢየሱስ ክርስቶስ ስብከት ለብዙ ዘመናት ተሰውሮ የነበረው ምሥጢር ሲገለጥ ነው።
1 8 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
3. ይህ ምስጢር የእምነት መታዘዝን ለማምጣት በሐዋርያትና በነቢያት ለአሕዛብ ሁሉ ይገለጣል።
ለ. ጽሑፍ ሁለት፡ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ፣ የክብር ተስፋ የእግዚአብሔር ምሥጢር መገለጥ፣ ቆላ. 1፡25-29
ስለ ምስጢሩ የምንማራቸው ወሳኝ ግንዛቤዎች፡-
1. ለዘመናት እና ለትውልድ የተሰወረው ምስጢር አሁን ለቅዱሳኑ ተገልጧል።
1
2. እግዚአብሔር የዚህን ምሥጢር ክብር ባለጠግነት በአሕዛብ መካከል አስታወቀ።
3. ይህ ምሥጢር ክርስቶስ በእናንተ በአህዛብ ውስጥ ነው፥ እርሱም የክብር ተስፋችን ነው።
ሐ. ጽሑፍ ሦስት፡ የአሕዛብ በቤተክርስቲያን ውስጥ የመካተት የመክፈቻ ምሥጢር፣ ኤፌ. 3.4-12.
በክርስቶስ ያለው የእምነት ምስጢር፡-
1. ላለፉት ትውልዶች አልተገለጠም ነበር አሁን ግን ለክርስቶስ ቅዱሳን ሐዋርያት እና ነቢያት በመንፈስ ተገልጧል።
2. አሕዛብ አብረው ወራሾች ናቸውን? የአንድ አካል ብልቶች ናቸውን? በወንጌልስ በማመን በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን የተስፋ ቃል ተካፋዮች ናቸውን?
3. በሐዋርያዊ አገልግሎት፣ የእግዚአብሔር ምሥጢር ወደ ብርሃን ወጥቷል፡- እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያን በኩል ይህን ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ በሰማያዊ ስፍራ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት ያስታውቃል።
/ 1 9
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
III. ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር የራሱን የተለየ ህዝብ፣ የእግዚአብሔር ላኦስ ምስል በሰጠበት በእስራኤል ሕዝብ ጥላ ውስጥ ሆናለች፣ 2ኛ ቆሮ. 6፡16 እና 2 ተሰ. 2፡13-14።
ሀ. እስራኤል መሲህ የሚመጣበት መንገድ ናት።
1. እስራኤል ከመልአኩ ጋር ካደረገው ታላቅ የጸሎት ተጋድሎ በኋላ ለያዕቆብ እንደተሰጠ መጠሪያ፣ ዘፍ 32፡28
1
2. ይህ ለያዕቆብ ዘሮች የተሰጠ የጋራ መጠሪያ ስም ነው።
ሀ. አሥራ ሁለቱ ነገዶች “እስራኤላውያን” ይባላሉ።
ለ. “የእስራኤል ልጆች” ኢያሱ 3.17; 7.25; መሳፍንት። 8.27; ኤር. 3.21
ሐ. “የእስራኤል ቤት” ዘጸ. 16.31; 40.38
3. ይህ የአብርሃም ሥጋዊ የዘር ሐረግ፣ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታማኝነት ላይ ተመርጧል፣ ዘዳ. 7.6-8
4. የእግዚአብሔር ምርጫ እና ቃል ኪዳን ከአብርሃም፣ ከይስሐቅ እና ከያዕቆብ ጋር እስከ ዘሮቻቸው ድረስ ዘልቋል። መሲሑ በእስራኤል በኩል ይመጣል፣ በእርሱ በኩል ደግሞ መዳን ለዓለም ይመጣል።
ሀ. ዘጸ. 19.5-6
ለ. ዘዳ. 14.2
2 0 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ሐ. ዘዳ. 26፡18-19
መ. ዮሐንስ 4፡22
5. እስራኤላውያን እንደ እግዚአብሔር ሕዝብ ተለይተዋል፡- ዘጸ. 15.13, 16; ዘኁ. 14.8; ዘዳ. 32.9-10; ኢሳ. 62.4; ኤር. 12.7-10; እና ሆሴዕ. 1.9-10
6. አህዛብ አስቀድሞ እንደ እግዚአብሔር ሕዝብ ታይተው ነበር፣ ሮሜ. 9፡24-26
1
ለ. የእስራኤል ምስል እንደ እግዚአብሔር ሕዝብ አሁን ለቤተክርስቲያን እንደ እግዚአብሔር የቃል ኪዳን መንግሥት ማህበረሰብ ተተግብሯል።
1. ቤተክርስቲያን እንደ እግዚአብሔር አዲስ ሰው፣ አይሁድም ሆነ አህዛብ፣ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ሆነዋል፣ 1 ጴጥ. 2.9-10.
ሀ. የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የምትታወቀው በግርዛት ሳይሆን በኢየሱስ በማመን በሆነ አዲስ ፍጥረት ነው፣ 2ኛ ቆሮ. 5.17 (ፊልጵ. 3.2-3)።
ለ. የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የምትዛመደው በዜግነት ላይ ተመስርታ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት ላይ በተመሰረተውና በመንፈስ ቅዱስ መገኘት በታተመው በአዲሱ ኪዳን ነው፣ 2ቆሮ. 3.3-18.
2. ለእስራኤል ተሰጥተው የነበሩት ተስፋዎች አሁን ለቤተክርስቲያን ተሰጥተዋል።
ሀ. 2 ቆሮ. 6፡16-18
ለ. ዘጸ. 29.45
/ 2 1
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ሐ. ሌዋ. 26.12
3. ቤተክርስቲያን የተለየ ቦታ ቢሰጣትም፣ እስራኤልም ግን አልተተወችም ወይም ከምርጫ አልተሰረዘችም።
ሀ. ዘካርያስ በክርስቶስ ያለውን የቃል ኪዳን ፍጻሜ እንዳወጀ ሁሉ፣ ሉቃስ 1፡67 79፣ ጳውሎስም የእግዚአብሔር ቃል አሁንም እንደሚሰራ ያረጋግጥልናል፣ ሮሜ. 9.6.
1
ለ. ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ሕዝቡን አልጣለም። ሮሜ. 11.1.
ሐ. “የእግዚአብሔር ስጦታና ጥሪ የማይሻር ስለሆነ” በእግዚአብሔር የተጠራችው እስራኤል ትድናለች። ሮሜ. 11. 25-26, 29.
መ. የእግዚአብሔር ጸጋ እስራኤል እንደምትድን ያረጋግጣል፣ ሮሜ. 9.27-29; ኢሳ. 1፡24-26።
ማጠቃለያ
» ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር ከፍ ባለ ዓላማ ውስጥ ተጠልላለች፡ ከአብርሃም ጋር በገባው ቃል ኪዳን አማካኝነት በአዲሱ ሰው በኩል ክብርን ለማምጣት ወስኗል። » ቤተክርስቲያን አሕዛብን ለዓለም ባለው ቤዛነት ዓላማ ውስጥ ለማካተት በገባው የተስፋ ቃል ጥላ ውስጥ ነች።
» ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር የሕዝቡ ሥዕል፣ የእግዚአብሔር ላኦስ ጥላ ውስጥ ነበረች።
2 2 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
እነዚህን እና ሌሎች ቪዲዮው ያነሳቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ አስፈላጊውን ያህል ጊዜ ውሰድ። ለመጀመር ያህል እግዚአብሔር ለራሱ ክብርና ሞገስ ለማምጣት ስላለው ዓላማ፣ እና ይህም ሰዎችን ከምድር ለራሱ ለመቤዠት ካለው ከፍተኛ ዓላማ ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ግልጽ መሆን አለብን። እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር በገባው ቃል ኪዳን፣ የአህዛብ የወንጌል ተሳትፎን በሚመለከት ምስጢሩ መገለጥ እና የራሱን ሰዎች መፈጠር፣ ስለሚመጣው አዲሱ የሰው ልጅ ምስል፣ ስለ ዘላለማዊ አላማው ግልፅ ፍንጭ ይሰጣል። መልሶችህ ግልጽ እና አጭር ይሁኑ፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ በቅዱሳት መጻሕፍት አስደግፍ! 1. በእርሱ በኩል የምድር ነገዶች ሁሉ እንዲባረኩ እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር ቃል ኪዳን የገባው በምን መንገድ ነው? 2. እግዚአብሔር ስለ ፍጥረታቱ፣ ራሱን ስለመግለጡ እና ሌሎችን ለእርሱ ቤዛ አድርጎ ስለመውሰዱ የቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት ምንድ ነው? እግዚአብሔር አጽናፈ ሰማይን ለምን ፈጠረው? 3. በሮሜ 16፣ ኤፌሶን 3 እና ቆላስይስ 1 ላይ የእግዚአብሔርን የመቤዠት አላማ በተመለከተ የተነገረው ምስጢር ምን አይነት ነው? 4. እግዚአብሔር ሰዎችን ከምድር ለራሱ ለማውጣት ካለው ዓላማ ጋር በተያያዘ ከአህዛብ ጋር ስላለው ዓላማ ምን ገልጿል? ይህ ዓላማ እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር በገባው ቃል ኪዳን ውስጥ የሚታየው እንዴት ነው? 5. እስራኤል መሲሑ ወደ ዓለም እንዲመጣ የእግዚአብሔር መሣሪያ የሆነችው በምን መንገድ ነው? እስራኤል ከእግዚአብሔር ጋር ባላት ግንኙነት የእግዚአብሔርን ሕዝብ፣ የቤተክርስቲያንን ግልጽ ገጽታ እንዴት ትገልጣለች? 6. ሐዋርያት የእስራኤልን ተስፋ በኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ላይ እንዴት ይተገብራሉ? ምሳሌዎችን ስጥ። 7. በክርስቶስ በኩል ያለችው ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር የማዳን እቅድ ውስጥ ልዩ ቦታ ተሰጥቷታል። እንግዲህ የእስራኤል ቦታ እንደ እግዚአብሔር ሕዝብ ምንድር ነው? እግዚአብሔር እስራኤልን ትቷታልን ወይስ መመረጧን ሰርዟል? አብራራ።
መሸጋገሪያ 1
የተማሪው ጥያቄዎች እና ምላሾች
1
/ 2 3
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
በእግዚአብሔር እቅድ ጥላ ውስጥ ያለች ቤተክርስቲያን ሴግመንት 2፡ መዳን፡ የእግዚአብሔርን ሕዝብ መቀላቀል
ቄስ ቴሪ ኮርኔት
ሴግመንት 2 ማጠቃለያ
በኃጢአት ምክንያት፣ እያንዳንዱ ሰው ተስፋ ቢስ በሚመስል ሁኔታ ላይ ነው። ከኃጢአትና ከሚያስከትላቸው ውጤቶች መዳን በጣም ያስፈልገናል፣ ነገር ግን ኃጢአተኛ ተፈጥሮአችን የእግዚአብሔርን ማዳን እንዳንፈልግ ወይም ከእርሱ ጋር የምንገናኝበት ምንም ዓይነት መንገድ እንዳንይዝ ያደርገናል። በሚያስደንቅ ሁኔታ እግዚአብሔር እኛን እንደ ጠላቶቹ ሊተወን አልመረጠም። ሐዋርያው ጳውሎስ ገና በኃጢአት ቀንበር ስር ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአል ሲል ያስተምራል። ወንጌል ለራሳችን ማድረግ ለማንችለው ነገር እግዚአብሔር የሚያድነን ጸጋን እንደሚሰጠን የሚናገር የምሥራች ነው። ይህንን ጸጋ መረዳቱ የቤተክርስቲያን የአምልኮ ማህበረሰብ የመሆንን ሃላፊነት ለመገንዘብ መሰረት ነው። ድነት፡ የእግዚአብሔርን ህዝብ መቀላቀል የተሰኘው የዚህ ሴግመንት አላማችን የሚከተሉትን ማስቻል ነው፡- • ስለ ድነት ሥነ-መለኮታዊ ፍቺ ትሰጥ ዘንድ • ከእግዚአብሔር መለየት የሚያስከትለውን መዘዝ መግለጽ ትችል ዘንድ • ከክርስቶስ ጋር ባለን አንድነት የምናገኛቸውን ጥቅሞች መግለጽ ትችል ዘንድ • ዘፀአት ለክርስቲያን ድነት እንደ ምሳሌ (ዓብነት) እንዴት እንደሚያገለግል ትረዳ ዘንድ • ወደ ቤተክርስቲያን (የእግዚአብሔር ሰዎች) መቀላቀል ድነትን ተከትሎ የሚጨመር ነገር ሳይሆን የመዳን ትርጉም ማዕከል እንደሆነ ማስረዳት ትችል ዘንድ ነው።
1
2 4 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
I. መዳን ሲባል ምን ማለት ነው?
የቪዲዮ ሴግመንት 2 መመሪያ
ሀ. ብዙውን ጊዜ በአዲስ ኪዳን ድነት ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል soteria ነው። አንድን ሰው ለማዳን ወይም ለማዳን ወይም ለማዳን ማለት ነው።
1. ሮሜ. 1.16
2. 1 ተሰ. 5.9
1
3. 1 ጴጥ. 1.9
ለ. የመዳን ፍቺ፡- ለእኔ እንደ ግለሰብ፣ መዳን ማለት፡- እኔ ከክርስቶስ ጋር በመዋሃድ ኃጢአት ካስከተለው ጥፋትና መለያየት ድኛለሁ ስለዚህም እርሱ ቃል የገባውን መንግሥት ከሚወርሱት “የእግዚአብሔር ሕዝብ” ጋር ተቀላቅያለሁ ማለት ነው።
II. መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድነት ማለት በኃጢአት ምክንያት ከመጣው መጥፋት/መለያየት ድነናል ማለት ነው።
ሀ. ኃጢአት የሰውን ልጅ ከእግዚአብሔር ለየ።
1. ዘፍ.3.8
2. ኢሳ. 59.2
3. ቆላ.1.21
/ 2 5
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ለ. በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር መለየቱ የሰው ልጅ ጠፋ ማለት ነው።
የሰው ልጅ ይሆን ይገባው በነበረበት ቦታ ላይ አይገኝም፣ ይልቁንም እንደጠፋ በግ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተቅበዘበዘ። ኢየሱስ በሉቃስ 15 ላይ በኃጢአት ምክንያት የተፈጠረውን የሰው ልጅ ሁኔታ እንደ ፍጹም ጥፋት ገልጾታል። የሰው ልጅ እንዲህ ነው የተባለባቸውን ታሪኮች ይተርካል፡-
1. እንደጠፋ ልጅ
1
2. እንደጠፋ በግ
ሉቃስ 19፡10 የሰው ልጅ የጠፉትን ሊፈልግና ሊያድን መጥቷልና።
3. እንደጠፋ ገንዘብ
ሐ. ከእግዚአብሔር የመለየት ሦስት ውጤቶች ሞት፣ እስራት እና ፍርድ ናቸው።
1. እግዚአብሔር የሕይወት ሁሉ ምንጭ ስለሆነ የአዳምና የሔዋን ታሪክ በግልጽ እንደሚያሳየው ይህ በኃጢአት ምክንያት የተፈጠረው መጥፋት/መለየት የሞት ውጤት ነው።
ሀ. ዘፍ 2፡16-17
ለ. ሉቃ 15፡24
ሐ. ሮሜ. 5፡12፣ ኤፌ. 2.1
2. እግዚአብሔር የነጻነትና የጥበቃ ምንጭ ስለሆነ ከእርሱ መጥፋታችን/መለየታችን የኃጢአትና የዲያብሎስ ባሪያዎች እንድንሆን ያደርገናል።
ሀ. ዮሐንስ 8፡34
2 6 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ለ. ሮሜ. 6፡20-21
ሐ. ቆላ.1.13
3. እግዚአብሔር የመልካምነት ሁሉ ምንጭ ስለሆነ፣ መጥፋታችንና ከእሱ መለየታችን እንዲሁም የኛ መጥፎ ተግባራችን የቅጣትና የፍርድ ተጨማሪ መዘዝ ነው።
ሀ. ሮሜ. 2.5-6 (በተጨማሪም ኤፌ. 2.3 ተመልከት)
1
ለ. ዮሐንስ 3፡36
III. ሰዎች የሚድኑት ከክርስቶስ ጋር አንድ በመሆን እና በእርሱም በኩል ከእግዚአብሔር አብ ጋር አንድ በመሆን ብቻ ነው።
ሀ. ከክርስቶስ ጋር ህብረት
1. 2 ቆሮ. 5.17
2. ዮሃንስ 15፡5
3. ገላ. 2.19 ለ-20
4. ሮሜ. 6.5
/ 2 7
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ለ. ከክርስቶስ ጋር ያለው አንድነት ህጋዊ ገጽታ አለው፡ እግዚአብሔር ቁጣውን እና ፍርዱን በእኛ ምትክ በሞተው በክርስቶስ ላይ አደረገ። ከክርስቶስ ጋር በመተባበር በመስቀል ላይ በሞቱ ተካፋዮች እንሆናለን ስለዚህም እግዚአብሔር ኃጢአታችን እንደተከፈለ ይቆጥረዋል፣ በቸርነቱም ይቅር ይለናል።
1. ኢሳ. 53.5
2. ዕብ. 9.28
1
3. ቆላ.2.13-14
እምነት ከክርስቶስ ጋር ያለ እምነት እና አንድነት ስለሆነ፣ ይህ የጽድቅ ተምሳሌት በምንም መልኩ ማስመሰል የለበትም አይደለም፣ ይልቁንም በእምነት ከክርስቶስ ጋር ባለን አንድነት (በክርስቶስ በእኛ ስለሚኖር) እግዚአብሔር እውነተኛ የሆነውን ይመሰክራል። በእርግጥ እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ያጸድቃል፣ ነገር ግን በክርስቶስ አምነው ከእርሱ ጋር የተባበሩትን ብቻ ነው። ስለዚህ የክርስቶስ ጽድቅ ኃጢአተኛውን ያለብሳል፣ እርሱም ጻድቅ ይሆናል። ነገር ግን ይህ የሚሆነው አንድ ሰው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በእምነት ሲዋሃድ ብቻ ነው። . . .ይህ ማለት ከእንግዲህ ኃጢአተኞች አይደለንም ማለት አይደለም፤ ምክንያቱም በራሳችን በእርግጥም ሃጢአተኞች ነን። ነገር ግን በክርስቶስ እኛ ሙሉ በሙሉ ጻድቃን ነን! ~ J. Rodman Williams. Renewal Theology. Vol. 2. Grand Rapids: Zondervan, 1996. p. 74.
ሐ. ከክርስቶስ ጋር ያለው አንድነት መንፈሳዊ ገጽታ አለው፡ መንፈሳችን ከመንፈሱ ጋር ስለተጣመረ፣ የኢየሱስ ህይወት ውድቀትን እና ሞትን በማሸነፍ በእኛ ውስጥ ይፈስሳል።
1. ሮሜ. 8፡10-11
2. ቆላ.3.3-4
2 8 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
መ. ከክርስቶስ ጋር ያለው ኅብረት ነጻ የማውጣት ገጽታ አለው፡ ሰይጣንን ድል ከነሳው ጋር ስለተባበርን፣ ከእንግዲህ በክፉው መሸነፍ አንችልም። ክርስቶስ ከክፉው ባርነት ነፃ አውጥቶናል።
1. ዮሃንስ 8፡34-36
2. ሉቃ 11፡20-22
1
3. ቆላ.2.15
4. ያዕ 4፡7
IV. መዳን ማለት እርሱ ቃል የገባላቸውን መንግሥት ከሚወርሱት ‘የእግዚአብሔር ሕዝብ’ ጋር ተቀላቅለናል ማለት ነው።
በዚህ ወሳኝ ነጥብ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት “ድነት የእግዚአብሔርን ሕዝብ እንደ መቀላቀል” የሚለውን አባሪ ተመልከት።
ሀ. ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ስለሆነ ከእርሱ ጋር ያለን አንድነት ከእግዚአብሔር ቤተሰብ ጋር ይቀላቅለናል።
1. ኤፌ. 1.5.
2. ዕብ. 2፡11-13
3. ገላ. 4.6
ለ. እግዚአብሔር ለሕዝቡ ቃል ከገባላቸው ነገሮች መካከል፡-
1. የማይናወጥ መንግሥት
/ 2 9
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ሀ. ሉቃ 12፡32
ለ. ዕብ. 12.27
2. ክፋትና ሕመም የሌለበት አዲስ ሰማይና ምድር
ሀ. 2 ጴጥ. 3.13
1
ለ. ራእይ 21.1-5
3. የማይበሰብስ እና ዘላለማዊ አዲስ አካል
ሀ. ሉቃስ 18፡29-30
ለ. 1 ቆሮ. 15፡50-57
4. በአዲሲቷ ኢየሩሳሌም ውስጥ በእግዚአብሔር ፊት የመኖር መብት
ሀ. ራእይ 21፡2-3
ለ. ራእይ 22፡3-4
5. በአዲስ ሥርዓት ከእግዚአብሔር ጋር የመግዛት መብት
ሀ. 2 ጢሞ. 2.12
3 0 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ለ. ራእይ 22.5
6. በዚህ ምድር ህይወት ውስጥ ላለ ለታማኝነት ሽልማት
ሀ. 2 ጢሞ. 4.8
ለ. ያዕቆብ 1፡12
1
ሐ. ራእይ 2.10
7. መግለጫን ወይም ግንዛቤን የሚቃወሙ የማይታሰቡ አዳዲስ ድንቆች
ሀ. 1 ቆሮ. 2.9
ለ. 1ኛ ዮሐንስ 3፡2
ሐ. ጳውሎስም ሆነ ጴጥሮስ ድነትን “የእግዚአብሔር ህዝቦች” አካል እንደመሆን ይገልጹታል።
በመጽሐፍ ቅዱሳዊ መልኩ መዳን ማለት የእግዚአብሔርን መንግስት ለመቀበል የተመረጡት የእግዚአብሔር ህዝቦች አካል በመሆን በእነዚህ ልምዶች መካፈል ነው። አዲሱ ሰማይና አዲሱ ምድር የሚፈጠሩት በተገለሉ ሰዎች ሳይሆን እግዚአብሔር ከምድር በጠራው አዲስ ማኅበረሰብ ነው። እነዚህን በረከቶች ሲወርሱ በእግዚአብሔር ሕዝብ መካከል ቦታውን የማይይዝ ማንኛውም ሰው “የጠፋ” እንደሆነ ይታሰባል።
1. 1 ጴጥ. 2.10
2. ኤፌ. 1.18-23
/ 3 1
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
እግዚአብሔር ግለሰቦችን እያዳነና ለመንግስተ ሰማያት እያዘጋጃቸው ብቻ አይደለም። ይልቁንም እግዚአብሔር የሚያድርባቸው እና በሕይወታቸው አብረው የእግዚአብሔርን ሕይወትና ባሕርይ የሚገልጡትን ሕዝብ ለስሙ እየፈጠረ ነው። ይህ የመዳን አመለካከት በጳውሎስ ዘንድ ጥልቅ አመለካከት ነው። ~ Gordon D. Fee. God’s Empowering Presence. Peabody: Hendrickson, 1994. p. 872.
መ. ድነት ማለት ከእግዚአብሔር ሰዎች ጋር መዋሃድ መሆኑን እንድንረዳ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት ጥለውልናል።
1
1. ከግብፅ መዳን (ዘፀአት)፡-
ምናልባት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሁሉ የተሻለው የድነት ምስል የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ባርነት ነፃ የወጡበት የዘፀአት ታሪክ ነው። በቤተክርስቲያን ታሪክ ከጥንት ጀምሮ የዘፀአት ታሪክ ክርስቲያናዊ የመዳንን ግንዛቤ የሚያብራራ ታሪክ እንደሆነ ይወሰዳል። የዘጸአት ታሪክ ድነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዴት አድርጎ እንደሚስል አስተውል።
ሀ. ያለ ተስፋ በመከራ ውስጥ የሚኖር ባሪያ ሕዝብ (በግብፅ ያሉ እስራኤላውያን)
ለ. እርሱ በላከው (ሙሴ) አማካኝነት በእግዚአብሔር ምርጫ ተጠርተዋል
ሐ. በደሙ (በፋሲካው በግ በኢየሱስ) አማካኝነት ከእግዚአብሔር ቁጣ ይድናሉ
መ. በእግዚአብሔር ታላቅ ኃይል (በፈርዖን እና በሠራዊቱ ሽንፈት) ከክፉ አገዛዝ ነፃ ወጡ
ሠ. በውሃ (ቀይ ባህር) ውስጥ በማለፍ ነጻ ይወጣሉ
ረ. የእግዚአብሔርን ፈቃድ (ሕግ) የሚታዘዙ የተቀደሰ ሕዝብ (እስራኤል) ሆነው ተመስርተዋል
ሰ. ለአሕዛብ ምስክር የመሆን ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል (ዘጸ. 19.5-6)
3 2 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ሸ. በመጨረሻም ወደ ተስፋይቱ ምድር (ከነዓን) ወደ ቅድስቲት ከተማ (ኢየሩሳሌም) ገብተዋል በዚያም በታላቁ ንጉሥ (በዳዊት) ሥር በሰላም ይኖራሉ።
2. ከኃጢአት መዳን፡-
ሀ. ያለ ተስፋ በመከራ ውስጥ የሚኖር ባሪያ ሕዝብ (በኃጢአት ሥር ያለ ሰው ሁሉ)
ለ. እርሱ በላከው (ኢየሱስ) አማካኝነት በእግዚአብሔር ምርጫ ተጠርተዋል
1
ሐ. ደሙን በመቀባት ከእግዚአብሔር ቁጣ ድነዋል (የታረደው የእግዚአብሔር በግ ኢየሱስ)
መ. በእግዚአብሔር ታላቅ ኃይል (በሰይጣንና በአጋንንቱ ሽንፈት) ከክፉ አገዛዝ ነፃ ወጥተዋል
ሠ. የሚድኑት በውሃ ውስጥ በማለፍ ነው (ጥምቀት)
ረ. የእግዚአብሔርን ፈቃድ (የክርስቶስን ትእዛዛት) የሚታዘዝ የተቀደሰ ሕዝብ (ቤተ ክርስቲያን) ሆነው ተመሥርተዋል
ሰ. ለአሕዛብ ምስክር የመሆን ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል (ማቴ. 28.18-20)
ሸ. በመጨረሻ ወደ ተስፋይቱ ምድር (አዲስ ፍጥረት) ወደ ቅድስቲት ከተማ (አዲሲቷ ኢየሩሳሌም) ገብተዋል በዚያም በታላቁ ንጉስ (ኢየሱስ) ስር በሰላም ይኖራሉ።
/ 3 3
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
3. በዘፀአት መዳን ማለት ምን ማለት ነው?
4. በአዲስ ኪዳን መዳን ማለት ምን ማለት ነው?
ሀ. ሮሜ. 8.20-25
ለ. 2 ጴጥ. 3.13
1
ማጠቃለያ
» ድነት ማለት ከክርስቶስ ጋር አንድ በመሆን ኃጢአት ካስከተለው ጥፋትና መለያየት መዳን ማለት ነው ይህም እርሱ ቃል የገባላቸውን መንግሥት ከሚወርሱት ‘የእግዚአብሔር ሕዝብ’ ጋር መቀላቀል ማለት ነው። » ይህ መዳን ሁልጊዜ ኃጢአት ከሚያስከትለው የእግዚአብሔር ፍርድ መዳንን እና ኃጢአት በሰው ሕይወት ውስጥ ከሚያመጣው እስራት ነፃ መውጣትን ያካትታል። » መዳን እና ቤተክርስቲያን በእውነት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው ምክንያቱም መዳን ማለት በትርጉሙ የእግዚአብሔር ህዝብ አካል መሆን ማለት ነው። ግለሰቦች መዳንን ይለማመዳሉ ነገር ግን ማንም በራሱ የዳነ የለም። ከክርስቶስ ጋር አንድ መሆን ሁልጊዜም ከሕዝቡ ጋር አንድ መሆንን ይጨምራል። » ቤተ ክርስቲያን አዲሶቹ የሰው ልጆች በአዲስ ሰማይ እና አዲስ ምድር ውስጥ በእግዚአብሔር አገዛዝ ሥር የሚያመጡት ተጽዕኖ ትልቅ የእግዚአብሔር ታሪክ አካል ነች ይህም በዓለም ላይ የኃጢአትና የሞትን መዘዝ ሙሉ በሙሉ የሚቀይር ነው። » ሰዎች እንዲድኑ ጥሪ ማድረግ በኢየሱስ በማመን እርሱ በሚገዛበት በዚህ አዲስ ዓለም ውስጥ እንዲሳተፉ መጋበዝ ማለት ነው።
3 4 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
የሚከተሉት ጥያቄዎች የተነደፉት በሁለተኛው የቪዲዮ ክፍል ውስጥ የሚገኘውን የመዳንን ትርጉም እንዲከልሱ ለመርዳት ነው። ለጥያቄዎቹ መልስ ስትሰጥ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ “መዳን” ሲናገር ምን ማለት እንደሆነ ግልጽ በሚያደርጉ ሐሳቦች ላይ አተኩር። አስታውስ እነዚህ ጥያቄዎች ኢየሱስ እንዴት ድነትን እንዳከናወነ ወይም ሰዎች እንዴት እንደዳኑ ለመግለጽ እየሞከሩ እንዳልሆነ (እነዚህ ሃሳቦች በሌሎች የካፕስቶን ሞጁሎች ውስጥ ይብራራሉ) ይልቁንም መዳን ምን እንደሆነ ግልጽ እንዲሆንልን ይረዱናል። መልሶችህ ግልጽ እና አጭር ይሁኑ፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ በቅዱሳት መጻሕፍት አስደግፍ! 1. የሰው ልጆች መዳን ያለባቸው ሦስቱ የኃጢአት ውጤቶች ምንድን ናቸው? 2. በሉቃስ 15 ላይ ኢየሱስ ስለጠፉ ነገሮች የተናገራቸው ምሳሌዎች ስለ ድነት ምን ያስተምሩናል? 3. የመዳን ቁልፉ ‘ከክርስቶስ ጋር ኅብረት’ የሆነው ለምንድን ነው? 4. መዳን ሁል ጊዜ በቤተክርስቲያን ውስጥ መካተትን እንደሚጨምር መረዳት ለምን አስፈለገ? 5. ለምንድነው አንድ ክርስቲያን አማኝ “ድኛለሁ” እና “እድናለሁ” የሚለው እናስ እንዴት ነው ሁለቱም አባባሎች እኩል እውነት መሆናቸውን የሚያውቀው? ይህ ትምህርት የሚያተኩረው እግዚአብሔር ለዘላለም የእርሱ የሆኑትን ሕዝቦች ከምድር ላይ ለመቤዠት ባዘጋጀው ሉዓላዊ ንድፍ ላይ ነው። ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር ለአብርሃም በገባው ቃል ኪዳን፣ አሁን ስለ አሕዛብ በተገለጠው ምሥጢር፣ እና በእስራኤል ሕዝብ ምሳሌ ትታያለች። እግዚአብሔር ህዝቡን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ከራሱ ጋር አንድ አድርጎ ለራሱ ክብር ሲል አዳነ። በግል መዳን ማለት በእምነት ከክርስቶስ ጋር እና በእርሱም ከተዋጀው ማህበረሰቡ ጋር አንድ መሆን ማለት ነው። ³ የእግዚአብሔር ከፍ ያለው ዓላማ፣ የመጨረሻ ሐሳቡ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት አማካኝነት በፍጥረቱ እና በሕዝቡ በኩል ለራሱ ክብር እና ሞገስን ማምጣት ነው። ሁሉ በእርሱ ፈቃድና ለክብሩ ሆነዋል። ³ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በእግዚአብሔር የላቀ ዓላማ ውስጥ ተጠልላለች። እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ ለራሱ ክብርን ለማምጣት ከአህዛብ መካከል ለዘላለም የእርሱ የሆኑትን ሕዝቦች በመቤዠት ወስኗል። ይህንንም ከአብርሃም ጋር በገባው ቃል ኪዳን ፈጽሟል። ³ ቤተክርስቲያን አህዛብ በክርስቶስ ኢየሱስ በሚካተቱበት ታላቁ ምስጢር መገለጥ ጥላ ውስጥ ነበረች። እግዚአብሔር በልጁ በማመን አሕዛብን ለማዳን በእርሱ ቤተሰብ ውስጥ ለዘላለም እንዲካተቱ በሐዋርያት እና በነቢያት በኩል ለዚህ ትውልድ እና ለአለቆችና ለሥልጣናት አሳውቋል።
መሸጋገሪያ 2
የተማሪው ጥያቄዎች እና ምላሾች
1
ግንኙነት
የቁልፍ ፅንሰ ሀሳቦች ማጠቃለያ
/ 3 5
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
³ ቤተ ክርስቲያን በእግዚአብሔር ሕዝብ ምስል ጥላ ስር: ላኦስ ውስጥ ነበረች። በእስራኤል ሕዝብ በኩል እግዚአብሔር ሊመጣ ያለውን አንድ አዲስ የሰው ዘር ምልክት ሰጠን፣ እርሱም አሕዛብንና አይሁዳውያንን ያካትታል። ³ ምንም እንኳን እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያን የተለየ ቦታ ቢሰጣትም እስራኤልንም ጨርሶ አልተዋትም፣ ጥሪዋንና መመረጧንም ፈጽሞ አልሻረውም። በሮሜ 9-11 እንደተጠቀሰው እግዚአብሔር የአሕዛብን ድነት በሙላት ካመጣ በኋላ የእስራኤልን ቅሬታዎች ደግሞ ያድናቸዋል። ³ መዳን፣ ሶቴሪያ፣ ማለት አንድን ሰው መታደግ፣ ነጻ ማውጣት ወይም ደህንነቱ የተጠበቀ ማድረግ ማለት ነው። ³ ኃጢአት ከእግዚአብሔር የሚለየን ከመሆኑም በላይ እንድንጠፋ ያደርገናል፤ ይህም የእግዚአብሔርን ፍቅር፣ ጥበቃና እውነት እንዳናጣጥም ‘ያደርገናል። ³ ከእግዚአብሔር ‘መለየት’ የሚያስከትላቸው ውጤቶች፡- ሥጋዊና መንፈሳዊ ሞት፣ የኃጢአት እስራትና ፍርድ/ቅጣት ናቸው። ³ ከክርስቶስ ጋር ህብረት (በህይወቱ፣ በሞቱ እና በትንሳኤው በማመን) እግዚአብሔር እኛን ከራሱ ጋር ወደ ቀድሞው ህብረት የሚመልስበት መንገድ ነው። ³ ከክርስቶስ ጋር ኅብረት በኃጢአት ምክንያት የሚመጡትን ሦስት ችግሮች ሽሯል። ክርስቶስ ቅጣታችንን እና ፍርዳችንን በመስቀል ላይ ስለተሸከመ የክርስቶስ ሞት የእግዚአብሔርን ህግ በመጣሳችን የነበረብንን የህግ ዕዳ ከፍሎልናል። ክርስቶስ በሰይጣን ላይ የተጎናጸፈው ድል ከኃጢአት ባርነት ነፃ አውጥቶናል። ክርስቶስ በሞት ላይ የተጎናጸፈው ድል ደግሞ ከህይወቱ ጋር ስለተባበርን የዘላለምን ህይወት ዋስትና ይሰጠናል። ³ አንድ ሰው ከክርስቶስ ጋር ህብረት በማድረግ በአዲሱ መንግሥት ውስጥ ሕይወትን ከሚለማመዱ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ጋር ይካተታል። የክርስቲያን ማንነት የተመሰረተው እርሱ ወይም እርሷ አሁን የተመረጠው የእግዚአብሔር ህዝብ በሆነው የቤተክርስቲያን አካል በመሆናቸው ነው። በታሪክ እና በቅዱሳት መጻህፍት ጥላ ስለነበረችው ቤተክርስቲያን የዚህን ትምህርት ፅንሰ-ሃሳብ በተመለከተ ከተማሪዎችህ ጋር የምትወያይበት ጊዜ አሁን ነው። የቤተክርስቲያንን ፅንሰ-ሃሳብ ጥልቀት ለማድነቅ፣ እግዚአብሔር ለስሙ አህዛብን ከምድር ለመጥራት ያለው ፍላጎት ጥንታዊ እና ጥልቅ መሆኑን መረዳት አስፈላጊ ነው። ለእናንተ፣ እንደ ተማሪዎች፣ ከእግዚአብሔር የአጽናፈ አለሙ ታላቅ እቅድ ጋር መጋፈጥ የዚህ ክፍል አላማ ነው። አሁን ካጠናኸው ጽሑፍ አንጻር ምን ልዩ ጥያቄዎች አሉህ? ምናልባት ከዚህ በታች ያሉት አንዳንድ ጥያቄዎች የራስህን ግልጽ እና ወሳኝ ጥያቄዎችን እንድትፈጥር ሊረዱህ ይችላሉ።
1
የተማሪው ትግበራ እና አንድምታ
3 6 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
* አንድ የቤተ ክርስቲያን መሪ ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር ሕዝቦች መካከል ራሱን ለማክበር በእግዚአብሔር የላቀ ዓላማ ጥላ ስር እንደምትገኝ መረዳቱ እና ማስረዳት መቻሉ ለምን ጠቃሚ ይሆናል? አንተ ያለህበት አጥቢያ ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ለዘላለም የሚኖርን አዲስ የሰው ዘር ለመፍጠር ካለው ፍላጎት ጋር ያለው ዝምድና ምንድን ነው? * እግዚአብሔር ዓለምን ሁሉ ለመቤዠት ባለው ዓላማ ውስጥ አሕዛብን ለማካትት ስላለው ሐሳብ አንዳንድ ተግባራዊ አንድምታዎች ምንድን ናቸው? እግዚአብሔር በአካባቢህ ያሉ አጥቢያ አብያተክርስቲያናት ግልጽ እና ከጭፍን ጥላቻና ከአድልዎ ነፃ እንዲሆኑ ስላለው ዓላማ ምን ይላል? * በክርስቶስ የሚያምኑት ሁሉ ሕዝቡ ከሆኑ፣ ከሁሉም ታናሽ የሆነችውንና ኢየሱስ የሚመለክባትና የሚከበርባትን ትንሿን የአማኞች ስብስብ የሆነችውን ቤተክርስቲያን እንኳን እንዴት ልንመለከት ይገባናል? ትናንሽ የሆኑት የከተማ አብያተ ክርስቲያናት እግዚአብሔር የራሱ የተለየ ሕዝብ አድርጎ ለራሱ እንደሚያስነሣው ቃል የገባለትን ሕዝብ (ላኦስ) አካል ነን ብለው እንዴት ሊናገሩ ይችላሉ? * በእግዚአብሔር ሕዝቦች መካከል ያሉ አንዳንድ ቡድኖች ከሌሎቹ የበለጠ ክብደትና ክብር የተሸከሙ የሚመስሉት ለምንድን ነው? በክርስቲያን ቡድኖች መካከል ያለው ይህ የተለመደ ዝንባሌ እግዚአብሔር ከምድር አህዛብ ሁሉ ለራሱ የሚሆንን ሕዝብ ለማውጣት እየሠራ ያለውን ሐሳብ የሚቃረነው እንዴት ነው? * በአንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለ መሪ እግዚአብሔር ለብዙ ዘመናት ሕዝቡን በአንድነት ለመሰብሰብ ሲሠራ እንደነበረ መገንዘቡ አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድነው? ጠላት ለአንድ ተስፋ ለቆረጠመሪ ቤተክርስቲያንን ለመገንባት የሚያደርገው ጥረት መቼም እንደማይሳካለት ምን አይነት ውሸት ሊነግረው ይችላል? * ለአንድ የከተማ አገልጋይ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሥነ ምግባር ጥሰት፣ ከጣዖት አምልኮ እና ከኃጢአት ጋር ለተያያዙት ለአህዛብም ቢሆን ቤተክርስቲያንን ለሁሉም ሰው ማድረግ የእግዚአብሔር ጥልቅ ፍላጎት መሆኑን መረዳቱ ለምን አስፈላጊ ሊሆን ይችላል? ይህ ዛሬም ለዚህ ማህረሰብ ውጭ ስላሉት ሰዎች ምን ሊጠቁም ይችላል? * ለአንድ የተሰጠ ክርስቲያን ሠራተኛ እግዚአብሔር ሕዝቡን በአንድ ላይ የማሰባሰብ ዓላማ እንዳለው ማረጋገጥ ለምን አስፈላጊ ይሆናል? ለክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ለማድረግ ከዚህ ያነሰ መሥራት አለብን ማለት ነው?
1
/ 3 7
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ጥናቶች
“እስራኤል ከአሁን በኋላ የእግዚአብሔር ሕዝብ አይደለም” በቅርብ ጊዜ በርካታ ሰዎች በሚካፈሉበት የአዋቂዎች የሰንበት ትምህርት ቤት በርካታ አባላት እስራኤል በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ ስላላት ስፍራ ሞቅ ያለ ውይይት አድርገዋል። አንዳንዶች አይሁዳውያን በኢየሱስ ሞት ውስጥ እጃቸው ስላለበት እግዚአብሔር እንደ ሕዝቡ አድርጎ አይቀበላቸውም ብለው ይከራከሩ ነበር። ሌሎች ደግሞ እግዚአብሔር እስራኤልን እንደ ሕዝቡ አልተወም ነገር ግን በክርስቶስ ስላላመኑ ቀድሞ በእግዚአብሔር ፊት የነበራቸው አይነት ሞገስ እንደሌላቸው ይናገራሉ። ሌላው ቡድን ደግሞ ኢየሱስ በዳግም ምጽአት እስከሚመለስበት ወቅት ድረስ እስራኤላውያን የእግዚአብሔር ሕዝብ ሆነው እንደሚቀጥሉ ያምናሉ። አንድ ሌላ ቡድን ደግሞ ስለ እስራኤል ብዙ መጨነቅ እንደሌለብን በመግለጽ ጥያቄው እንኳን ያን ያህል አስፈላጊ እንዳልሆነ ያምናል፣ ዋናው ጉዳይ መሆን ያለበት ራሱ ክርስቶስ እና በእርሱ በማመን ስለሙገኘው ድነት ነው ብለው ያምናሉ። ይህ መምህር ለእርዳታ ወደ አንተ ቢመጣ ምን ትመክረዋለህ? “ቤተ ክርስቲያን ማን ያስፈልገዋል?” አንድ ጓደኛህ እግዚአብሔርን የሚወድ፣ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነብ እና በመልካም ሥራ ሕይወት ለመኖር የሚጥር የተሰጠ ክርስቲያን ነኝ ብሎ ያምናል። ነገር ግን ይህ ግለሰብ ወደ ቤተ ክርስቲያን አይሄድም ወይም እራሱን በክርስቶስ አካል ውስጥ አያሳትፍም። ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲመጣ በጋበዝከው ጊዜ ሁሉ “ክርስቲያን ለመሆን የቤተክርስቲያን አባል መሆን ግድ ነው ብዬ አላምንም፣ እንዳውም እኔ በቤተክርስቲያን ሕንፃ ውስጥ ከማደርገው አምልኮ በተሻለ በውጭ በተፈጥሮ እግዚአብሔርን ማምለክ እመርጣለሁ” ይላል። ይህ ሰው ስለ ክርስትና ስላለው አመለካከት ምን ትላለህ? መላውን መጽሐፍ ቅዱስ መስበክ የዚህ ትምህርት ርዕስ “በእግዚአብሔር ጥላ ውስጥ ያለች ቤተ ክርስቲያን” የሚለው ሃሳብ በብሉይ ኪዳኑ የእግዚአብሔር ሕዝብና በቤተ ክርስቲያን መካከል ግንኙነት እንዳለ ይጠቁማል፣ ሐዋርያው ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 10፡1-11 የዳሰሰው ሐሳብ - “ወንድሞች ሆይ፥ ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ። አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች ነበሩ ሁሉም በባሕር መካከል ተሻገሩ፤ ሁሉም ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ በደመናና በባሕር ተጠመቁ፤ ሁሉም ያን መንፈሳዊ መብል በሉ ሁሉም ያን መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ዓለት ጠጥተዋልና፥ ያም ዓለት ክርስቶስ ነበረ። እግዚአብሔር ግን ከእነርሱ በሚበዙት ደስ አላለውም፥ በምድረ በዳ ወድቀዋልና። እነዚህም ክፉ ነገር እንደ ተመኙ እኛ ደግሞ እንዳንመኝ ይህ ምሳሌ ሆነልን። ሕዝብም ሊበሉ ሊጠጡም ተቀመጡ ሊዘፍኑም ተነሡ ተብሎ እንደ ተጻፈ ከእነርሱ አንዳንዶቹ እንዳደረጉት ጣዖትን የምታመልኩ አትሁኑ። ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንደ ሴሰኑ በአንድ ቀንም ሁለት እልፍ ከሦስት ሺህ እንደ ወደቁ አንሴስን። ከእነርሱም አንዳንዶቹ ጌታን እንደ ተፈታተኑት በእባቦቹም እንደ ጠፉ ጌታን አንፈታተን። ከእነርሱም አንዳንዶቹ
1
1
2
3
3 8 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
እንዳንጎራጎሩ በሚያጠፋውም እንደ ጠፉ አታንጐርጕሩ። ይህም ሁሉ እንደ ምሳሌ ሆነባቸው፥ እኛንም የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን ሊገሥጸን ተጻፈ።” አንድ ወጣት ሰባኪ አብዛኞቹ ስብከቶቹ የወጡት ከአዲስ ኪዳን ቅዱሳት መጻሕፍት ነው ብለን እናስብ። “በብሉይ ኪዳን የተጠቀሱት ጦርነቶች፣ ትእዛዛትና ታሪኮች ከቤተ ክርስቲያኔ ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ አላውቅም” ሲል አምኗል። የብሉይ ኪዳኑ የእግዚአብሔር ሕዝብ (እስራኤል) ታሪክ እግዚአብሔር በአዲስ ኪዳን ህዝቡ (ቤተክርስቲያን) እየሰራ ያለውን ስራ ለመገንዘብ እንደ መሰረት ሆኖ እንደሚያገለግል እንዲረዳ እንዴት ልትረዳው ትችላለህ? ቤተክርስቲያንን እንደ “እግዚአብሔር ሕዝብ” መገንዘብ ይህን ትስስር ለመፍጠር እንዴት ይረዳናል? “የእኛ ቤተ ክርስቲያን ትክክለኛዋ ቤተ ክርስቲያን ናት” አንድ የወጣት ቡድን አባላት እምነታቸውን ለጎረቤቶቻቸው ሲያካፍሉ ሁሉም አማኝ የሆኑበት ቤት አጋጥሟቸዋል ነገር ግን እነዚህ ሰዎች የሚሄዱበት ቤተክርስቲያን ምርጡ እንደሆነ አያምኑም። “እናንተ በአህዛብ የተጀመሩ ብዙ ልምምዶችን ታደርጋላችሁ - ገና፣ ፋሲካ፣ በተለይም ቤተ ክርስቲያናችሁ የምትፈቅደው ሙዚቃ፣ ፊልም፣ ጭፈራ፣ እና ሌሎች ከቅድስና የወረዱ እንደሆናችሁ የሚያሳዩ በርካታ ነገሮች አሉ!” ይህን ሲሰሙ አንዳንዶቹ ወጣቶች በጣም ተስፋ ቆረጡ፤ እንዲያውም አንዳንዶቹ ክርስቲያኖች እንዳልሆኑ ማሰብ ጀመሩ። ይህ ወጣት አገልጋይ ወጣቶቹ ያገኟቸውን አማኞች የሚቃወም ሳይመስል፣ የእግዚአብሔርን ጸጋ ምንነት እና ከክርስቶስ ጋር አንድ መሆንን ለተማሪዎቹ ማስተማር ይፈልጋል። የማን ቤተ ክርስቲያንና ጉባኤ የተሻለ እንደሆነ ስለሚያነሳው ይህ ችግር ምን ማለት ይገባዋል? ክርስቲያናዊ ድነት ማለት ከክርስቶስ ጋር አንድ በመሆን ኃጢአት ካስከተለው ጥፋትና መለያየት መዳን ማለት ነው ይህም እርሱ ቃል የገባላቸውን መንግሥት ከሚወርሱት ‘የእግዚአብሔር ሕዝብ’ ጋር መቀላቀል ማለት ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር የላቀውን አላማውን በሚፈጽምበት ጊዜ ጥላ ትሆናለች፣ ማለትም እግዚአብሔር ከዘመናት በፊት ከአብርሃም ጋር በገባው ቃል ኪዳን አማካኝነት በአዲስ የሰው ዘር በኩል ለራሱ ክብርን ለማምጣት ወሰኗል። ይህ ሃሳብ ለጸጋው የድኅነት እቅዱ መገለጥ ጉልህ ክፍል ነው፣ ይህም አሕዛብን በክርስቶስ ኢየሱስ የሚካተቱበት ታላቁ ምስጢር ነው። በእስራኤል ሕዝብ ውስጥ፣ ዛሬ እግዚአብሔርን እና መንግሥቱን እንደሚወክል እግዚአብሔር ልዩ እና ልዩ የሆኑትን የእግዚአብሔርን ላኦስ፣ ቤተ ክርስቲያን ሥዕል ሰጥቶናል። በእግዚአብሔር እቅድ ጥላ ውስጥ ያለችው ቤተክርስቲያን ስለሚለው ትምህርት ተጨማሪ ሀሳቦችን ለመከታተል ፍላጎት ካለህ እነዚህን መጻሕፍት መመልከት ይረዳህ ይሆናል: Chapter 6 in Fee, Gordon D. Paul, the Spirit, and the People of God . Peabody, MA: Hendrickson Publishers, 1996.
1
4
የትምህርቱን ንድፈ ሃሳብ በድጋሚ መጻፍ
ማጣቀሻዎች
/ 3 9
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
Snyder, Howard A. Kingdom, Church, and World: Biblical Themes for Today . Eugene, OR: Wipf and Stock Publishers, 2001. -----. The Problem of Wineskins: Church Structure in a Technological Age . Downers Grove: InterVarsity, 1975. Wallis, Jim. Agenda for Biblical People . New York: Harper and Row, 1976. ይህንን ከፍተኛ ሥነ-መለኮት በእውነተኛ የተግባር አገልግሎት ግንኙነት ለመመስከር የምትሞክርበት ጊዜ አሁን ነው፣ እሱም በዚህ በሚቀጥለው ሳምንት ስለምታስብበት እና ልትጸልይለት ትችላለህ። እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር በገባው ቃል ኪዳን የአህዛብ የመዳን ተካፋይነት ምሥጢር መገለጥ ስለተገለጠችው ስለ ቤተ ክርስቲያን ሐሳብ፣ መንፈስ ቅዱስ ምን ይጠቁማል? በኢየሱስ እና በክርስቶስ አካል ላይ ባለው የግል እምነት መካከል ስላለው ግንኙነት ስታስብ ወደ አእምሮህ የሚመጣው ልዩ ሁኔታ ምንድን ነው? ከክርስቶስ ጋር አንድ መሆን ከሕዝቡ ጋር አንድ መሆን ማለት ነው የሚለውን ትምህርት በግልህ ተግባራዊ ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው? ይህን እውነት ለመጀመሪያ ጊዜ መስማት የሚያስፈልጋቸው ወይም አሁን የበለጠ ማብራሪያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ግለሰቦች አሉ? በህይወትህ እና በአገልግሎትህ ግላዊ ሁኔታ ላይ ለማሰላሰል ጊዜ ስጥ፣ እና ለእነዚህ እውነቶች እና መርሆዎች ትግበራህ ተገቢ የሆኑትን ግለሰቦች ወይም ሁኔታዎች እንዲያስታውስ መንፈስ ቅዱስን ጠይቅ። በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ የቤተክርስቲያንን ቦታ እና አስፈላጊነት ሙሉ በሙሉ ለማድነቅ የመንፈስ ቅዱስ ትምህርት እና አመራር ያስፈልገናል። ጳውሎስ በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ የአሕዛብ ምሥጢር መገለጥ የመጣው በእግዚአብሔር ትምህርት በነቢያትና በሐዋርያት በኩል እንደሆነ ተናግሯል (ሮሜ. 16.25-27፤ ኤፌ. 3.3 ዘፍ.)። የእግዚአብሔር ሰዎች ለክርስቶስ ምን ያህል ውድ እንደሆኑ እና ራሳችንን ለማገልገል እና የእግዚአብሔርን ህዝብ ለማነጽ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ በበቂ ሁኔታ ሊያሳየን የሚችለው የእግዚአብሔር መንፈስ ብቻ ነው። ስለ ቤተክርስቲያን ዝቅተኛ ወይም የማይገባ ሃሳቦችን አስተናግደህ ከነበረ እግዚአብሔር በመንግሥቱ ስራ ውስጥ ስለ ቤተክርስቲያን ሚና አዲስ ግንዛቤ እንዲሰጥህ ወደ እርሱ ጸልይ፣ ህዝቡንም በማገልገል እርሱን ስታገለግል ዘንድ አዲስ ጉልበት፣ ጥበብ እና ሃብት እንዲሰጥህ ጠይቀው።
የአገልግሎት ግንኙነቶች
1
ምክር እና ጸሎት
4 0 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ምደባዎች
1ኛ ጴጥሮስ 2፡9-10
የቃል ጥናት ትውስታ
ለክፍል ለመዘጋጀትና የሚቀጥለውን ሳምንት የምንባብ ምደባ ለማግኘት www.tumi.org/books ን ጎብኝ ወይም መምህርህን ጠይቅ።
የንባብ የቤት ስራ
የቀጣዩን ትምህርት ስራህን የምትጀምረው አሁን ነው ስለዚህ ስራህን አታዘግይ ወይም በመጨረሻው ሰዓት ለመስራት አትጣደፍ። በሚቀጥለው ሳምንት የምንመለከታቸዉን ፅንሰ-ሀሳቦች ከወዲሁ ለመቃረም እንዲረዳህ ለንባብህ በቂ ጊዜ ስጥ። በተጨማሪም በሚገባ በመሸምደድ ለመጪው ፈተና ያዘጋጁህ ዘንድ የዚህን ሳምንት ትምህርቶች በጥንቃቄ ገምግም። ቀጣዩ ፈተና የሚያተኩረው በዚህ ትምህርት በተሸፈነው የቪዲዮ ይዘት ላይ ነው ስለሆነ ማስታወሻህን ለመመልከት በቂ ጊዜ ማጥፋትህን እርግጠኛ ሁን፣ በተለይም በትምህርቱ ዋና ዋና ሃሳቦች ላይ አተኩር። እባክህን የተመደበውን ንባብ አንብበህ እያንዳንዱን ንባብ ከአንድ ወይም ከሁለት ሁለት አንቀጽ በማይበልጥ አጠቃልል። ማጠቃለያህን አጭር እና ቀላል አድርገው፣ እባክህ በእያንዳንዱ ንባብ ውስጥ ዋናው ነጥብ ነው ብለህ ስለምታስበው ሃሳብ ያለህን ግንዛቤ ግለጽ። ዝርዝር መግለጫ ለመስጠት ከልክ በላይ አትጨነቅ፤ ከዚህ ይልቅ በመጽሐፉ ክፍል ውስጥ የተብራራውን ዋና ሃሳብ ጻፍ። እባክህ በሚቀጥለው ሳምንት እነዚህን ማጠቃለያዎች ወደ ክፍል አምጣቸው። (እባክህ በዚህ ትምህርት መጨረሻ ላይ ያለውን “የንባብ ማጠናቀቂያ ቅጽ” የሚለውን ተመልከት።) በዚህ ትምህርት ውስጥ በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ከእርሱ ጋር ለዘላለም የሚኖሩትን የራሱን ህዝብ ከምድር ወደ ራሱ ለመጥራት ስላለው የእግዚአብሔር ዘላለማዊ እቅድ ተነጋግረናል። በሚቀጥለው ትምህርት ደግሞ ኃጢአተኞች የተመረጡት ህዝብ አካል እንዲሆኑ ስለሚያስችለው የእግዚአብሔር ጸጋ እና ጸጋው በአምልኮና በምስጋና ምላሽ እንድንሰጥ እንደሚያደርገን እንነጋገራለን። የሚቀጥለው ትምህርት “በአምልኮ ላይ ያለች ቤተክርስቲያን” የሚሰኝ ሲሆን ቤተክርስቲያን ከምትኖርባቸው ምክንያቶች አንዱና ዋነኛው ለእግዚአብሔር የሚገባውን ክብር ለመስጠት እንደሆነ ያስታውሰናል!
ሌሎች የቤት ስራዎች
1
የሚቀጥለውን ትምህርት በጉጉት እንጠባበቃለን።
ይህ ሥርዓተ-ትምህርት የThe Urban Ministry Institute (TUMI) የሺዎች ሰዓታት የሥራ ውጤት በመሆኑ ያለ ፈቃድ ማባዛት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ TUMI እነዚህን መማሪያዎች ለእግዚአብሔር መንግሥት እድገት ለመጠቀም ለሚፈልጉ ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል፤ በተጨማሪም ለማባዛት በተመጣጣኝ ዋጋ ፈቃድ ይሰጣል፡፡ እባክህ ይህ መጽሐፍ በትክክል ፈቃድ ያገኘ መሆኑን ከመምህርህ ጋር በመሆን አረጋግጥ፡፡ በ TUMI እና በፈቃድ አሰጣጥ ፕሮግራማችን ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት Www.site.org እና Www.tumi.org/license ን ጎብኝ፡፡
ስም _________________________________________
ሞጁል 3: የቤተ ክርስቲያን ሥነ-መለኮት ንባብ ማጠናቀቂያ ገፅ
ቀን _________________________________________
ለእያንዳንዱ ለተመደበው ንባብ የጸሃፊውን ዋና ነጥብ አጭር ማጠቃለያ (አንድ ወይም ሁለት አንቀጽ) ጻፍ ፡፡ (ለተጨማሪ ንባብ ፣ የዚህን ገጽ ጀርባ ተጠቀም ፡፡)
ንባብ 1
ርዕሱ እና ጸሐፊው: ______________________________________________ ገጾች _____________
ንባብ 2
ርዕሱ እና ጸሐፊው: ______________________________________________ ገጾች ______________
/ 4 3
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
በአምልኮ ላይ ያለች ቤተ ክርስቲያን
ት ም ህ ር ት 2
የትምህርቱ ዓላማዎች
ሃያል በሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን ! የዚህን ትምህርት መጽሐፍ ካነበብክ፥ ካጠናህ፥ ውይይት ካካሄድክና ወደ ተግባር ከቀየርከው በኋላ የሚከተሉትን ማድረግ ትችላለህ:- • መዳን የሚገኘው በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ ነው የሚለውን ሀሳብ እና የሰው ልጅ በምንም መንገድ ሊያገኘው ወይም ሊገባው አይችልም ለሚለው ሃሳብ ትሟገታለህ። • አምልኮ ለእግዚአብሔር ፀጋ ትክክለኛ ምላሽ መሆኑን ትገነዘባለህ። • “ምስጢረ ቁርባን” እና “ሥርዓት” በሚሉት ቃላት መካከል ያለውን ልዩነት ማብራራት እና ከእያንዳንዱ ቃል በስተጀርባ ያለውን ሥነ-መለኮታዊ አመለካከት መግለጽ ትችላለህ። • የጥምቀትን እና የጌታን እራትን ትርጉም ትረዳለህ፣ ደግሞም ክርስቲያኖች ስለነዚህ ትርጉም በሚያስቡበት መንገድ ላይ ያሉትን ቁልፍ ልዩነቶች ማብራራት ትችላለህ። • እግዚአብሔርን መሳይ ከማይገኝለት ቅድስናው፣ ወሰን ከሌለው ውበቱ፣ ወደር ከሌለው ክብሩ እና አቻ ከማይገኝለት ስራው የተነሳ እግዚአብሔርን ማክበር የቤተክርስቲያን የአምልኮ ዋነኛ አላማ እንደሆነ ታሰላስላለህ። • ቤተክርስቲያን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል አምላከ ሥላሴን እንደምታመልክ መግለጽ ትችላለህ። በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካኝነት በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ያህዌ አምላክን ብቻ እናመልካለን። • ቤተክርስቲያን በምስጋና እና በውዳሴ እና ቃሉንና ምስጢራትን በሚያጎላ በስርዓተ ቅዳሴ፣ እንዲሁም እንደ ቃል ኪዳን ማህበረሰብ በመታዘዝ እና በአኗኗር ዘይቤዋ እንዴት እንደምታመልክ መረዳት እና መተግበር ትችላለህ። የምስጋና መስዋዕትን እናመጣለን። ሮሜ 12፡1-2፣ ዕብራውያን 13፡15 እና ዕንባቆም 3፡17-19 አንብብ። ከብሉይ ኪዳን የአምልኮ ሥርዓት ጋር ከተያያዙት በጣም የተለመዱ ሃሳቦች አንዱ የመስዋዕት ሃሳብ ነው። በቤተ መቅደሱ ውስጥ ካለው አገልግሎት ጋር በተገናኘ በጋራ በሚከወን ሕዝባዊ አምልኮ ወቅት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡ ሁሉ፣ በመደበኛው የአምልኮ ጊዜም ሆነ ወይም እንደ ቤተ መቅደሱ ምርቃት ባሉ አስፈላጊ ዝግጅቶች ወቅት በማንኛውም ሁኔታ መስዋዕቶችን ያቀርቡ ነበር። በእንዲህ አይነት ጊዜ፣ አምላኪዎቹ በቤቱ ምሥረታ ላይ እግዚአብሔር ስላደረገው ታላቅ ቸርነት ምስጋናቸውን ለማቅረብ የእንስሳትን ደም ያፈስሳሉ (2ዜና. 7.5)። በጣም የሚያስደንቀው ነገር፣ ማንም ሰው ስለ እርሱ ሲባል የሚሠዋውን
2
ጥሞና
4 4 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ነገር ሳያቀርብ ወደ እግዚአብሔር ፊት መምጣት አለመቻሉ ነው። እግዚአብሔር የእኛን ምርጡን፣ የላቀውንና በጣም ውዱ መስዋዕታችን ይገባዋል፣ ይልቁንም ከስጦታዎቻችንና ከነገሮቻችን በላይ እኛ ራሳችን ሁለንተናችን ይገባዋል። እጅግ ደስ በሚያሰኙና ነገሮች መልካም በሚሆኑባቸው በእነዚያ ጊዜያት ብቻ ሳይሆን ከባድ መከራና ፈተና በሚደርስብንም ጊዜ እንኳ ለእርሱ የላቀ ምስጋናችንን ልናቀርብለት ይገባል። አምላካችን የማይለወጥ አምላክ ነው፣ በሕይወታችንና በአገልግሎታችን ውስጥ ደስ የማያሰኙ ነገሮች እየተከናወኑ ቢሆንም እንኳ እርሱ ሊመለክ ይገባዋል። ከፍጡራን ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያለው እርሱ ጌታ እግዚአብሔር ነው፣ በላቀ ትኩረትና ኃይላችን፣ በምርጥ መዝሙሮቻችን፣ በሕያው ሽብሸባችን፣ በታላቁ አገልግሎታችንና በሁለንተናዊ ምላሻን አምልኳችን ይገባዋል። በአምልኮ ላይ ያለች ቤተክርስቲያን ደግሞ ዘወትር ለእርሱ ለቅድስናው የሚስማማና ለክብሩ የሚመጥንን መስዋዕት ታቀርባለች። በእርግጥ እርሱ በእውነት ሊመለክና ምስጋናችንን ሊቀበል ይገባዋል። ዕንባ. 3፡17-19 ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥ [18] እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። [19] ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል። ነቢዩ ዕንባቆም ለእግዚአብሔር የምስጋናን መስዋዕት ከማቅረብ አንጻር መንገዱን ያሳየናል፡-
2
ስለዚህ የዕብራውያን ጸሐፊ የተናገረውን ቃል እንከተል፡-
ዕብ. 13፡15፡ 15 እንግዲህ ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት፥ ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ፥ በእርሱ እናቅርብለት።
የኒቂያን የእምነት መግለጫ (በአባሪው ውስጥ ይገኛል) ካነበብክ እና/ወይም ከዘመርክ በኋላ የሚከተለውን ጸሎት ጸልይ፥ የዘላለም አምላክ አባታችን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ሆይ፡ አንተ ብቻ ምስጋና ይገባሃል ስለዚህ ክብርና ውዳሴ፣ ምስጋናም እንድናቀርብልህ ትጠብቅብናለህ። በፍጹም ልባችን በደስታ የሆነን አምልኮ በሁሉም ስብሰባዎቻችን፣ በሁሉም ግንኙነቶቻችን እናቀርብልህ ዘንድ የመንፈስን ኃይል እንድትሰጠን በተወደደ ልጅህ በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጠይቃለን። በሁሉም ተግባሮቻችን እና በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውስጥ የምንናገረውንና የምናደርገው ሁሉ እንደ ጌታ አምላካችን ለምስጋናና ለክብር የተሠዋ መስዋዕት አድርገህ ትቀበለው ዘንድ በኢየሱስ ስም እንጸልያለን አሜን።
የኒቅያ የእምነት መግለጫ እና ጸሎት
Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online