Theology of the Church, Amharic Student Workbook
1 0 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
የኤክሴጄሲስ ፕሮጀክት በካፕስቶን ፋውንዴሽን የቤተየክርስቲያን ስነ መለኮት የጥናት ሞጁል ተሳታፊ እንደመሆንህ መጠን ከሚከተሉት ንባቦች በአንዱ ላይ የክርስቲያን ሚሽን እና የከተማ አገልግሎት ምንነት ላይ ኤክሴጄሲስ (ኢንደክቲቭ ጥናት) እንድትሰራ ትጠየቃለህ። ሮሜ 12:3-8 ገላትያ 3:22-29 1 ቆሮንቶስ 12.1-27 ኤፌሶን 2.11-22 ኤፌሶን 4.1-16 1 ጴጥሮስ 2:9-10 የዚህ ፕሮጀክት አላማ ስለ ቤተክርስቲያን ዋና ምንባብ በዝርዝር እንድታጠና እድል ለመስጠት ነው። ከእነዚህ ንባቦች ውስጥ አንዱን ስታጠናና ስታሰላስል ተስፋችን ይህ ክፍል እንዴት የእግዚአብሔርን ለህዝቡ ያለውን ራእይ አንዳንድ ገፅታዎች እንደሚያበራ ትረዳ እና ታሳይ ዘንድ ነው። እናም በእርግጥ ጸሎታችን አንተ ቤተክርስቲያንን በተሻለ መንገድ በመረዳት፣ እነዚህን እውነቶች ከራስህ የግል የደቀመዝሙርነት ጉዞ፣ በቤተክርስቲያንህ ውስጥ ካለው አመራር እና ከከተማ አገልግሎት ጋር በማዛመድ የበለጠ ውጤታማ እንድትሆን ነው። ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮጀክት እንደመሆኑ የትርጓሜ ጥናት (ኤክሴጄሲስ) ለመስራት የጥናት ክፍሉን በአውዱ ውስጥ መረዳት ያስፈልጋል። በመቀጠልም ዋናውን ትርጉም ከተረዳህ በኋላ ለሁላችንም ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል መርህ ማውጣትና ይህንም በተጨባጭ ከህይወት ጋር ማዛመድ ይኖርብሃል። ይህን የግል የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጥናት በምታደርግበት ወቅት እነዚህ ሶስት ደረጃዎች ሊያግዙህ ይችላሉ:- 1. በተሰጠው ምንባብ ውስጥ ለተጠቀሱት ዋና አድማጮች እግዚአብሔር መናገር የፈለገው ምንድነው? 2. ከዚህ ምንባብ ልንማረው የምንችለውና ለሁሉም ዘመንና በየትኛውም ቦታ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ ልንወስደው የምንችለው መርህ ምንድነው? 3. ዛሬምመንፈስ ቅዱስ እኔን ከተማርኩት መርህ በመነሳት ምን እንዳደርግ ነው የሚፈልግብኝ? እንግዲህ እነዚህን ጥያቄዎች በተገቢው መንገድ ከመለስክ በቀጣይ ለወረቀት ስራህ የግልህን መረዳት ለማቅረብ ዝግጁ ነህ ማለት ነው። ለወረቀት ስራህ ይህን ቅደም ተከተል ተከትሎ መስራት ይረዳሃል፥ 1. የመረጥከው የንባብ ክፍል ዋና ጭብጥ ወይም ሃሳብ ምን እንደሆነ ለይተህ አስቀምጥ። 2. የምንባቡን ዋና ትርጉም በአጭሩ ግለጽ (ይህን በሁለት ወይም በሶስት አንቀጽ ልታስቀምጠው ትችላለህ ወይም ደግሞ በእያንዳንዱ ቁጥር አጫጭር ማጣቀሻ ወይም ማመሳከሪያ እየተጠቀምክ መሄድ ትችላለህ።) 3. ይህ የምንባብ ክፍል ሊሰጠን የሚችሉ ከአንድ እስከ ሶስት የሚደርሱ የክርስቲያን ሚሽን መርሆዎችን ዘርዝር።
ዓላማ
ዝርዝር መግለጫ እና አወቃቀር
Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online