Theology of the Church, Amharic Student Workbook
1 4 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።” ይላቸዋል። ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር የተመረጠ ሕዝብ ናት፣ እርሱን የሚያመልኩት ካህናት። ስለዚህም ቤተክርስቲያን አሁን በአሕዛብ ሁሉ መካከል በእግዚአብሔር መንግሥት እሴቶች በዓለም ውስጥ የምትኖር የእግዚአብሔር ሕዝብ ነች። እንግዲህ የእኛ ተግባር በእግዚአብሔር የሚመራ ዓለም ምን እንደሚመስል ለማወቅ የሚፈልግ ሰው ቤተክርስቲያንን በማየት ብቻ ሊያውቅ በሚችልበት መንገድ መኖር ነው። እንዴት ያለ ታላቅ ዕድል እና ክቡር ጥሪ ነው። የኒቂያን የእምነት መግለጫ (በአባሪው ውስጥ ይገኛል) ካነበብክ እና/ወይም ከዘመርክ በኋላ የሚከተለውን ጸሎት ጸልይ፥ የአብርሃም፣ የይስሐቅ እና የያዕቆብ አምላክ፣ በኢየሱስ ያመንነውን የአብርሃም ልጆች እና ለእርሱ የገባኸውን የተስፋ ቃል ወራሾች አድርገህ ስላካተትከን በጣም አድርገን እናመሰግንሃለን። አባት ሆይ፣ በዚህ በኃጢአተኛ ዓለም ውስጥ አንተን በትክክል እንድንወክል እርዳን። በተራራ ላይ እንዳለች ከተማ እንድንደምቅ በዙሪያችን ካሉ አሕዛብ እንድንለይ እርዳን። ሰዎች ያንተን ልብ እንዲገነዘቡ እና በሰማያት የምትኖር አባታችን ለአንተ ክብር የሚያመጡበትን መልካም ሥራ እንሰራ ዘንድ እርዳን። ከሁሉም በላይ ደግሞ ሰዎች ሁሉ ከመረጥከው ሕዝብህ ጋር የመካተት ዕድል ያገኙ ዘንድ የኢየሱስን ወንጌል በድፍረት እንድንሰብክ እርዳን። ይህንም ከአንተና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ለዘላለም በሚነግስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጸልያለን። አሜን።
የኒቂያ የእምነት መግለጫ እና ጸሎት
1
ይህ ትምህርት ፈተና የለውም
ፈተና
የቃል ጥናት ጥቅስ ምዘና
ይህ ትምህርት የቃል ጥናት ጥቅስ የለውም
የቤት ስራ/መልመጃ ማስረከቢያ
ይህ ትምህርት የቤት ስራ/መልመጃ የለውም
እውቂያ
ስለወደፊቱ የባከነ በጣም ብዙ ጊዜ
መጋቢው ስለመጨረሻው ዘመን ሲሰጥ ከነበረው ሴሚናር በኋላ፣ ከምእመናን አንዱ በመኪና ማቆሚያው ቦታ ላይ አስተያየት ሰጥቷል፣ “በትልልቅ ምስል ጉዳዮች ላይ ብዙ ጊዜ ማጥፋታችን ለምን እንደሚያስፈልገን በትክክል አልገባኝም። ለዛም ነው ቤተክርስቲያን ለአብዛኞቹ ሰዎች በጣም አሰልቺ የሆነችው - ዛሬ በሚከሰቱ ነገሮች ላይ እንዴት ማተኮር እንዳለብን አናውቅም። ሁሉም ነገር ላም አለኝ በሰማይ ነው፣ ስለ አንዳንድ የወደፊት ገነት፣ እግዚአብሔር አንድ ቀን ስለሚያደርገው ነገር
1
Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online