Theology of the Church, Amharic Student Workbook

/ 1 6 5

የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት

አ ባ ሪ 1 5 ድነት እንደ እግዚአብሔር ህዝብ ውህደት ቴሪ ኮርኔት

I. መዳንን በመጽሐፍ ቅዱስ አውድ ውስጥ ለመግለፅ በጣም የተሻለው መንገድ እንደ እግዚአብሔር ህዝብ ውህደት መግለፅ ነው። ሀ. ብሉይ ኪዳን 1. የብሉይ ኪዳን የመጀመሪያ የድነት ምስል እግዚአብሔር ሕዝቦቹን ከግብፅ ባርነት እና እስራት “ያዳነበት” የዘፀአት ምስል ነው፡፡ ሀ. መዳን ማለት ከባርነት ነጻ ወጥተው በእግዚአብሔር ጌትነት ፣ ሕጎች ፣ ጥበቃ ፣ አቅርቦት እና መገኘት ውስጥ ከእግዚአብሔር ሰዎች ጋር መቀላቀል ማለት ነው። ለ. ዘጸአት 6.7 (ዘሌዋውያን 26.12 ፣ ዘዳግም 4.20 ፣ ሆሴዕ 13.4) 2. እግዚአብሔር እስራኤልን “ሕዝቡ” አድርጎ መምረጡ ከምድር ሕዝቦች ሁሉ ልዩ ስፍራን ሰጥቷቸዋል፡፡ ሀ. ዘዳግም 7.6 ለ. ዘዳግም 27.9 3. ከእስራኤል ውጭ ላለ ማንኛውም ሰው የመዳን መንገድ ከእግዚአብሄር ህዝብ ጋር መቀላቀል ነበር ፡፡

ሀ. ዘፀአት 12.37-38, 48 ለ. ኢሳያስ 56.3-8

4. አዲስ ኪዳን እንደሚጠቁመው ሙሴ (የዘር ሃረጉ ዕብራይዊ ግን በባህሉ ያደገው ግብፃዊ በመሆኑ መጻተኛ ነበር) መዳንን እንዲያገኝ በእምነት ከእግዚአብሄር ህዝብ ጋር ለመቀላቀል ምርጫ ማድረግ ነበረበት ፡፡

ዕብራውያን 11.25

5. ማጠቃለያ [በብሉይ ኪዳን] መዳን የተገኘው አንድ ሰው ባሳየው ብቃት ሳይሆን ያ ግለሰብ በእግዚአብሔር የተመረጠው ህዝብ አካል በመሆኑ ነው (“Salvation,” International Standard Bible Encyclopedia [Electronic ed.]. Cedar Rapids: Parsons Technology, 1998.).

ለ. አዲስ ኪዳን

(ቲቶ 2.14)

Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online