Theology of the Church, Amharic Student Workbook

/ 2 7

የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት

ለ. ከክርስቶስ ጋር ያለው አንድነት ህጋዊ ገጽታ አለው፡ እግዚአብሔር ቁጣውን እና ፍርዱን በእኛ ምትክ በሞተው በክርስቶስ ላይ አደረገ። ከክርስቶስ ጋር በመተባበር በመስቀል ላይ በሞቱ ተካፋዮች እንሆናለን ስለዚህም እግዚአብሔር ኃጢአታችን እንደተከፈለ ይቆጥረዋል፣ በቸርነቱም ይቅር ይለናል።

1. ኢሳ. 53.5

2. ዕብ. 9.28

1

3. ቆላ.2.13-14

እምነት ከክርስቶስ ጋር ያለ እምነት እና አንድነት ስለሆነ፣ ይህ የጽድቅ ተምሳሌት በምንም መልኩ ማስመሰል የለበትም አይደለም፣ ይልቁንም በእምነት ከክርስቶስ ጋር ባለን አንድነት (በክርስቶስ በእኛ ስለሚኖር) እግዚአብሔር እውነተኛ የሆነውን ይመሰክራል። በእርግጥ እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ያጸድቃል፣ ነገር ግን በክርስቶስ አምነው ከእርሱ ጋር የተባበሩትን ብቻ ነው። ስለዚህ የክርስቶስ ጽድቅ ኃጢአተኛውን ያለብሳል፣ እርሱም ጻድቅ ይሆናል። ነገር ግን ይህ የሚሆነው አንድ ሰው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በእምነት ሲዋሃድ ብቻ ነው። . . .ይህ ማለት ከእንግዲህ ኃጢአተኞች አይደለንም ማለት አይደለም፤ ምክንያቱም በራሳችን በእርግጥም ሃጢአተኞች ነን። ነገር ግን በክርስቶስ እኛ ሙሉ በሙሉ ጻድቃን ነን! ~ J. Rodman Williams. Renewal Theology. Vol. 2. Grand Rapids: Zondervan, 1996. p. 74.

ሐ. ከክርስቶስ ጋር ያለው አንድነት መንፈሳዊ ገጽታ አለው፡ መንፈሳችን ከመንፈሱ ጋር ስለተጣመረ፣ የኢየሱስ ህይወት ውድቀትን እና ሞትን በማሸነፍ በእኛ ውስጥ ይፈስሳል።

1. ሮሜ. 8፡10-11

2. ቆላ.3.3-4

Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online