Theology of the Church, Amharic Student Workbook
/ 3 5
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
³ ቤተ ክርስቲያን በእግዚአብሔር ሕዝብ ምስል ጥላ ስር: ላኦስ ውስጥ ነበረች። በእስራኤል ሕዝብ በኩል እግዚአብሔር ሊመጣ ያለውን አንድ አዲስ የሰው ዘር ምልክት ሰጠን፣ እርሱም አሕዛብንና አይሁዳውያንን ያካትታል። ³ ምንም እንኳን እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያን የተለየ ቦታ ቢሰጣትም እስራኤልንም ጨርሶ አልተዋትም፣ ጥሪዋንና መመረጧንም ፈጽሞ አልሻረውም። በሮሜ 9-11 እንደተጠቀሰው እግዚአብሔር የአሕዛብን ድነት በሙላት ካመጣ በኋላ የእስራኤልን ቅሬታዎች ደግሞ ያድናቸዋል። ³ መዳን፣ ሶቴሪያ፣ ማለት አንድን ሰው መታደግ፣ ነጻ ማውጣት ወይም ደህንነቱ የተጠበቀ ማድረግ ማለት ነው። ³ ኃጢአት ከእግዚአብሔር የሚለየን ከመሆኑም በላይ እንድንጠፋ ያደርገናል፤ ይህም የእግዚአብሔርን ፍቅር፣ ጥበቃና እውነት እንዳናጣጥም ‘ያደርገናል። ³ ከእግዚአብሔር ‘መለየት’ የሚያስከትላቸው ውጤቶች፡- ሥጋዊና መንፈሳዊ ሞት፣ የኃጢአት እስራትና ፍርድ/ቅጣት ናቸው። ³ ከክርስቶስ ጋር ህብረት (በህይወቱ፣ በሞቱ እና በትንሳኤው በማመን) እግዚአብሔር እኛን ከራሱ ጋር ወደ ቀድሞው ህብረት የሚመልስበት መንገድ ነው። ³ ከክርስቶስ ጋር ኅብረት በኃጢአት ምክንያት የሚመጡትን ሦስት ችግሮች ሽሯል። ክርስቶስ ቅጣታችንን እና ፍርዳችንን በመስቀል ላይ ስለተሸከመ የክርስቶስ ሞት የእግዚአብሔርን ህግ በመጣሳችን የነበረብንን የህግ ዕዳ ከፍሎልናል። ክርስቶስ በሰይጣን ላይ የተጎናጸፈው ድል ከኃጢአት ባርነት ነፃ አውጥቶናል። ክርስቶስ በሞት ላይ የተጎናጸፈው ድል ደግሞ ከህይወቱ ጋር ስለተባበርን የዘላለምን ህይወት ዋስትና ይሰጠናል። ³ አንድ ሰው ከክርስቶስ ጋር ህብረት በማድረግ በአዲሱ መንግሥት ውስጥ ሕይወትን ከሚለማመዱ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ጋር ይካተታል። የክርስቲያን ማንነት የተመሰረተው እርሱ ወይም እርሷ አሁን የተመረጠው የእግዚአብሔር ህዝብ በሆነው የቤተክርስቲያን አካል በመሆናቸው ነው። በታሪክ እና በቅዱሳት መጻህፍት ጥላ ስለነበረችው ቤተክርስቲያን የዚህን ትምህርት ፅንሰ-ሃሳብ በተመለከተ ከተማሪዎችህ ጋር የምትወያይበት ጊዜ አሁን ነው። የቤተክርስቲያንን ፅንሰ-ሃሳብ ጥልቀት ለማድነቅ፣ እግዚአብሔር ለስሙ አህዛብን ከምድር ለመጥራት ያለው ፍላጎት ጥንታዊ እና ጥልቅ መሆኑን መረዳት አስፈላጊ ነው። ለእናንተ፣ እንደ ተማሪዎች፣ ከእግዚአብሔር የአጽናፈ አለሙ ታላቅ እቅድ ጋር መጋፈጥ የዚህ ክፍል አላማ ነው። አሁን ካጠናኸው ጽሑፍ አንጻር ምን ልዩ ጥያቄዎች አሉህ? ምናልባት ከዚህ በታች ያሉት አንዳንድ ጥያቄዎች የራስህን ግልጽ እና ወሳኝ ጥያቄዎችን እንድትፈጥር ሊረዱህ ይችላሉ።
1
የተማሪው ትግበራ እና አንድምታ
Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online