Theology of the Church, Amharic Student Workbook
4 0 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
ምደባዎች
1ኛ ጴጥሮስ 2፡9-10
የቃል ጥናት ትውስታ
ለክፍል ለመዘጋጀትና የሚቀጥለውን ሳምንት የምንባብ ምደባ ለማግኘት www.tumi.org/books ን ጎብኝ ወይም መምህርህን ጠይቅ።
የንባብ የቤት ስራ
የቀጣዩን ትምህርት ስራህን የምትጀምረው አሁን ነው ስለዚህ ስራህን አታዘግይ ወይም በመጨረሻው ሰዓት ለመስራት አትጣደፍ። በሚቀጥለው ሳምንት የምንመለከታቸዉን ፅንሰ-ሀሳቦች ከወዲሁ ለመቃረም እንዲረዳህ ለንባብህ በቂ ጊዜ ስጥ። በተጨማሪም በሚገባ በመሸምደድ ለመጪው ፈተና ያዘጋጁህ ዘንድ የዚህን ሳምንት ትምህርቶች በጥንቃቄ ገምግም። ቀጣዩ ፈተና የሚያተኩረው በዚህ ትምህርት በተሸፈነው የቪዲዮ ይዘት ላይ ነው ስለሆነ ማስታወሻህን ለመመልከት በቂ ጊዜ ማጥፋትህን እርግጠኛ ሁን፣ በተለይም በትምህርቱ ዋና ዋና ሃሳቦች ላይ አተኩር። እባክህን የተመደበውን ንባብ አንብበህ እያንዳንዱን ንባብ ከአንድ ወይም ከሁለት ሁለት አንቀጽ በማይበልጥ አጠቃልል። ማጠቃለያህን አጭር እና ቀላል አድርገው፣ እባክህ በእያንዳንዱ ንባብ ውስጥ ዋናው ነጥብ ነው ብለህ ስለምታስበው ሃሳብ ያለህን ግንዛቤ ግለጽ። ዝርዝር መግለጫ ለመስጠት ከልክ በላይ አትጨነቅ፤ ከዚህ ይልቅ በመጽሐፉ ክፍል ውስጥ የተብራራውን ዋና ሃሳብ ጻፍ። እባክህ በሚቀጥለው ሳምንት እነዚህን ማጠቃለያዎች ወደ ክፍል አምጣቸው። (እባክህ በዚህ ትምህርት መጨረሻ ላይ ያለውን “የንባብ ማጠናቀቂያ ቅጽ” የሚለውን ተመልከት።) በዚህ ትምህርት ውስጥ በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ከእርሱ ጋር ለዘላለም የሚኖሩትን የራሱን ህዝብ ከምድር ወደ ራሱ ለመጥራት ስላለው የእግዚአብሔር ዘላለማዊ እቅድ ተነጋግረናል። በሚቀጥለው ትምህርት ደግሞ ኃጢአተኞች የተመረጡት ህዝብ አካል እንዲሆኑ ስለሚያስችለው የእግዚአብሔር ጸጋ እና ጸጋው በአምልኮና በምስጋና ምላሽ እንድንሰጥ እንደሚያደርገን እንነጋገራለን። የሚቀጥለው ትምህርት “በአምልኮ ላይ ያለች ቤተክርስቲያን” የሚሰኝ ሲሆን ቤተክርስቲያን ከምትኖርባቸው ምክንያቶች አንዱና ዋነኛው ለእግዚአብሔር የሚገባውን ክብር ለመስጠት እንደሆነ ያስታውሰናል!
ሌሎች የቤት ስራዎች
1
የሚቀጥለውን ትምህርት በጉጉት እንጠባበቃለን።
ይህ ሥርዓተ-ትምህርት የThe Urban Ministry Institute (TUMI) የሺዎች ሰዓታት የሥራ ውጤት በመሆኑ ያለ ፈቃድ ማባዛት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ TUMI እነዚህን መማሪያዎች ለእግዚአብሔር መንግሥት እድገት ለመጠቀም ለሚፈልጉ ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል፤ በተጨማሪም ለማባዛት በተመጣጣኝ ዋጋ ፈቃድ ይሰጣል፡፡ እባክህ ይህ መጽሐፍ በትክክል ፈቃድ ያገኘ መሆኑን ከመምህርህ ጋር በመሆን አረጋግጥ፡፡ በ TUMI እና በፈቃድ አሰጣጥ ፕሮግራማችን ላይ የበለጠ መረጃ ለማግኘት Www.site.org እና Www.tumi.org/license ን ጎብኝ፡፡
Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online