Theology of the Church, Amharic Student Workbook

6 0 /

የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት

2. የፔላጊን ኑፋቄ ምንድን ነው? 3. ጥምቀትን እና የጌታን እራትን እንደ ቅዱስ ቁርባን በሚገልጹት እና እነዚህን እንደ ስርዓት በሚያስቧቸው የክርስቲያን ወጎች መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? 4. ጥምቀትን እንደ “የጸጋ መንገድ” የመመልከት ዋናዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ክርክሮች ምንድን ናቸው? 5. ስለ ጌታ እራት አራቱ ዋና ዋና አመለካከቶች ምንድን ናቸው? 6. የጥምቀታዊ ዳግም ውልደት (መጠመቅ መዳንን ያመጣል የሚለው እምነት) መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ትምህርት የሆነው ለምንድን ነው? ይህ ጥምቀትን እንደ ቅዱስ ቁርባን ከሚወስደው እይታ እንዴት ይለያል? 7. የፕሮቴስታንት ተሃድሶ አራማጆች ኤክስ ኦፔራ ኦፔራቶ በሚሰኘው የካቶሊክ መሠረተ ትምህርት ያልተስማሙት ለምንድን ነው? 8. በቅዱስ ቁርባን/በስርዓተ አምልኮ ልምምዶች ላይ እምነት የሚጫወተው ሚና ምንድነው?

2

በአምልኮ ላይ ያለች ቤተ ክርስቲያን ሴግመንት 2፡ የቤተክርስቲያን ጥሪ

ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ

የቤተ ክርስቲያን ጥሪ ሁሉን ቻዩን እግዚአብሔርን ማምለክ ነው። እግዚአብሔርን በአምልኮአችን ውስጥ የምናከብረው ስለ ፍጹም ባሕርይው - ብቸኛ ቅድስናው፣ ወሰን የለሽ ውበቱ፣ ወደር የሌለው ክብሩ እና አቻ ስለሌለው ሥራው ነው። ቤተ ክርስቲያን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እውነተኛ አምላክ የሆነውን አምላከ ሥላሴን ታመልካለች። በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካኝነት በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ያህዌ አምላክን ብቻ እናመልካለን። በተጨማሪም ቤተክርስቲያን እግዚአብሔርን የምታመልከው በምስጋና እና በውዳሴ እና ቃሉንና ምስጢራትን በሚያጎላ በስርዓተ ቅዳሴ፣ እንዲሁም እንደ ቃል ኪዳን ማህበረሰብ በመታዘዝ እና በአኗኗር ዘይቤዋ ነው። የዚህ የቤተክርስቲያን ጥሪ የተሰኘ ሴግመንት አላማችን የሚከተሉትን እንድታዩ ለማስቻል ነው፡- • እግዚአብሔርን በአምልኮአችን ውስጥ ስለ ፍጹም ባሕርይው - ብቸኛ ቅድስናው፣ ወሰን የለሽ ውበቱ፣ ወደር የሌለው ክብሩ እና አቻ ስለሌለው ሥራው የምናከብረው መሆኑን። • እኛ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እውነተኛ አምላክ የሆነውን አምላከ ሥላሴን እንደምናመልክ እና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካኝነት በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ያህዌ አምላክን ብቻ ማምለካችንን።

የሴግመንት 2 ማጠቃለያ

Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online