Theology of the Church, Amharic Student Workbook

/ 6 3

የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት

ሠ. ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔርን ብቻ ታመልካለች፡ አምላከ ሥላሴ እግዚአብሔር አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ክብሩን ለሌላ ለማንም አያካፍልም፤ ብቻውን ምርጡና የላቀው ምስጋናችን ይገባዋል።

1. ኢየሱስ አብ የተለየ አምልኮ እንዲሰጡት ሕዝቡን እንደሚፈልግ አስተምሮናል፣ ዮሐንስ 4፡21-24።

2. ቤተ ክርስቲያን የምታመልከው አምላክ ክብሩን ለሌላ አያካፍልም።

ሀ. ኢሳ. 48.11

2

ለ. ኢሳ. 42.8

ሐ. ዮሐንስ 5፡22-23

ረ. ቤተ ክርስቲያን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔርን ታመልካለች፣ ታከብራለች።

1. በመስቀል ላይ የፈሰሰው ደሙ ቤተክርስቲያን ወደ እግዚአብሔር ፊት እንድትገባ አስችሏታል፣ ዕብ. 10፡19-20።

2. ደሙ እግዚአብሔርን በእውነትና በእምነት እንድናመልከውና እንድናገለግለው ከሞተ ሥራ ሕሊናችንን ያነጻል፣ ዕብ. 9፡13-14።

3. ወደ እግዚአብሔር የምንቀርበው በራሳችን ጽድቅና ክብር አይደለም። ይልቁንም በኢየሱስ የሊቀ ክህነት አገልግሎት፣ አሁን በተረጋገጠ ሙሉ እምነት ወደ ቅዱሱ አምላካችን መቅረብ እንችላለን፣ ዕብ. 10፡21-22።

Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online