Theology of the Church, Amharic Student Workbook
7 0 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
³ ቤተክርስቲያን እግዚአብሔርን የምታመልከው በፍጥረታቱ እና በማዳን ስራው በኩል ባለው ምጡቅ ባህሪው እና አቻ በሌለው ተፈጥሮው ነው። ስለዚህም እግዚአብሔር በቤተክርስቲያን አባላት ዘወትር ሊመለክና ሊመሰገን የተገባው ነው። ³ ሁሉም ነገር የሚኖረው በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድና ለእርሱ ደስታ በመሆኑ፣ ሁሉም ፍጥረታትና ግኡዛን ባላቸው ዓላማ ጋር የሚካፈሉት አንዱ ተግባር እግዚአብሔርን ማምለክ ነው። የሁሉም ነገር ቴሎስ (የመጨረሻው ግብ) እግዚአብሔርን ስለ ማንነቱ እና ስላደረገው ሁሉ ማመስገን እና ማክበር ነው። ³ ቤተ ክርስቲያን በምስጋናና በአምልኮ አገልግሎት እግዚአብሔርን ታመልካለች፤ እንደ ወንድና ሴት ካህናት በዝማሬ፣ በሽብሸባ፣ በመንበርከክ፣ በዝምታ፣ በጭብጨባ፣ በእልልታ፣ እና በተለያዩ መንገዶችና ዘዴዎች ክብርን ትሰጣለች። ³ ስርዓተ ቅዳሴ የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ሳይገድበው የእግዚአብሔርን ቃል ስብከትና ትምህርት የምታውጅበትና ሁሉም በጋራ በሚሰበሰቡበት ጊዜ የጌታ ማዕድ አንድ ላይ የሚቆርሱበት ልዩ የአገልግሎት ሥርዓት ነው። ³ ቤተክርስቲያን በአምልኮቷ ውስጥ የምትገለጽባቸው መንገዶች ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት እንደ እግዚአብሔር ቃል መሆን አለባቸው። እያንዳንዱ የቤተክርስቲያን ባህል ነፃ ቢሆንም ዝማሬውን፣ ስልቱን እና የአምልኮ ሥርዓቱን ከክርስቶስ መርሆችና እውነቶች ጋር በሚስማማ መልኩ የመግለፅ ሃላፊነት አለበት። አሁን አብረውህ ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር በመሆን በአምልኮ ላይ ያለች ቤተክርስቲያን ላይ ያሉህን ጥያቄዎች የምትወያይበት ጊዜ ነው፡፡ በእግዚአብሔር እና በአምላኪው ማህበረሰብ መካከል ያለውን ግንኙነት ለመመስረት የጸጋን ስልታዊ ሚና እንዲሁም ቤተክርስቲያን እግዚአብሔርን ከፍ ለማድረግ ያላትን ነፃነት እና ሃላፊነት መረዳት ዛሬ መሪ ለመሆን መሰረታዊ ነው። አንድ ሰው እነዚህን እውነቶች እስካልተረዳ እና በቃላት እና በድርጊት መግለጽ እስኪችል ድረስ፣ አንድ ሰው በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ውጤታማ አመራርን መስጠት እንደማይችል መከራከር ይቻላል። የጽሑፉን እውነታዎች እና አንድምታዎች ተመልክተህ ከአንተና በአገልግሎትህ ውስጥ ካሉ ግንኙነቶች ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ለማወቅ እነዚህን ጥያቄዎች ተመልከት። ስለእነዚህ እውነታዎች ስለራስህ ግንዛቤ አሁን ካጠናኸው ጽሑፍ አንጻር ምን ልዩ ጥያቄዎች አሉህ? ምናልባት ከዚህ በታች ያሉት አንዳንድ ጥያቄዎች የራስህን ይበልጥ ግልጽ እና ወሳኝ ጥያቄዎችን እንድታነሳ ሊረዱህ ይችሉ ይሆናል። * ምንም እንኳን ብዙ ሰዎች ስለ “ፔላጂያን ኑፋቄ” ሰምተው የማያውቁ ቢሆንም ይህን ስህተት የሚፈጽሙ ብዙ ሰዎች አሉ። በዚህ መንገድ መዳንን የተረዳ ሰው እንዴት ክርስቲያን መሆን ምን ማለት እንደሆነ ሊናገር ይችላል? * ቤተክርስቲያንህ (ወይ ቤተ እምነትህ) የጌታ እራት እና ጥምቀትን እንደ ቅዱስ ቁርባን ወይስ እንደ ስርአተ አምልኮ ነው የምትረዳው? ለምን? * ቤተ ክርስቲያን የጌታን እራት በየምን ያህል ጊዜ አንድ ላይ መውሰድ አለባት? ለምን?
2
የተማሪው ትግበራ እና አንድምታዎች
Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online