Theology of the Church, Amharic Student Workbook
7 2 /
የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት
አቋም ይዟል ስለዚህም ይህን ሁሉ በሰውነት እንቅስቃሴ ላይ ያለውን ትኩረት ማስቆም ይፈልጋል። ከሁሉም በላይ ይህ የፕሮፌሽናል እግር ኳስ ጨዋታ አይደለም፣ ሁሉን ቻይ ለሆነው አምላክ የሚቀርብ አምልኮ እንጂ የሚል አቋም አለው። ለዚህች ቤተ ክርስቲያን የሚበጀውን በተመለከተ በአባላት መካከል ግጭት እየተፈጠረ ነው። ይህን ችግር እንዲፈቱ እንዴት ልትረዳቸው ትችላለህ?
ጸጋ ብቻ አንድ መጋቢ ለአንዲት ወጣት ሴት ስለ ኢየሱስ ይመሰክርላትና ወደ ቤተ ክርስቲያን እንድትሄድ ይጋብዛታል። ሴትየዋም እንዲህ ስትል መለሰች፡- “አሁን ይህን ለማድረግ ብቁ አይደለሁም። ስለ ኃይማኖት እና ስለመሳሰሉት ነገሮች ፍላጎት አለኝ ነገር ግን በመጀመሪያ ህይወቴን ማስተካከል እፈልጋለሁ። አንዳንድ ነገሮችን ካጸዳሁ በኋላ ወደ ቤተክርስቲያን እመጣለሁ።” መጋቢው ለዚች ወጣት ምን ሊመልስላት ይገባል? ለጌታ ዝቅ ማለት ራሳቸውን ሴላ ብለው የሚጠሩ አንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ አዲስ የጃዝ-ፈንክ-ሮክ የአምልኮ ባንድ ተነስቷል። በጉባኤው ውስጥ ምሥጋና እና አምልኮን ወደ አዲስና ኃይለኛ ደረጃ ለማምጣት ቆርጠው ተነስተዋል፣ ነገር ግን ይህን የሚያደርጉት በጣም በከፍተኛ የድምጽ መጠን እና በርካታ የቤተ ክርስቲያን አባላትን በሚይዝ ትዕይንት፣ እንዲያውም አንዳንዶቹ ነገሮች ስለራሳቸው ነው። ሴላ በቅዳሜ ምሽት ኮንሰርታቸው ላይ ከፍተኛ ተቀባይነትን እያገኙ ነው፤ በከተማ ዙሪያ ባሉ አንዳንድ የጀማ ወንጌል ስራዎችም ላይ ጌታ በእጅጉ ተጠቅሞባቸዋል። ሆኖም ስትሰሙዋቸው ልክ ዓለማዊ ባንዶችን ይመስላሉ። እንደ እውነቱ ከሆነ ብዙዎቹ መርሙሮቻቸው በክርስቲያናዊ ግጥሞች የተዋቀሩ ታዋቂ የፖፕ ሙዚቃ ዘፈኖችን ይመስላሉ። አንዳንድ ሰዎች ለመደነስ ወደ ኮንሰርታቸው እንደሚመጡ አምነዋል! ከበሮ ተጫዋቹ “ለጌታ ዝቅ ማለት” እንዳለው እርሱን ሳይተዉ ሴላ በአምልኮ ለእግዚአብሔር ያላቸውን ፍቅር ሙሉ በሙሉ ለመግለጽ ከሚያደርጉት ሙከራ አንጻር ምን ትመክራቸዋለህ? በእግዚአብሔር ቸርነት እንደ ነጻ ስጦታ ያልተሰጠንን መዳን ለመመኘትም ሆነ ለማግኘት የምናደርገው ምንም ነገር የለም። ይህ የእግዚአብሔር የጸጋ ልምምድ ቤተክርስቲያንን እግዚአብሔርን ማምለክ ግዴታውና ደስታው የሆነለት ማህበረሰብ እንድትሆን አድርጓታል። እግዚአብሔርን በአምልኮአችን የምናከብረው ስለ ፍጹም ባሕርይው - ብቸኛ ቅድስናው፣ ወሰን የለሽ ውበቱ፣ ወደር የለሽ ክብሩ እና አቻ ስለሌለው ሥራው ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ባለው የእግዚአብሔር ጸጋ፣ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አምላከ ሥላሴ የሆነውን እውነተኛ አምላክ እንድናመልከው ነጻ ወጥተናል። በተጨማሪም ቤተክርስቲያን እግዚአብሔርን የምታመልከው በምስጋና እና በውዳሴ እና ቃሉንና ምስጢራትን በሚያጎላ በስርዓተ ቅዳሴ፣ እንዲሁም እንደ ቃል ኪዳን ማህበረሰብ በመታዘዝ እና በአኗኗር ዘይቤዋ ነው።
3
2
4
የትምህርቱን ንድፋዊ ሃሳብ በድጋሚ መጻፍ
Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online