Theology of the Church, Amharic Student Workbook

7 4 /

የ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሥ ነ - መ ለ ኮ ት

ምደባዎች

ዕብራውያን 10፡19-22

የቃል ጥናት ትውስታ

ለክፍል ለመዘጋጀትና የሚቀጥለውን ሳምንት የምንባብ ምደባ ለማግኘት www.tumi.org/books ን ጎብኝ ወይም መምህርህን ጠይቅ።

የንባብ የቤት ስራ

ከላይ የተሰጡትን የቤት ስራዎች በሚገባ ካነበብክ በኋላ ልክ እንደ ባለፈው ሳምንት አጠር ያለ ማጠቃለያ በመጻፍ በቀጣዩ ክፍለ ጊዜ ይዘህ ቅረብ፡፡ (እባክህ በዚህ ትምህርት መጨረሻ ላይ የሚገኘውን “የንባብ ማጠናቀቂያ ገጽ” ተመልከት)፤ አሁን በቀጣይ ስለምትሰራው ኤክሴጄቲካል ፕሮጀክት የንባብ ክፍል የምትመርጥበትና ስለ ሚኒስትሪ ፕሮጀክትህ የምታስብበት ጊዜ ነው፡፡ እነዚህን ውሳኔዎች ለማድረግ አትዘግይ፤ ቶሎ መወሰንህ ለዝግጅት በቂ ጊዜ እንዲኖርህ ያደርጋል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በክርስቶስ በማመን በእግዚአብሔር ጸጋ የተለወጡና የእግዚአብሔርን ጸጋ የተለማመዱ ናቸው። ይህ ጸጋ ይህን ኃያል የፍቅር አምላክ እንዲያመልኩና እንዲያመሰግኑ ያደርጋቸዋል፣ ነገር ግን በሌላ መልኩ ደግሞ ይህን አስደናቂ የኢየሱስን የፍቅር ታሪክ ለሌሎች ለማካፈል ከፍተኛ ሃላፊነትን ይሰጣቸዋል። በሚቀጥለው ትምህርታችን ቤተክርስቲያን ለክርስቶስ እና ለመንግስቱ በድርጊቷ እና በአዋጅዋ እንድትመሰክር ስለሰጣት ስልጣን እና እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን በመንፈሱ በዚህ አለም የእርሱ ወኪልና ተጠሪ እንድትሆን እንዴት እንደሚያስታጥቃት እንመለከታለን።

ሌሎች የቤት ስራዎች

2

ለቀጣዩ ትምህርት መዘጋጀት

Made with FlippingBook - professional solution for displaying marketing and sales documents online