Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide
1 1 0 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
በእርግጥ እውነትን ለተራቡ፣ ምሳሌው የጌታን ማንነት እንዲመረምሩ እና የእግዚአብሔርን ሥራ በጥልቀት እንዲያስሱ ይጋብዛል። ቃሉን ለማሰስ ለማይፈልጉ፣ መዝ 78 በአዲስ ኪዳን በጌታ በኢየሱስ ትምህርት ውስጥ እንደተገለጸው የምሳሌውን ቃል ለማይሰሙት የሚያበሳጭ እና ማስተዋልን የሚከለክል ነው፡፡ ማቴ. 13፡13 - “ስለዚህ እያዩ ስለማያዩ እየሰሙም ስለማይሰሙ ስለማያስተውሉም በምሳሌ እነግራቸዋለሁ።” ማቴ. 13፡34-35 - “ኢየሱስም ለሕዝቡ ይህን ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፤ በነቢዩም፦ በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ያለ ምሳሌ አልተናገራቸውም።”
ማር 4፡34 - “ለብቻቸውም ሲሆኑ ነገሩን ሁሉ ለገዛ ደቀ መዛሙርቱ ይፈታላቸው ነበር።”
እውነትን በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ የጌታን ሃሳብ ለመመርመር ግብዣን የሚወክል እያንዳንዱ ምሳሌ፣ ታሪክ፣ ምልክት እና ዘይቤ ያለው የምስሎች ዓለም ነው። ና፣ ፍለጋውን በመቀላቀል በምስላዊው አለም ውስጥ የጌታን እውነት ፈልግ።
የኒቂያን የእምነት መግለጫ (በአባሪው ውስጥ የሚገኝ) ካነበብክ እና/ወይም ከዘመርክ በኋላ የሚከተለውን ጸሎት ጸልይ የምህረት አምላክ ሆይ የማይሻርን ቃል ኪዳን ገብተኽልናል፡፡ በሚለዋወጡት ቃሎቻችን መካከል፣ የማይለውጠውን ዘላለማዊ ቃልህን ተናገር። ያኔ ለቃል ኪዳኖችህ በታማኝነት እና በታዛዥነት ህይወት ምላሽ እንድንስጥ በጸጋ ታግዘናለህ፤ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል። አሜን።
3
የኒቂያ የሀይማኖት መግለጫ እና ጸሎት
~ Presbyterian Church (U.S.A.) and Cumberland Presbyterian Church. The Theology and Worship Ministry Unit. Book of Common Worship. Louisville: Westminister/John Knox Press, 1993. p. 91.
ማስታወሻዎችህን አስቀምጠህ ፣ ሃሳቦችህን እና ምልከታዎችህን ሰብስበህ ለትምህርት 2 “የመጽሐፍ ቅዱስ ስነ አፈታት: የሶስት ደረጃ ሞዴል” የተዘጋጀውን አጭር ፈተና ውሰድ
የሙከራ ፈተና
ከሌላ ተማሪ ጋር በመሆን ላለፈው ክፍለ ጊዜ የተመደቡ የቃል ጥናት ጥቅሶችን ገምግሙ ፣ ፃፉ እና/ ወይም አንብቡ - ዕዝራ 7፡10; የሐዋ 17፡11; እና መዝ 1፡1-3።
የቃል ጥናት ጥቅስ ቅኝት
ያለፈውን ሳምንት ለንባብ የጠሰጠ ሥራ በማጠቃለል አጭር ክለሳ በማዘጋጀት በተመደበው ንባብ (ንባብ ማጠናቀቂያ ገጽ) ላይ ለማንሳት ዋና ዋና ነጥቦችን አብራራ፡፡
የቤት ስራ/መልመጃ ማስረከቢያ
Made with FlippingBook flipbook maker