Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide
/ 1 8 1
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
5. መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በየትኞቹ ጥንታዊ ቋንቋዎች ነው? የእነዚህ ቋንቋዎች ትርጉምስ ለምን ያስፈልገናል? ለሁሉም አማኞች በቂ የሆነ ትርጉም መፍጠር አስቸጋሪ የሆነባቸው አንዳንድ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? አብራራ። 6. በአብዛኞቹ ዘመናዊ የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጉሞች ላይ ምን ያህል መተማመን እንችላለን? እነዚህ አስተማማኝ የመጀመሪያዎቹ ቋንቋዎች ትርጉም መሆናቸውን እንዴት እናውቃለን? 7. ኮንኮርዳንስ፣ ሌክሲከን እና የኤክስፖዚሽን መዝገበ ቃላት ምንድን ናቸው፣ ስለ መጽሐፍ ቅዱሳዊው ጽሑፍ ያለንን ግንዛቤ ከማሳደግስ አንፃር እንዴት ይሠራሉ? እንዴት ጥቅም ላይ መዋል አለባቸው? በምንጠቀማቸው ጊዜስ ምን ዓይነት ጥንቃቄዎችን ልናስተውል ይገባል? 8. የምንባብ ማብራሪያዎች ምንድን ናቸው? የቅዱሳት መጻሕፍትን አንድ ክፍል ወይም ምንባብ ለመተርጎም በምናደርገው ጥረት ውስጥ እንዴት ሊረዱን ይችላሉ? 9. ያሉንን መሠረታዊ መሣሪያዎች በነጻነት ለመጠቀም በምንፈልግበት ጊዜ የትኛውን መሠረታዊ ሥርዓት ማስታወስ ይኖርብናል? እነዚህን መሣሪያዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን ውስጥ ስንጠቀም ምንጊዜም መጠንቀቅ ያለብን ስለምንድነው?
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ውስጥ የጥናት መሣሪያዎችን መጠቀም ሴግመንት 2፡ ተጨማሪ ሥነ-መለኮታዊ መሣሪያዎች
4
ቄስ ዶክተር ዶን ኤል ዴቪስ
ከመሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ የትርጓሜ መሳሪያዎች በተጨማሪ (ማለትም፣ ጥሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም፣ የግሪክ እና የዕብራይስጥ መዝገበ-ቃላት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ ኮንኮርዳንስ፣ እና ተዓማኒ የሆኑ የትርጓሜ ማብራሪያዎች)፣ ለእግዚአብሔር ቃል ያለንን ግንዛቤ የሚያበለጽጉ ተጨማሪ መሣሪያዎች አሉ። እነዚህም የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ አትላስ እና የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፣ ርዕሳዊ መጽሐፍ ቅዱስ፣ የሥነ መለኮት መዝገበ-ቃላት እና ሥነ-መለኮታዊ ማብራሪያዎችን ያካትታሉ። እያንዳንዳቸው እነዚህ መሳሪያዎች የሚያተኩሩት ከቋንቋ፣ ባህል፣ ታሪክ እና ስነ-መለኮት ጉዳዮች ጀምሮ በልዩ የመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጐም ተግዳሮቶች ላይ ነው። ልክ እንደማንኛውም አጋዥ መሣሪያ፣ የመጽሐፍ ቅዱስን አስፈላጊ መልእክት በመካድ ወይም በማሳነስ ሳይሆን ነገር ግን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነት እና ስለመዳናችን ስለሚናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ ጽሑፍ እውቀታችንን ለማሳደግ ልንጠቀምባቸው ይገባል። የዚህ ተጨማሪ ሥነ-መለኮታዊ መሣሪያዎች የተሰኘ ሴግመንት ዓላማ የሚከተሉትን እንድትመለከት ለማስቻል ነው፡- • ከመሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ የትርጓሜ መሳሪያዎች በተጨማሪ (ማለትም፣ ጥሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም፣ የግሪክ እና የዕብራይስጥ መዝገበ-ቃላት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣
የሴግመንት 2 ማጠቃለያ
Made with FlippingBook flipbook maker