Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide

1 8 0 /

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

ማጠቃለያ

» ለመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜ መሰረታዊ አጋዥ መሳሪያዎች ስለ ጥንታዊው ጽሑፍ ባለን ግንዛቤ እና እኛ ዛሬ ላይ በምንተገብርበት መንገድ መካከል ያለውን ርቀት ለማጥበብ ይረዳል። » አንድ የቅዱሳት መጻሕፍት ተማሪ በአንጻራዊ አነስተኛ ጥረት፣ ስለ ጽሑፉ ያለንን ግንዛቤ የሚከለክሉትን ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ ቋንቋዊ እና ማህበራዊ ክፍተቶችን እነዚህን መሳሪያዎች አግኝቶ ሊማር ይችላል።

እባክህ በነዚህና በሌሎችም በዚህ ቪዲዮ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች በቂ ጊዜ ወስደህ ምላሽ ለመስጠት ሞክር፡፡ በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሑራን ባደረጉት ታላቅ ሥራ ምክንያት፣ አሁን ስለ መጽሐፍ ቅዱሳዊው ጽሑፍ ዓለም ግንዛቤ ለመስጠት የተነደፉ አስደናቂ ምሁራዊ መሣሪያዎችን የመጠቀም ዕድል አለን። እንደዚህ አይነት ምሁራዊ ማመሳከሪያዎችን የመጠቀማችን አስፈላጊነት በመጽሐፍ ቅዱሳዊው ዓለም እና በእኛ ዘመናዊ ዓለም መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ እንድንችል ለመርዳት እና በዚህም ቃሉን በቀደመው አውድ ውስጥ በትርጉሙ እንደገና ለመገንባት በትክክል መተርጎም መቻል ነው። የሚከተሉትን ጥያቄዎች በምትገመግምበት ወቅት የመሠረታዊ አጋዥ መሳሪያዎችን ሚና እና አጠቃቀም እንዲሁም የጽሑፍ ጥናታችንን እንዴት እንደሚያሳድጉ እርግጠኛ መሆን ይኖርብሃል። 1. ለጠቅላላው ህዝብ የምሁራን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሳሪያዎች አቅርቦት አሁን ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል? ስለዚህኛው እና ስለ ጥንታዊው ዓለም ባለን እውቀት መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ፍላጎት ላላቸው ሰዎች እንደዚህ ያሉ መሳሪያዎች ምን አይነት አማራጮችን ይሰጧቸዋል? 2. የዚህን ቃል ትርጉም አብራራ፡- “በመጽሐፍ ቅዱሳዊ አተረጓጎም ውስጥ ያሉት ማመሳከሪያዎች በመጽሐፍ ቅዱሳዊው ዓለም እና በእኛ ዘመናዊ ዓለም መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ የሚረዱን ናቸው።” በእነዚህ ሁለት ዓለማት መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ የእግዚአብሔርን ቃል በትክክል ለመተርጎምና ለእኛ ያለውን ጥቅም ለመረዳት ወሳኝ የሆነው ለምንድን ነው? 3. በቋንቋ፣ በባህል ወይም በእኛና በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ደራሲዎችና ተደራሲያን ባህል መካከል ስላለው ልዩነት ባለን እውቀት የምናጠብብበትን መንገድ ለይቶ ለማወቅ የሚረዳንን መሣሪያ በምን መልኩ መገምገም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? 4. በዚህ ሴግመንት ውስጥ “መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ የትርጓሜ መሣሪያዎች” ተብለው የተወሰዱትን ዘርዝር። ከእነዚህ ሁሉ መሰረታዊ መሳሪያዎች ውስጥ በሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ውስጥ በጣም አስፈላጊ እና መሠረታዊ የሆነው የትኛው ነው ብለህ ታምናለህ? አብራራ።

መሸጋገሪያ 1

የተማሪው ጥያቄዎች እና ምላሾች

ገጽ 307  3

4

Made with FlippingBook flipbook maker