Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide
1 9 6 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
ማጠቃለያ
» ከመሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ የትርጓሜ መሳሪያዎች በተጨማሪ፣ ለእግዚአብሔር ቃል ያለንን ግንዛቤ የሚያበለጽጉ ሌሎች በርካታ ታሪካዊ፣ ሥነ-መለኮታዊ እና ገላጭ መሳሪያዎች አሉ። » ምንም አይነት መሳሪያዎች ብንጠቀምም፣ አንዳቸውም ቢሆኑ ለራሳችን በጥንቃቄ፣ በጸሎት እና በታዛዥነት የምናደርገው የእግዚአብሔር ቃል ጥናት ምትክ ሆኖ እንዲያገለግል የታሰበ አይደለም። » ነገር ግን፣ ጠንቃቆች ከሆንን እና መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ዓለም ለመረዳት እነዚህን መሳሪያዎች በትክክል ከተጠቀምንባቸው፣ እነዚህ መሳሪያዎች የቃሉ ጥናታችን ላይ ተሃድሶ ሊያመጡ ይችላሉ። » በተሻለ ሁኔታ ለራሳችን መመገብ ብቻ ሳይሆን በእነርሱ አማካኝነት የመንግሥቱን የምሥራች መስበክና ክርስቶስ እንድናደርግ ባዘዘን መሠረት የእግዚአብሔርንም መንጋ መመገብ እንችላለን። » የእግዚአብሔርን ፍጹም የእውነት ቃሉን በቅንነት የምንይዝ ራሳችንን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ትጉ ሠራተኝነታችንን የምናረጋግጥ ሠራተኛ እንድንሆን እግዚአብሔር ልቦናንና ሃይልን ይስጠን! የሚከተሉት ጥያቄዎች የተነደፉት በሁለተኛው የቪዲዮ ሴግመንት ውስጥ ያለውን ይዘት ለመገምገም ለማስቻል ነው። ይህ ልዩ የማስተማር ክፍለ ጊዜ ያተኮረው በመጽሐፍ ቅዱሳዊ አተረጓጎም ውስጥ የእግዚአብሔር ቃል ጥናታችንን በእጅጉ ሊያሳድጉ በሚችሉ አንዳንድ ተጨማሪ መሳሪያዎች ላይ ነው። እነዚህም የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ አትላስ እና የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ መጽሐፍን፣ ርዕሳዊ መጽሐፍ ቅዱስን፣ የሥነ መለኮት መዝገበ ቃላት እና የተለያዩ ዓይነት ማብራሪያዎችን ያካትታሉ። እነዚህ ሁሉ አጋዥ መሳሪያዎች በእኛ አለም እና በደራሲዎች እና በተደራሲያኑ አለም መካከል ያለውን ርቀት በማጥበብ በዋጋ ሊተመን የማይችል እርዳታ ሊሰጡን ይችላሉ። በራሳችን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አተረጓጎም ውስጥ በትክክል ለመጠቀም የትኞቹን ደንቦች እና መርሆዎች ማወቅ እንዳለብን በማተኮር ስለእነዚህ መሳሪያዎች የሚከተሉትን እውነታዎች ከልስ። 1. ለክለሳ ያህል፣ “መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ የትርጓሜ መሣሪያዎች” ተደርገው የተቆጠሩትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሀብቶች እንደገና ዘርዝር። እንደገና፣ በተለይም ሌሎችን በቤተክርስትያን ውስጥ ሌሎችን የመምራት እና የመመገብ ሃላፊነት እንደተጣለባቸው ሰዎች እነዚህ መሳሪያዎች ቃሉን በታማኝነት እቅረብ ለምን መሰረታዊ እንደሆኑ ግለጽ። 2. በዚህ ክፍል ውስጥ የተመለከትናቸው ተጨማሪ መሳሪያዎች በመጽሐፍ ቅዱሳዊው ዓለም እና በእኛ አለም መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ አቅማችንን ለማሳደግ የተነደፉ ናቸው። ከእነዚህ ተጨማሪ መሣሪያዎች ውስጥ፣ በተለይም የከተማ መሪዎች የከተማ
4
መሸጋገሪያ 2
የተማሪው ጥያቄዎች እና ምላሾች
Made with FlippingBook flipbook maker