Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide
2 0 2 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
መለኮት ጉዳዮች ውዝግቦች የተሞላ ነው። ወንድማችን ምን ነካው? በማመሳከሪያዎች፣ በእውቀት እና በሙያዊ ብቃት ላይ ከመጠን በላይ ማተኮር ለዚያ ትኩረት የተጋለጠውን ሰው በምን መልኩ ነው ያስታበየው? አንድ ሰው በሂደቱ ውስጥ አሰልቺ እና ፍሬ ቢስ ሳይሆንና ምንም ሳይታበይ ባሉት በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ማመሳከሪያዎች እንዴት ሊታነጽ ይችላል?
እውነትን ስላላወቅህ ነፃ አልወጣህም በቅርቡ በአካባቢው በሚገኝ አንድ የከተማ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚኖሩ ሦስት የይሖዋ ምሥክሮች የመንግሥት አዳራሽ አባላት አካባቢውን እየዞሩ አነጋግረው ነበር። ከትንሽ ጊዜ የጨዋነት ውይይት በኋላ፣ የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት ወደሚክደው ዋና ጉዳያቸው ገቡ። በቅዱሳን ጽሑፎች ላይ ሙሉ እውቀት ያለው አባልህ፣ ስለ ኢየሱስ አምላክነት ያለውን ግንዛቤ የቻለውን ያህል ተሟግቷል። ሦስቱ ምስክሮች ግን የግሪክኛውን የዮሐንስ 1.1ን ደጋግመው ይጠቅሳሉ፣ ይህም የግሪክኛው ትክክለኛ አንቀፅ እንደጎደለው ይከራከራሉ፣ ይህም ከእኛ ዘመናዊ የእንግሊዝኛ ትርጉሞች ውስጥ አብዛኞቹን ትርጉሞች ሐሰት ያደርጋቸዋል። የተበሳጨውም አባል መጋቢውን ስለ ኢየሱስ ያለውን እምነት በላቀ እምነት እና በተሻለ ማስረጃ መከላከል ይችል ዘንድ የግሪክኛ መሰረታዊ ትምህርት እንዲወስድ ጠየቀ። አብዛኛው የክርስትና እምነት በእውቀት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በአጉል እምነት፣ በወግ እና ስለ መጽሐፍ ቅዱስ በተሳሳተ እውቀት ነው ብለው የሚከራከሩ እንደ እነዚህ ምስክሮች ያሉ ቡድኖች ለሚነሡት ጥያቄዎች መልስ የምንሰጠው እንዴት ነው? ሁሉም አማኞች የመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋን የተሻለ እውቀት እንዲያገኙ ለመርዳት ጥረት ማድረግ አለብን ወይንስ በእድገትና በመንፈሳዊ ብስለት ጉዳዮች ላይ ብቻ ትኩረት ማድረግ አለብን? አባሎቻችን የቅዱሳት መጻሕፍትን የእውነት ቃል በትክክል እንዲከፋፈሉና እንዲከላከሉ ለማድረግ የቋንቋ እና የነገረ መለኮት መሳሪያዎች አጠቃቀም ሚና ምን ሊሆን ይገባል? ትንሽ እውቀት ከምንም የከፋ ነው? ብዙዎቻችን ስላመንነው ነገር ሁሉ ሊያርሙን ከሚፈልጉ ሰዎች ጋር የተደረገ ውይይት ሰለባ ሆነናል። ስለ ታዋቂው የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር “ዶ/ር. ኤክስ” ሰምተን ይሁን አይሁን በመጠየቅ፣ በእርሱ አዲስ የእግዚአብሔር ቃል መገለጥ እንዴት እንደተለወጡ በታላቅ ወኔና ሃይል ይነግሩናል። ጉዳዩ ምንም ይሁን ምን “ዶ/ር. ኤክስ” የተካነበት እና የተናገረው ነገር፣ በጉዳዩ ላይ ቁርጥ ያለ ቃልን ይወክላል። ስለ ዶ/ር ኤክስ እና በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ስላለው ሕይወትን ለዋጭ ትምህርቱ ሰምተን የማናውቅ መሆናችን በዚህ ጉዳይ ላይ የጌታን የጊዜውንና ምርጡን ትምህርት ላለማግኘት መገለልን እና አለማወቅን ያሳያል። አንተም የዶ/ር ኤክስን ሀሳብ ለተወሰነ ጊዜ ከሰማህ በኋላ በተቻለ መጠን በትህትና ውይይቱን ትዘጋለህ። እንግዲህ በይበልጥ ስታሰላስል፣ እውቀትን ከማስፋፋት ጋር በተያያዘ ካሉት ችግሮች አንዱ የአዳዲስ የስህተት ትምህርቶች፣ ኑፋቄዎችና የተለዩ ክፍሎች በፍጥነት እያደጉ መሆናቸው ትገነዘባለህ። አሁን ብዙዎች የእግዚአብሔር ምሪት እና በረከት እንደሆነ በመናገር፣ በሺዎች የሚቆጠሩ አስተማሪዎች እና ሰባኪዎች ሁሉም እንደ “ነብይ እከሌ” እና “ቢሾፕ እከሌ” ያሉ ማዕረጎችን ለራሳቸው በመስጠት በየአብያተ ክርስቲያናቱ እና በአየር ሞገዶች ላይ አዲሱ መገለጥ ያሉትን ይሰብካሉ። አብዛኛዎቹ እነዚህ አዳዲስ አስተማሪዎች ከራሳቸው ወይም ከስህተታቸው ሊጠብቃቸው ለሚችል ለማንኛውም አይነት መንፈሳዊ ስልጣን ወይም ማህበር የማይገዙ ፍፁም ነፃ
3
4
4
Made with FlippingBook flipbook maker