Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide

/ 2 0 3

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

ሰዎች ናቸው። ብዙዎች ለመንፈሳዊ ሥልጣን እና ለማስተማር የራሳቸው ግብአት ራሳቸው የሆኑበትን እና የራሳቸዉን ቃል ከጌታ እንደተሰጣቸውን እየተናገሩ ከምንም አይነት ስልጣን ነጻ የሆኑበትን ይህን ወቅታዊ ሁኔታ እንዴት ማስተካከል እንችላለን?

ቅዱሳት መጻሕፍትን ለሚያከብሩና ለሚወዱ በመቶዎች ለሚቆጠሩ የተሰጡ ምሁራን ሥራ ምስጋና ይግባውና፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ጽሑፍ ትርጉም እንድንረዳ የሚያስችለንን አስደናቂ የሆኑ ምሁራዊ መሣሪያዎችን አግኝተናል። ምሁራዊ ማመሳከሪያዎችን የመጠቀማችን አስፈላጊነት በመጽሐፍ ቅዱሳዊው ዓለም እና በእኛ ዘመናዊ ዓለም መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ እንድንችል ለመርዳት ነው። ይህም ትጉህ የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚው ትርጉሙን ጽሑፉን በዋናው አውድ ውስጥ እንደገና እንዲገነባ በማስቻል ለእግዚአብሔር ቃል የበለጠ ታማኝ እንዲሆን ይረዳዋል። የመጽሃፍ ቅዱስ አተረጓጎም መሰረታዊ መሳሪያዎች ጥሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም፣ የግሪክ እና የዕብራይስጥ መዝገበ ቃላት፣ መደበኛ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ ኮንኮርዳንስ እና የምንባብ ማመሳከሪያዎችን የሚያካትት ሲሆን ይህም በጽሑፉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉሞች ላይ ያተኩራል። እነዚህ መሳሪያዎች በትክክለኛ ቦታቸው እና ጊዜያቸው ጥቅም ላይ ሲውሉ በመጽሐፍ ቅዱሳዊው ዓለም እና እኛ ስለዚያ ዓለም ባለን ግንዛቤ መካከል ያለውን ልዩነት በማጥበብ ረገድ ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ። ከመሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ የትርጓሜ መሳሪያዎች በተጨማሪ (ማለትም፣ ጥሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም፣ የግሪክ እና የዕብራይስጥ መዝገበ-ቃላት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ ኮንኮርዳንስ እና ተዓማኒ የሆኑ የምንባብ ማብራሪያዎች) ስለ እግዚአብሔር ቃል ያለንን ግንዛቤ የሚያበለጽጉ ተጨማሪ መሣሪያዎች አሉ። እነዚህም የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ አትላስ እና የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፣ ርዕሳዊ መጽሐፍ ቅዱስ፣ የሥነ መለኮት መዝገበ ቃላት እና ሥነ-መለኮታዊ ማብራሪያዎችን ያካትታሉ። እያንዳንዱ እነዚህ ማመሳከሪያዎች የሚያተኩሩት ከቋንቋ፣ ባህል፣ ታሪክ እና ስነ-መለኮት ጉዳዮች ጀምሮ በልዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ተግዳሮቶች ላይ ነው። እንደማንኛውም አጋዥ መሣሪያ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ዋና መልእክት የሆነውን በኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት በኩል የሆነልንን መዳን በማይክድ ወይም በማያሳንስ መልኩ የጽሑፉን እውቀታችንን ለማሳደግ ልንጠቀምባቸው ይገባል። ስለ “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ውስጥ ማመሳከሪያዎችን መጠቀም” ተጨማሪ ሀሳቦችን ለመከታተል ፍላጎት ካለህ እነዚህን መጻሕፍት መመልከት ይረዳህ ይሆናል: Bruce, F. F. New Testament History . New York: Doubleday, 1969. Penney, Russell, and Mal Couch. eds. An Introduction to Classical Evangelical Hermeneutics: A Guide to the History and Practice of Biblical Interpretation . Grand Rapids: Kregel Books, 2000. Sire, James W. Scripture Twisting: Twenty Ways the Cults Misread the Bible . Downers Grove, IL: InterVarsity, 1980. Stott, John. The Contemporary Christian: Applying God’s Word to Today’s World . Downers Grove, IL: InterVarsity, 1992.

የትምህርቱን ንድፈ ሃሳብ በድጋሚ መጻፍ

4

ማጣቀሻዎች

Made with FlippingBook flipbook maker