Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide

/ 5

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

የትምህርቱ/የሞጁሉ መግቢያ

ኃያል በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ላንተ ይሁን!

በቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት መሰረት እግዚአብሔር በመንፈሰ-እስትንፋስ በተሞላው የእግዚአብሔር ቃል አማካኝነት ወኪሎቹን ያስታጥቃቸዋል። እግዚአብሔር ወደ አገልግሎት የጠራው ማንኛውም ሰው የቃሉን ይዘት ጠንቅቆ ለማጥናት፣ ለትእዛዛቱ ለመገዛት እና እውነቱን ለማስተማር ራሱን ለማስገዛት የወሰነ መሆን አለበት። እንደ ትጉህ ሰራተኛ የእውነትን ቃል በቅንነት ለመናገር እና በትምህርቱም በጌታ ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት መጣር አለበት (2ጢሞ. 2.15)። ይህ ሞጁል መጽሐፍ ቅዱስን ለመተርጎም የሚያስፈልጉትን እውነታዎች፣ መሠረታዊ ሥርዓቶችና ውጤቶች ያብራራል። የመጽሐፍ ቅዱስ እስትንፋሰ እግዚአብሔር: የመጽሐፍ ቅዱስ አመጣጥና ሥልጣን በተሰኘው የመጀመሪያ ትምህርታችን ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ አስፈላጊነትና ለዚህ ታላቅ ተግባር ለመዘጋጀት ምን ማድረግ እንዳለብን እንመለከታለን። የመጽሐፍ ቅዱስን መለኮታዊም ሆነ ሰዋዊ ገጽታ እንመረምራለን፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ዓላማ ምን እንደሆነ እንመለከታለን፤ እንዲሁም ቅዱሳት መጻሕፍት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያላቸውን ከፍተኛ ቦታ በተመለከተ የሥነ መለኮታዊ አስተሳሰባችንን በግልጽ እናቀርባለን። የእግዚአብሔርን ቃል በትክክል ለመተርጎም የሚያስፈልገውን የአኗኗር ዘይቤና የልብ ዝግጅት በተመለከተ ይበልጥ ትኩረት እንሰጣለን። በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር መንፈስ አነሳሽነት እንደተጻፈ የሚገልጸውን ሐሳብ እንዲሁም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለውን ሥልጣንና ቦታ እንመለከታለን። የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን በከፍተኛ ደረጃ እየጨመሩ ባሉበት በዚህ ዘመን ዘመናዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትችቶችን በአጭሩ እንመለከታለን፤ እንዲሁም ከቅዱሳት መጻሕፍት ጥናታችን ጋር በተያያዘ የሚነሱትን ጥያቄዎች እንመረምራለን። የመጽሐፍ ቅዱስ ስነ-አፈታት: የሶስት ደረጃ ሞዴል በተሰኘው በሁለተኛው ትምህርታችን ደግሞ በጥንታዊ እና በዘመናዊ ዓለማችን መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ወደ ቅዱሳት መጻሕፍት ጥናትህ እንድትቀርብ ለማገዝ የተነደፈውን ውጤታማ የመጽሐፍ ቅዱስ ስነ አፈታት ዘዴ እናስተዋውቃለን። የሶስት ደረጃ ሞዴል ብለን እንጠራዋለን: የመጀመሪያውን ተደራሲያን መረዳት፣ አጠቃላይ መርሆችን ማስቀመጥ እና በህይወትህ መተግበር። በዚህ ትምህርት ውስጥም ይህንን ሞዴል በመጠቀም የቅዱሳት መጻሕፍትን ክፍሎች እንመረምራለን፣ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ ውስጥ ያለውን ክፍል እንመለከታለን፣ በመጀመሪያው መልእክቱ 9.1-14 የመጽሐፍ ቅዱስ ስነአፈታት ቁልፎች በተባለው ተጨማሪ ክፍል ውስጥ የሚገኘውን ማዕቀፍ በመጠቀም ይህን ታላቅ የቅዱሳት መጻሕፍት ምንባብ በጥንቃቄና በጸሎት በመመርመር የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቃል በመጠቀም ፈቃዱን ለመረዳት ስንጥር እንዴት ታላቅ መረዳትና መነሳሳት ማግኘት እንደምንችል እንመረምራለን። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስነ ጽሑፍ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘውጎችን መተርጎም በተሰኘው ሦስተኛው ትምህርት ላይ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን ጽሑፎችና እንዴት መተርጎም እንደሚቻል እንመለከታለን። የመጽሐፍ ቅዱስ ስነ አፈታት ውስጥ የዘውግ ፅንሰ-ሀሳብን (ዣንራ ተብሎ የሚጠራውን) እንመለከታለን፣ ስለ ሀሳቡ አጠቃላይ እይታ እናቀርባለን ፣ እንዲሁም ስለዚህ ዓይነቱ ልዩ የስነ አፈታት ዘዴ ጥቂት መሠረታዊ ግምቶችን እንሰጣለን። በመቀጠልም የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘውጎችን

Made with FlippingBook flipbook maker