Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide

6 /

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

እንመለከታለን፣ ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱስን እውነተኛ ይዘት በአብዛኛው ለሚወክሉት ሁለት የስነ ጽሑፍ ዓይነቶች ልዩ ትኩረት እንሰጣለን - ትረካዊ እና ትንቢታዊ። ስለ ትረካ ጥናት (ማለትም ፣ ስለ ታሪክ ሥነ-መለኮት) እንዲሁም ስለ ትንቢታዊ እና አፖካሊፕቲክ ሥነ-ጽሑፍ አጭር ግን ጥልቅ ውይይቶችን እናደርጋለን፣ ለተለያዩ ዘውጎች ትኩረት መስጠታችን ቅዱሳት መጻሕፍትን በተሻለ ለመተርጎም እንዴት እንደሚረዳን ያሳያል። በመጨረሻም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች:- ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማመሳከሪያዎችን መጠቀም በተሰኘው አራተኛው ትምህርታችን እንጨርሳለን። አንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ ትርጉም ለመረዳት ስንሞክር ምን ዓይነት አስተማማኝ የማመሳከሪያ መሣሪያዎች እንዳሉ እንመለከታለን። ዛሬ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ የቃሉን እውቀት ለማግኘት የሚረዱትን በጽሑፍም ሆነ በሶፍትዌር መልክ ማመሳከሪያዎችን ማግኘት ይችላል። በመጀመሪያ ለጠንካራ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜ መሠረታዊ መሳሪያዎች፡ ጥሩ የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጉም፣ የዕብራይስጥ እና የግሪክ መርጃዎች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ ኮንኮርዳንስ እና የኤክሲጀሲስ ማጣቀሻዎች ላይ እናተኩራለን። በተጨማሪም የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናታችንን ሊያዳብሩ የሚችሉ ተጨማሪ መርጃዎችንም እንመለከታለን። እነዚህም የማመሳከሪያ መርጃዎች፣ ርዕስ መር መጽሐፍ ቅዱሶች፣ ማጣቀሻ መጽሐፍ ቅዱሶች እና ርዕስ መር ኮንኮርዳንስን ያካትታሉ። በተጨማሪም በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክና ልማዶች ላይ የሚያተኩሩትን መርጃዎች፡ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ኢንሳይክሎፔዲያዎች፣ አትላስ እና ሌሎች ተዛማጅ የማመሳከሪያ ጽሑፎችን እንጠቀማለን። በመጨረሻም፣ መጽሐፍ ቅዱስን ለአምልኮ፣ ለስብከት እና ለማስተማር በምትተረጉሙበት ወቅት የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎችን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያዎችን፣ የጥናት መጽሐፍ ቅዱሶችን፣ እና በአጠቃላይ ማመሳከሪያዎች ስለሚኖራቸው ሚና በመመልከት እናጠቃልላለን። መጽሐፍ ቅዱስ የራሱ የመለወጥ ኃይል እንዳለው የሚገልጸው አስደናቂ ሐሳብ የእግዚአብሔርን ቃል ጠንቅቀን እንድንማር ሊገፋፋን ይገባል። “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።” 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥16-17። በሰዎች ቃል ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር እስትንፋስ ያለው የእግዚአብሔር ቃል እኛን ለማጎልበት፣ ለማነጽ እና ለበጎ ስራ ሁሉ ብቁ እና የታጠቀን እንድንሆን በቂ ነው። በእርግጥ የእግዚአብሔር ቃል ሊሰበር አይችልም፣ አላማውን ሁል ጊዜ ይፈጽማል፣ የእግዚአብሔርም ልጆች የትም ቢሆኑ የእግዚአብሔርን መንግስት ለማስፋት በሚያደርጉት ሁሉ መልካም ስኬት እንደሚያገኙ ያረጋግጣል (ዮሐ. 10.35፣ ኢሳ. 55.8-11፤ ኢያሱ 1.8)። የእኔም ልባዊ ጸሎት መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ እና ዘላለማዊ ቃሉን የመተርጎም መርሆችን እና ልምምዶችን እንድትመረምር ይረዳህ ዘንድ፣ እነዚህ ሁሉ እና ሌሎችም በረከቶች ያንተ ይሆኑ ዘንድ ነው።

ለመታነጽ ይሆንህ ዘንድ በከፍተኛ ጉጉት፣

- ቄስ ዶ/ር ዶን ኤል ዴቪስ

Made with FlippingBook flipbook maker