Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide

/ 5 7

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ የሦስት ደረጃ ሞዴል

ትምህርት 2

ገጽ 297  1

የትምህርቱ አላማዎች

ኃያል በሆነው በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን! የዚህን ሞጁል (ትምህርት) መጽሐፍ ካነበብክ፣ ካጠናህ፣ ውይይት ካደረግህና ወደ ተግባር ከቀየርክ በኋላ የሚከተሉትን ማድረግ ትችላለህ:- • የቅዱሳት መጻሕፍትን እውነት እንድንረዳ እና በጥንታዊ እና በዘመናዊው ዓለማችን መካከል ያለውን ልዩነት ለማስተካከል እንዲረዳን የተነደፈ ውጤታማ የመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎም ዘዴ የሶስት-ደረጃ ሞዴል እንደሆነ ለማሳየት ማስረጃ መስጠት። • የሶስት-ደረጃ ሞዴል የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ፍቺን መስጠት እና ያለማመሳከሪያ ማሰላሰል፡ “በመንፈስ ነጻነት በግል ሕይወታችን ውስጥ ሊተገበሩ የሚችሉ አጠቃላይ የእውነት መርሆችን ከመጀመሪያው ሁኔታ ትርጉም በመነሳት ማግኘት።” • የእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አካል እና ስራ ውስጥ መግለጥ የፈለገውን የእግዚአብሔርን የመጨረሻ መገለጥ ትርጉም እና መልእክት ሁሉም የእግዚአብሔር ቃል ጥናት መንገዶች እንዴት እንደሚያሳዩ መግለጽ። • የሶስት-ደረጃ ሞዴል እንዴት ከቅዱሳት መጻህፍት የትርጓሜ ሰዋሰዋዊ-ታሪካዊ ዘዴ ጋር እንደሚዛመድ ያለህን ግንዛቤ ማሳየት፣ እርሱም የትርጓሜውን ግልጽ ግንዛቤ፣ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ሂደታዊ መገለጥ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ አንድነት እና የጽሑፉ ታማኝነት። • በሶስት ደረጃ ሞዴል ውስጥ ለእያንዳንዱ ደረጃ ወሳኝ የሆኑትን ምክንያቶች እንደገና ማባዛት፣ ይህም እያንዳንዱ ለምን አስፈላጊ እንደሆነ፣ ከእያንዳንዱ ጋር የተያያዙ ችግሮች፣ በእያንዳንዱ ደረጃ የሚፈለጉትን ቁልፍ አመለካከቶች፣ ከእያንዳንዱ ጋር የተያያዙ ተግባራትን፣ እንዲሁም የእያንዳንዱ እርምጃ ምሳሌ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ማሳየትን ያጠቃልላል። • በሶስት ደረጃ ሞዴል ውስጥ ለእያንዳንዱ የጥናት ደረጃ አስፈላጊ የሆኑትን የአመለካከት ዓይነቶች መለየት፡ በቅደም ተከተል ትህትና፣ ጥልቅነት እና ነጻነትን ለእያንዳንዱ ደረጃዎች ማሳየት። • 1 ቆሮንቶስ 9.1-4ን በመጠቀምና በጽሁፉ ውስጥ የተጠቀሱትን እያንዳንዱን ተግባራዊ እርምጃዎች በመከተል የሶስት ደረጃ ሞዴል ምሳሌን ማዘጋጀት። • የአንድ የተወሰነ ክፍል ጥናት ከጠቅላላው ምዕራፍ፣ ክፍል፣ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ እና በመጨረሻም በክርስቶስ ለእኛ ካለው የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት አንፃር እንዴት መከናወን እንዳለበት መመልከት። • የሶስት-ደረጃ ሞዴልን በግል በመጠቀም እያንዳንዱ ቁልፍ ደረጃዎች የፅሁፉን ትርጉም የማብራራት አላማን እና የህይወት መፅሃፍ ቅዱሳዊ መርሆችን በማግኘት የህይወታችን ለውጥ በምን አይነት መልኩ በፅሁፉ ላይ እንደሚያተኩር ማሳየት።

2

Made with FlippingBook flipbook maker