Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide
5 8 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
• የጽሑፉን የመጀመሪያ ሁኔታ በመመርመር፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሆችን በማግኘት እና የቅዱሳት መጻሕፍትን ትምህርት በሕይወትህ ላይ በትክክል ተግባራዊ ለማድረግ ዋና ዋና ነገሮችን፣ ማስጠንቀቂያዎችን እና ሂደቶችን ማወቅ።
ጥሞና
የእግዚአብሔርን ቃል ለማጥናት፣ ለመፈጸምና ለማስተማር የተዘጋጀ ልብ ዕዝራ 7፥10 — “ዕዝራም የእግዚአብሔርን ሕግ ይፈልግና ያደርግ ዘንድ፥ ለእስራኤልም ሥርዓትንና ፍርድን ያስተምር ዘንድ ልቡን አዘጋጅቶ ነበር።”
ገጽ 298 2
ልብህ በእግዚአብሔር ፊት ዝግጁ ነውን?
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ዋና ዋና ቅዱሳንን ስንመለከት አምላካችን በፊቱ የተዘጋጀውን ሰው ቃሉን በማጥናት በሕይወታቸው ውስጥ በትጋት እንዲለማመዱ እና ከዚያም የእርሱን እውነት ለሌሎች ለማካፈል እንደ ዕቃው እንደሚጠቀም ያሳያል። ምናልባትም ለዚህ ግልጽ ከሆኑት ምሳሌዎች አንዱ በብሉይ ኪዳን ታሪካዊ መጽሃፍ ዕዝራ ውስጥ ተመዝግቦ የሚገኘው እስራኤላውያን ከግዞት በኋላ ከባቢሎን ወደ ይሁዳ ስለመመለሳቸውና ስለመንፈሳዊ ሕይወታቸው መነቃቃት እና የጌታን አምልኮ በቤተመቅደስ ውስጥ ስለማቋቋማቸው የተገለጸው ነው።እስራኤልና ይሁዳ በእግዚአብሔር ላይ በሰሩት ኃጢአት ምክንያት ወደ ምርኮ ከተላኩ በኋላ በተጻፉት የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ሁሉ የጌታን አምልኮ ተገቢና ትክክለኛ በሆነ መንገድ ማምለክ ቁልፍ ጭብጥ ሆኖ እንመለከተዋለን። በእነዚህ መጻሕፍት ውስጥ ቀዳማዊ እና ዜና መዋዕል፣ ዕዝራ፣ ነህምያ፣ ሐጌ፣ ዘካርያስ እና ሚልክያስ ተካትተዋል (ምናልባትም ከ መጽሐፈ አስቴር በስተቀር)። የዕብራይስጥ ቅዱሳት መጻሕፍት ወደ አገራቸው የተመለሱት ሰዎች በጌታ ፊት በደላቸውን ለመቀበል ዝግጁና ፈቃደኞች እንደነበሩ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር በሰጣቸው ምድር ላይ መልሶ እንደሚያቋቁማቸውና እርሱን ብቻ ማምለክ እንደሚገባቸውና በመጪው መሲሕ አማካኝነት በመንግሥቱ ላይ መግዛት እንደሚችሉ እምነት እንደነበራቸው ያሳያሉ። በእርግጥ ከባቢሎን ወደ እስራኤል ምድር የተመለሱት በ538፣ 458 እና 444 ዓ.ዓ ገደማ ሦስት ጊዜ ነበሩ። ይህም በቅደም ተከተል በ605፣ 597 እና በ586 ዓ.ዓ ሕዝቡ ከእስራኤል ወደ ባቢሎን ከተሰደደበት ጊዜ ሦስት ጊዜ ከነበረው እውነታ ጋር ይዛመዳል። ተመላሾቹ የሚመሩት ፈሪሃ እግዚአብሔር ባላቸው የጌታ አገልጋዮች ሲሆን የመጀመሪያው በ538 ዓ.ዓ ነበር። በዘሩባቤል (ዕዝራ 1-6፤ ሐጌ፤ ዘካርያስ)፣ ጥረቱ ቤተ መቅደሱን እንደገና እንዲገነባ አስችሎታል። ሁለተኛው መመለስ በ458 ዓ.ዓ. በእዝራ መሪነት እና ቁጥጥር (ዕዝራ 7-10) በሰዎች ተሐድሶ እና መመሪያ ላይ፣ በመንፈሳዊ መነቃቃታቸው እና በቃል ኪዳኑ ፍፃሜ ወደ ጌታ እንዲመለሱ አስፈላጊነት ላይ ያተኮረ ነበር። በመጨረሻም ነህምያ በ444 ዓ.ዓ ሦስተኛውን የመልሶ ማቋቋም ጉዞ ያካሄደ ሲሆን ዋነኛው ሥራው የወደመውን የኢየሩሳሌምን ቅጥር መልሶ መገንባት እንዲሁም ከዕዝራ ጋር በመሆን የእግዚአብሔርን ሕዝቦች በመንፈሳዊ ሁኔታ በማደስና ቃል ኪዳኑን በመታዘዝ ወደ ጌታ እንዲመለሱ ማድረግ ነበር። በዛሬው ጊዜ ያሉ ብዙ ምሁራን ሚልክያስ የተጻፈው በነህምያ ዘመን ሳይሆን አይቀርም ብለው ያምናሉ፤ የአስቴርም መጽሐፍ የተጻፈው በዕዝራ 6 እና 7 ላይ በሚገኙት ክንውኖች ወቅት እንደሆነ ያምናሉ። በእስራኤል ታሪክ ውስጥ ይህ ወቅት ለእግዚአብሔር ስራ የተዘጋጁ ወንዶች እና ሴቶች ልጆች አስፈላጊነት ምን ያህል እንደነበረ ቁልፍ ግንዛቤዎችን ይሰጣል።
2
Made with FlippingBook flipbook maker