Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide

8 6 /

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

II. ደረጃ ሁለት፦ አጠቃላይ መርሆችን መፈለግ

ሀ. የደረጃው ትኩረት:- የእግዚአብሔርን እውነትና ለሁሉም ሰዎች ያለውን ዓላማ የሚያስተምረው ዋነኛ መልእክት፣ እውነት፣ ትእዛዝ ወይም መሠረታዊ መርህ ማግኘት

1. ጸሐፊው ሊናገር የፈለገውን ነገር በአጭሩ ተናገር።

2. ማጠቃለል የመጽሐፍ ቅዱስ ልማድ ነው።

የእንደዚህ አይነት አጠቃላይ አሠራሮች ህጋዊነት በራሱ በመጽሐፍ ቅዱሳዊው ጽሑፍ ውስጥ ተደጋግሞ ተረጋግጧል። እግዚአብሔር ሕጉን በአሥር ማጠቃለያ ብቻ ሳይሆን (ዘጸ. 20.1-17፤ ዘዳ. 5.6-21)፣ ነገር ግን ሌሎች ሰባት የሕጉን ማጠቃለያዎችንም ሰጥቷል። መዝሙር 15 የእግዚአብሔርን ህግ በአስራ አንድ መርሆች ይጠብቃል፣ ኢሳ. 33.15 በስድስት ትእዛዛት ያስቀምጠዋል; ሚክ 6.8 በሦስት ትእዛዛት ሸፍኖታል፣ ኢሳ. 56.1 የበለጠ ወደ ሁለት ትዕዛዞች ይቀንሳል; እና አሞጽ 5.4; ዕንባ. 2.4፣ እና ዘሌ. 19.2 እያንዳንዳቸው ህጉን በአንድ አጠቃላይ መግለጫ ያጠቃልላሉ። ኢየሱስ ራሱ ሕጉን በሙሉ በሁለት መሠረታዊ ሥርዓቶች በማጠቃለል ይህንኑ ወግ ቀጥሎታል:- ‘አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ ውደድ። . . . ሁለተኛው ትእዛዝ ደግሞ ከዚህ ጋር ይመሳሰላል፤ ‘ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ።’

2

~ Walter C. Kaiser. An Introduction to Biblical Hermeneutics. p. 276.

ለ. የመጽሐፍ ቅዱሳዊ መርህ ትርጓሜ

1. ቀላል መግለጫ ሰጪ ዓረፍተ-ነገር (ወይም ምሳሌያዊ አባባል) (በተረት ውስጥ ያለው የታሪኩ ሥነ ምግባር መርህ ነው) ።

2. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን ግልጽ እውነት የሚገልጽ

3. በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተደገፈ

Made with FlippingBook flipbook maker