Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide

9 6 /

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

ግንኙነት

የእግዚአብሔርን ቃል ጠንቅቆ ማወቅ የእግዚአብሔር ሰው ዋነኛና ወሳኝ ክህሎት ነው፣ ምክንያቱም እኛን ብቃት ያላቸው ሠራተኞችና የቤተክርስቲያን ታማኝ አገልጋዮች ሊያደርገን፣ ሌሎችን ለአገልግሎት ለማስታጠቅና በቤተክርስቲያን ውስጥም ሆነ ከቤተክርስቲያን ውጭ ያሉትን ለማገልገል የሚያስችለን በእግዚአብሔር መንፈስ የተጻፈው መጽሐፍ ነው (2 ጢሞ. 3.16-17)። በእግዚአብሔር ሥራዎች ስኬታማ ለመሆን ሌት ተቀን ማሰላሰል (ኢያሱ. 8) እንዲሁም ለጌታ በምታከናውናቸው ሥራዎች በሁሉም ደረጃ የምትመኘውን ፍሬያማነትና ኃይል እንድታገኝ (መዝ. 1.1-3) ቃሉን በቅንነት የመያዝ ችሎታህን አጉልተን ልንገልጽበት የምንችልበት ምንም መንገድ የለም (2ጢሞ. 2.15)። በዚህ የሶስት ደረጃ ሞዴል ትምህርት ውስጥ የተካተቱት ዋና ዋና ፅንሰ ሀሳቦች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል ፣ ስለሆነም እባክህ በትጋት እና በጥንቃቄ ከልሳቸው። ይህን ሞዴል መረዳትህ ቃሉን በትክክልና በቅንነት በምትይዝበት ጊዜ በእግዚአብሔር የተመሰገነና የማያሳፍር ሰራተኛ ሆነህ ለመቅረብ የሚያስችል እውቀትና ችሎታ እንድታገኝ ያስችልሃል። ³ የሶስት-ደረጃ ሞዴል የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ውጤታማ ዘዴ ነው የተዘጋጀው የቅዱሳት መጻሕፍትን እውነት እንድንረዳ እና በጥንታዊው እና በዘመናዊው ዓለሞቻችን መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ነው። የሶስት-ደረጃ ሞዴል ግልፅ እና አጠር ያለ ትርጓሜ “የመጀመሪያውን ሁኔታ ትርጉም በመረዳት እና በግል ሕይወታችን ውስጥ ሊተገበሩ የሚችሉትን የእውነትን አጠቃላይ መርሆች በመንፈስ ነፃነት ማግኘት” ነው። ³ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ የሚገኙትን ቃላት፣ ሐረጎች፣ አንቀጾች፣ ምዕራፎች፣ ክፍሎችና መጻሕፍት መመርመር ጠቃሚና አስፈላጊ ቢሆንም ስለ ቅዱሳን ጽሑፎች የምናገኘው ግንዛቤ በሙሉ ከመላው መጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ማለትም እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ማንነትና ሥራ አማካኝነት የገለጠልን የመጨረሻ መልእክት ትርጉም ጋር የሚስማማ መሆን ይኖርበታል። ³ የሶስት-ደረጃ ሞዴል የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ሰዋሰዋዊና ታሪካዊ ዘዴን የሚያስተጋባ ሲሆን ይህም የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም ግልጽነት፣ እግዚአብሔር በክርስቶስ ያደረገልንን ሂደታዊ መገለጥ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ አንድነትና በተለያዩ ዘውጎችና ቅርጾች ለእኛ የሚገልጸውን የቅዱሳን ጽሑፎችን ጽኑነት ያረጋግጣል። ³ ከሶስት-ደረጃ ሞዴል ጋር የተዛመደ እያንዳንዱ እርምጃ የራሱ የሆነ ዓላማ እና አመክንዮ፣ ምክንያቶች እና መሠረትና ቁልፍ አመለካከቶች አሉት፣ ይህም በተወሰነ ቅደም ተከተል እና በድርጊቶች ዝርዝር ይሟላል። ሞዴሉን ለመቆጣጠር እነዚህን እርምጃዎችና እንቅስቃሴዎች በደንብ ማወቅና መለማመድ ይኖርብናል። ³ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት የሚረዳ ወሳኝ ዝግጅት ቅዱሳት መጻህፍትን የሚያጠናው ግለሰብ ሊኖረው የሚገባው አመለካከት ነው፤ ምክንያቱም በሶስት-ደረጃ ሞዴል ውስጥ ያሉት የጥናት ደረጃዎች በቅደም ተከተል ትሕትናን፣ ጥልቀትንና ነፃነትን ይጠይቃል። ³ በክርስቶስ ጌትነት ስር የጽድቅ ባሪያዎች እንደመሆናችን መጠን ቃሉን በሕይወታችንና በአገልግሎታችን ሁሉ እንድንታዘዝ ተጠርተናል፤ ስለዚህ ሁሉም ሕጋዊ የመጽሐፍ

የቁልፍ ጽንሰ ሐሳቦች ማጠቃለያ

የመጀመሪያው አንባቢ አስፈላጊነት፡ የሶስት ደረጃ ሞዴል ቁልፍ ተርጓሚዎች የመጀመሪያዎቹ አንባቢዎች አንድን ምንባብ እንዴት ተረድተውት እንደነበር እራሳቸውን ሲጠይቁ፣ ለመመለስ የማይቻል መላምታዊ ጥያቄ ብቻ እያነሱ አይደለም (አእምሯቸውን ማግኘት ስለማንችል)። ይልቁንስ፣ ይህ በቀላሉ ወደ ብዙ ንዑስ ጥያቄዎች የመግቢያ መንገድ ነው፡ እነዚህን ቃላት በወቅቱ እንዴት ይረዱ ነበር? የትኞቹ ጉዳዮች እና ጭብጦች በጣም አስፈላጊ ነበሩ? መጽሐፍ ቅዱሳዊው ጽሑፍ ምን ዓይነት ፅንሰ-ሃሳባዊ ማዕቀፍ ያጋጥመዋል? እንደዚህ ያሉ ጥያቄዎችን ማንሳት ሁልጊዜ ፍጹም መልስ ማግኘት እንደምንችል ማረጋገጥ አይቻልም። አንዳንድ ጊዜ ጽሑፉን በራሱ ‘በመስታወት በማንበብ’ ተገቢ የሆነ መልስ ማግኘት እንችላለን። ~ Donald A. Carson. New Bible Commentary: 21st Century Edition . (electronic ed. of the 4th ed.). Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 1997.

2

Made with FlippingBook flipbook maker