Bible Interpretation, Amharic Mentor Guide

9 8 /

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

አሁን ስለ ሶስት-ደረጃ ሞዴል ያለህን ግንዛቤና በተለይ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን በሥርዓት ማጥናትን በተመለከተ ያለህን ጥያቄ ለክፍል ጓደኞችህ ማቅረብ የምትችልበት ጊዜ ነው። የራሳችን አመለካከት፣ የመረጥነው የጥናት ዘዴ፣ መንፈስ ቅዱስ፣ የማመሳከሪያ መሳሪያዎች፣ ሌሎች ክርስቲያኖች እና መሪዎች መካከል ያለው ግንኙነት ግልጽነት እና ጥበብን ይጠይቃል። ምሁራን፣ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች፣ መጋቢያንና ሰባኪዎች እንዲሁም መደበኛ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ጥያቄዎችን ለዘመናት ሲያስቡበት ኖረዋል፤ አሁን አንተም በዚህ ውይይት ውስጥ መሳተፍ ትችላለህ! መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናትህ ምን ጥቅም እንዳለው ለማወቅ ከዚህ በታች የቀረቡትን ጥያቄዎች ተጠቀምባቸው። * በዘመናዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ትችት ምክንያት የሚመጣውን ግራ መጋባትና ጥርጣሬ ከግምት በማስገባት ቅዱሳት መጻህፍትን ለማጥናት የሶስት ደረጃ ሞዴልን ጨምሮ ማንኛውንም ዘዴ ከመጠቀም መቆጠብ ይኖርብናልን? የሶስት ደረጃ ሞዴል እንኳ ቢሆን የክርስትናን መሠረታዊ ትምህርቶች እንደማያዛባና ወደ ክህደት እንደማይመራ እንዴት እናውቃለን? * እንደ ሶስት-ደረጃ ሞዴል ያሉ ዘዴዎችን መጠቀም “በራስህ ማስተዋል አትደገፍ” (ምሳሌ 3.5-6) የሚለው ሃሳብ መገለጫ ብቻ አይደለም ማለት የምንችለው እንዴት ነው? * ከፀሐይ በታች ባሉ ሁሉም ሊታሰቡ በሚችሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የተትረፈረፈ ጥናት እየተካሄደ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ሁሉም ግንዛቤዎቻችን ከመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ጋር የሚስማሙ መሆናቸውን እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን? መጽሐፍ ቅዱስን በምናጠናበት ጊዜ ‘በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ከመሰልጠን/ከማተኮር’ መራቅ የምንችለው እንዴት ነው? ተግባራዊ ምሳሌዎችን ስጥ። * የራሳችንን የግል ትርጉሞች እንደ ባለስልጣን በመውሰድ ረገድ መሪዎቻችን (ማለትም፣ ጳጳሳት፣ መጋቢያን፣ አማካሪዎች፣ ታዋቂ የክርስቲያን መሪዎች፣ ወዘተ.) ምን ሚና ይጫወታሉ? በትምህርታችን ውስጥ ያገኘነውን የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜ ከክርስትና እምነት መግለጫዎችና በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ካሉት ትምህርቶች ጋር የሚቃረን ከሆነ ልንይዘው ይገባል? አብራራ። * በቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት ሁሉ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ አጠቃላይ መርሆዎችን እንዳገኘን ከመግለጻችን በፊት ሌሎች ግኝቶቻችንንና ሐሳቦቻችንን እንዲተቹ መፍቀድ ያለብን ለምንድን ነው? አንድ ክርስቲያን ከጌታ ስለተማረው አዲስ ነገር ሲናገር ምን ዓይነት አመለካከት ሊኖረው ይገባል? * በጣም የተማረም ሰው ቢሆን እንኳ የራሱን ሃሳብ ለመመዘን እና ራሱን ከቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርት አንጻር ለመፈተሽ ፈቃደኛ ያልሆነውን ሰው እንዴት ልንይዘው ይገባል? የቤርያ ሰዎች የተዉት ምሳሌና ለጳውሎስ ትምህርት የሰጡት ምላሽ ሌሎች የሚያቀርቡትን ሐሳብ ከቅዱሳት መጻሕፍት ጋር ለማነጻጸር ፈቃደኞች መሆን እንዳለብን የሚያሳየው እንዴት ነው? (ገላ. የሐዋርያት ሥራ 17:11)?

የተማሪው ትግበራ እና አንድምታዎች

2

Made with FlippingBook flipbook maker