Bible Interpretation, Amharic Student Workbook
1 0 4 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
ከላይ የተሰጡትን የቤት ስራዎች በሚገባ ካነበብክ በኋላ ልክ እንደ ባለፈው ሳምንት አጠር ያለ ማጠቃለያ በመጻፍ በቀጣዩ ክፍለ ጊዜ ይዘህ ቅረብ፡፡ (እባክህ በዚህ ትምህርት መጨረሻ ላይ የሚገኘውን “የንባብ ማጠናቀቂያ ገጽ” ተመልከት)፤ አሁን በቀጣይ ስለምትሰራው ኤክሴጄቲካል ፕሮጀክት የንባብ ክፍል የምትመርጥበትና ስለ ሚኒስትሪ ፕሮጀክትህ የምታስብበት ጊዜ ነው፡፡ እነዚህን ውሳኔዎች ለማድረግ አትዘግይ፤ ቶሎ መወሰንህ ለዝግጅት በቂ ጊዜ እንዲኖርህ ያደርጋል፡፡ በዚህ ትምህርት ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም በዋናው እና በመጀመሪያው አውድ ውስጥ በቁም ነገር ለማየት፣ በጽሑፉ ውስጥ የተካተቱትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሆች ለማወቅ እና ከዚያም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የተሰጡ መመሪያዎችን በትጋት በሕይወታችን ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ የተነደፈውን የሶስት ደረጃ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ሞዴልን ተንትነናል። አሁን በሚቀጥለው ትምህርት ደግሞ የዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ሞዴል በመጠቀም በቅዱስ መጽሐፋችን ማለትም በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የሚገኙትን የበለጸጉ፣ የተለያዩና አስደናቂ የሆኑ መጻሕፍት ስናብራራ የሥነ ጽሑፍ ዓይነቶችን ወይም ዘውጎችን አስፈላጊነት እንመለከታለን። ለዘውግ ጥናት ትኩረት መስጠቱ ስለሚያስገኛቸው ጥቅሞች አጠቃላይ እይታ እናቀርባለን እንዲሁም የዚህ ዓይነቱ ልዩ የስነ አፈታት ዘዴ መሰረታዊ ቅድመ-ሁኔታዎች ጎላ አድርገን እናቀርባለን ።
ሌሎች የቤት ስራዎች
ለቀጣዩ ትምህርት መዘጋጀት
2
Made with FlippingBook - Online Brochure Maker