Bible Interpretation, Amharic Student Workbook
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት እንደ የቅዱሳት መጻሕፍት ግልጽ ምስክርነት አባባል፣ እግዚአብሔር ወኪሎቹን እስትንፋሰ እግዚአብሔር በሆነው የእግዚአብሔር ቃል፣ በቅዱሳት መጻሕፍት አማካኝነት ያስታጥቃቸዋል። እግዚአብሔር ወደ አገልግሎት የጠራው ማንኛውም ሰው ይዘቱን ጠንቅቆ ለማወቅ፣ ለትእዛዛቱ ለመገዛት እና እውነትን ለማስተማር ራሱን ለማስገዛት የወሰነ መሆን አለበት። እንደማያሳፍር ሰራተኛ የእውነትን ቃል በቅንነት ለመያዝ እና በትምህርቱም በጌታ ዘንድ የማይነቀፍ ይሆን ዘንድ መጣር አለበት (2ጢሞ. 2.15)። በዚህ ኮርስ ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጓሜ አስፈላጊነት እና ይህን ታላቅ ተግባር ለመፈፀም ምን እንደሚያስፈልግ እንመለከታለን። የመጽሐፍ ቅዱስን ሁለቱንም መለኮታዊ እና ሰዋዊ ገፅታዎች እንመረምራለን፣ እንዲሁም ለቅዱሳት መጻህፍት ጥናትህ እንዲረዳህ በጥንታዊው እና በዘመናዊው አለማት መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ የተቀየሰ ውጤታማ የመጽሐፍ ቅዱስ የትርጓሜ ዘዴን እናስተዋውቃለን። በተጨማሪም፣ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ አተረጓጎም ውስጥ የስነ-ጽሑፋዊ ዓይነቶችን አስፈላጊነት እናሳያለን፤ የአንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጽሑፍን ትርጉም ለመረዳት በምንሞክርበት ጊዜ ልንጠቀም የምንችላቸውን በርካታ ዓይነት ጠንካራ ምሁራዊ ማመሳከሪያ መሳሪያዎችንም እንቃኛለን።
ቄስ ዶ/ር ዶን ዴቪስ ፣ (ፒኤችዲ፥ አዮዋ ዩኒቨርሲቲ) የዎርልድ ኢምፓክት አገልግሎት አካል የሆነው የኧርባን ሚኒስትሪ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ናቸው። እንዲሁም የዎርልድ ኢምፓክት ከፍተኛ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ያገለግላሉ።
TUMI በዓለም ዙሪያ ቤተክርስቲያን የመትከል እንቅስቃሴዎችን በማመቻቸት መንግሥቱን በከተማ ድሆች መካከል ለማስፋፋት መሪዎችን በማስታጠቅ የሚያገለግል አገልግሎት ነው።
ዎርልድ ኢምፓክት የአሜሪካን የከተማ ድሆችን በወንጌል በማስታጠቅ ፣ በማስታጠቅ እና በማጎልበት የቤተክርስቲያን ተከላ እንቅስቃሴዎችን ለማመቻቸት የቆረጠ የክርስቲያን የሚሽን ተቋም ነው። የእኛ ራዕይ አብያተ ክርስቲያናትን የሚተክሉ እና አገር በቀል የቤተክርስቲያን ተከላ እንቅስቃሴዎችን የሚጀምሩ የከተማ መሪዎችን መመልመል ፣ ማስታጠቅ እና ማሰማራት ነው።
www.worldimpact.org • www.tumi.org
Made with FlippingBook - Online Brochure Maker