Bible Interpretation, Amharic Student Workbook

1 2 8 /

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

3. ማንኛውም ምሳሌ የእግዚአብሔርን ታላቅነትና ጥልቅነት ሊገልጸው አይችልም።

4. የእግዚአብሔር የዘውግ አጠቃቀም እራሱን ወይም ስራውን እስከ የስድ-ዓረፍተ-ነገር ሳይቀንስ የምስጢርን ብልጽግና ለመግለጥ የሚደረግ ሙከራ ነው።

IV. የመጽሐፍ ቅዱስ ዘውጎች ጥናት ጠቀሜታ

ሀ. ጸሐፊው በመጀመሪያ በቃላቱ እና በቅጾቹ ለማስተላለፍ ያሰበውን ለማወቅ ያስችለናል ።

ለ. ይህም ነፍሳችንን ያነቃዋል:: እግዚአብሔር በአለም (በታወቀው) እና በእግዚአብሔር እውነት (በማይታወቀው) መካከል የፈጠራ ግንኙነቶችን በማድረግ እንድናድግ ያደርገናል።

ሐ. ይህም ለሕይወት ያለንን አድናቆት ያበለጽግልናል። እግዚአብሔር ወደ “ተተኪነት ሕይወት” ይጎትተናል፣ የሌሎችን ተጨባጭ ሰብዓዊ ተሞክሮ እንድንለማመድ ያደርገናል፣ በትግላቸውም፣ በተስፋቸው እና በፈተናዎቻቸው ውስጥ እንድንሳተፍ ይጠይቀናል (አንተ እዚያ ነህ) ።

3

መ. ልባችንን ያስደስታል:: እግዚአብሔር በሥነ ጽሑፋዊ ጥንቅሮች ውበትና ጥበብ ያድሰናል።

ሠ. አእምሯችንን ያበራል። እግዚአብሔር ቃሉን ከዓለም አስተሳሰብና አኗኗር በተለየ መልኩ እንድናውቅ ይገፋፋናል፤ እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀት እንድንመረምር ይጋብዘናል።

ቅዱሳት መጻሕፍትን መንፈስ ቅዱስ በሰጠን መልክ ስናጠና እግዚአብሔር ወሰን የሌለው ጠቢብ አምላክ መሆኑን እናገኛለን፣ ሁልጊዜም እርሱን በምናስበው ሳጥን ወይም ፅንሰ ሀሳብ ውስጥ ለማስገባት ከምናደርገው ሙከራ በላይ ነው!

Made with FlippingBook - Online Brochure Maker