Bible Interpretation, Amharic Student Workbook
1 5 6 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
ምደባዎች
2 ጢሞቴዎስ 3:14-17
የቃል ጥናት ጥቅስ
ለክፍል ለመዘጋጀትና የሚቀጥለውን ሳምንት የምንባብ ምደባ ለማግኘት www.tumi.org/books ን ጎብኝ ወይም መምህርህን ጠይቅ።
የንባብ መልመጃ
እንደተለመደው ለሳምቱ የተሰጠውን የትምህርት ማጠቃለያ የሰራህበትን የንባብ መልመጃ ይዘህ መቅረብ ይጠበቅብሃል። በተጨማሪም ለምትሰራው ኤክሴጄቲካል ፕሮጀክት ምንባብ መርጠህ፥ ለሚኒስትሪ ፕሮጀክትህ ደግሞ ፕሮፖዛል አዘጋጅተህ አቅርብ።
ሌሎች የቤት ስራዎች
በዚህ ትምህርት በመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ውስጥ የዘውግ ጥናትን ምንነት መርምረናል። እንዲህ ዓይነቱ ጥናት መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት ልዩ ልዩ የሥነ-ጽሑፍ አይነቶችን ማካተቱን እንደሚገነዘብ አይተናል፣ እነዚህም ቅጾች በራሱ በስነ-ጽሑፍ ህጎች መሠረት መተርጎም እንዳለባቸው ተከራክረናል። የዘውግ ጥናት የሚጀምረው ስለ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ልክ እንደ ሌሎች የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች እግዚአብሔር ቃሉን ለእኛ ለማስተላለፍ እንደተጠቀመባቸው ሕጎች ባሉት የስነ ጽሑፍ ደንቦች እና መርሆዎች የሚገዛና የሚመራ መሆኑን በመገንዘብ ነው። በተለይም ሁለቱን ትረካዊ እና የትንቢት መጻሕፍትን ተመልክተናል፣ ስለዚህም ለአንዳንድ ህጎች የምናደርገው ጥንቃቄ የተሞላበት ትኩረት ለሰው ልጅ መሰረታዊ ልምምዳችን ያለንን እይታ እንዴት እንደሚያጎለብት እና የእግዚአብሔርን ሚስጢር ባለጠግነት እና በአለም ላይ ያለውን ስራው ምን ያህል እንደሚገልጥ አይተናል። በሚቀጥለው ትምህርታችን፣ የጽሑፉን ትርጉም ለመረዳት በምንሞክርበት ጊዜ የጥናታዊ መሳሪያዎች እና ግብዓቶች ሚና ላይ በማተኮር ይህንን ሞጁል እንጨርሳለን። የእግዚአብሔር ቃል ለሚማር ተማሪ ትምህርቱን ለማሻሻል የሚረዱ በርካታ አስደናቂ የጽሑፍ እና የዲጂታል መሳሪያዎች ይገኛሉ፣ በሚቀጥለው ትምህርታችንም የእነዚህን መሳሪያዎች መኖር፣ አላማ እና ውጤታማ ለሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ስለሚያስገኙት ጥቅም እንወያያለን።
ለቀጣዩ ትምህርት መዘጋጀት
3
Made with FlippingBook - Online Brochure Maker