Bible Interpretation, Amharic Student Workbook
/ 1 6 3
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
እውቂያ
ለተራበ ልብ ተስማሚ የሆኑ መሳሪያዎች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ቀለል ያለ አመለካከትን የሚይዙ (ማለትም፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ሥነ ጽሑፋዊ ተፈጥሮ ችላ የሚሉ፣ ስለዚህም ለሥነ ጽሑፍ ሕጎች እና ደንቦች ተገዢ የሆኑ) ትኩረታቸው በዘውግ ጥናትና ምሁራዊ ዘዴዎች አጠቃቀም ላይ በጣም አስቸጋሪ ሆኖ ያገኙታል። ጌታ ኢየሱስን ከሚወድና ከሚያምን ደቀመዝሙር እና የእግዚአብሔርን ቃል ለማመን እና ለመታዘዝ በማሰብ ለማንበብ ከሚጥር ተራ ሰው መጽሐፍ ቅዱስ መገፋቱ በትክክል ያሳስባቸዋል። እነሱ የግሪክ ቋንቋ ሊቃውንት አይደሉም፣ እና ሁሉንም የመጽሐፍ ቅዱስ መርሆዎች እና ደንቦች እንደ ስነ-ጽሑፍ ፈጽሞ መረዳት አይችሉም። የቅርብ ጊዜ መዝገበ ቃላት ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ማግኘት አይችሉም። የእግዚአብሔርን ቃል ለመረዳት ባላቸው ትህትና እና ለመንፈስ ቅዱስ ባላቸው ክፍት ማንነት ተድግፈዋል፣ በመካከላቸውም ቃሉን ሲያገለግል ለነበረው ለቤተክርስቲያናቸው መጋቢ አመራር ራሳቸውን በደስታ አስገዝተዋል። እንዲህ ዓይነቱ ግልጽነት፣ ትህትናን እና በታማኝነት የሆነ የቅዱሳት መጻሕፍት አጠቃቀም ለክርስቲያን መሪም በቂ አይደለምን? በአጋዥ መሳሪያዎች እና ሃብቶች ላይ ማተኮር የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜያችንን በጣም ውድ በሆኑና ሚሊዮኖች ለማግኘት እና/ወይም ለመረዳት በማይችሏቸው መሳሪያዎች ላይ ጥገኛ አያደርገውም? እንግዲህ ምሁራዊ መሳሪያዎች በመጽሐፍ ቅዱሳዊ አተረጓጎም ውስጥ የሚኖራቸው ጠቀሜታ ምን ሊሆን ይችላል፣ በትክክለኛውስ መንገድ እንዴት ልንጠቀምባቸው እንችላለን? የተናጥል የግለሰብ መርጃዎች አጠቃቀም እና በቤተክርስቲያን የማስተማር ስጦታ ስኮላርሺፕ እና ምሁራዊ አጋዥ መሳሪያዎች ብዙ አስቸጋሪና ከባድ የጽሑፍ ክፍሎችን የመረዳት ችሎታችንን በእጅጉ ሊያጎለብቱ ቢችሉም፣ የእግዚአብሔርን ቃል ትርጉም ለማወቅ በቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉት ህያው የመንፈስ ስጦታዎች ጋር የሚመሳከሩ መሆናቸውን መጠየቅ አለብን። በዛሬው ጊዜ ለብዙ የፕሮቴስታንት ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ የግል መጽሐፍ ነው፤ የራሳቸው የግል ጥናት እና የአምልኮ ሥርዓት መጽሐፍ ነው። ብዙ ጊዜ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን ከመንፈስ ስጦታዎችና ከቤተክርስቲያን የተነጠለ ቃል አድርገው ያስባሉ። በራሳቸው ቤተክርስትያን ውስጥ ባሉ የመንፈስ ስጦታ ባላቸው ወንዶችና ሴቶች ላይ አይተማመኑም፣ ነገር ግን አምነው የተቀበሉትን የሚያስተምሩ ማመሳከሪያዎችን፣ ሀብቶችን እና ማጣቀሻዎችን ይመርጣሉ። በምናምንባቸው የትምህርት ዓይነቶች እና ትርጓሜዎች ላይ ያተኮሩ መምህራንን በሕዝብ መስክ ውስጥ መመልከት የተለመደ ነው፣ እና “እከሌ” ወይም “እከሊት” ስለ ድነት፣ ቤዛነት፣ ፈውስ ወይም ስለማንኛውም ወቅታዊ ትኩስ ርዕሰ ጉዳይ ምን እንደሚሉና እናውቃለን። በቤተ ክርስቲያን ሥልጣን በሚሰጡት ትርጉሞች ላይ የበለጠ የሚያተኩሩ አንዳንዶች ከቤተ ክርስቲያን የመጋቢነት ሥልጣን ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ማመሳከሪያዎችን መጠቀም መከፋፈልን፣ ልዩነትን አልፎ ተርፎም ኑፋቄን ሊያስከትል እንደሚችል ይጠቁማሉ። እያንዳንዱ ክርስቲያን ለመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜ ራሱ ለራሱ ባለሥልጣን ከሆነ እንዴት የክርስትና እምነት ምን እንደሆነ በትክክል መረዳት እንችላለን? በማለት ይከራከራሉ። አጋዥ ማመሳከሪያዎችን ስለ ጠቀምን እና ስለ አንድ ቤተክርስትያንን ወይም የማህበረሰብን የማስተማር ስጦታ በምን መልኩ እውቅና ትሰጣለህ? በጣም ጠቃሚ የሆነው የራሳችን የግል ጥናት ወይስ በጉባኤ ውስጥ ያለን ቦታ?
1
2
4
Made with FlippingBook - Online Brochure Maker