Bible Interpretation, Amharic Student Workbook
1 8 2 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
ኮንኮርዳንስ እና ተዓማኒ የሆኑ የምንባብ ማብራሪያዎች) ስለ እግዚአብሔር ቃል ያለንን ግንዛቤ የሚያበለጽጉ ተጨማሪ መሣሪያዎች አሉ። • እንዴት እንደምንጠቀም ልንማርባቸው የሚገቡ ተጨማሪ መሳሪያዎች የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ አትላስ እና የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፣ ርዕሳዊ መጽሐፍ ቅዱስ፣ የሥነ መለኮት መዝገበ ቃላት እና ሥነ-መለኮታዊ ማብራሪያዎችን ያካትታሉ። • የማጣቀሻ መርጃዎች የሚያተኩሩት በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜዎች ውስጥ አንድ የጋራ ርዕስ ወይም ጭብጥ ማዕከል በሚጋሩ የተለያዩ ጽሑፎች እና ምንባቦች ግንኙነት ላይ ነው (ለምሳሌ፣ ርዕሳዊ መጽሐፍ ቅዱሶች፣ የማጣቀሻ መጽሐፍ ቅዱሶች፣ እና ወቅታዊ መመሪያዎች እና ኮንኮርዳንስ)። እነዚህ በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ጽሑፎችን አንድ ላይ እንድናጣምር ቢረዱንም፣ ጥቅሶችን ስናገናኝ የአውድ ስህተቶች እንዳንሠራ መጠንቀቅ አለብን፣ እና ሁልጊዜ አርታኢዎች አግባብ ወይም ትክክል ያልሆኑ አይነት ግንኙነቶችን ወይም ትሥሥሮችን ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ልብ በል። • አንዳንድ መሳሪያዎች ስለ መጽሐፍ ቅዱሳዊው ዓለም ታሪክ፣ ባህል፣ ማህበራዊ ልማዶች፣ ህዝቦች እና አካላዊ ሁኔታ ዳራ ይሰጣሉ፤ እነዚህም የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ኢንሳይክሎፔዲያዎች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ አትላሶች እና የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች፣ እና ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪክ እና ልማዶች ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ያካትታሉ። እነዚህ መሳሪያዎች በጽሁፉ አለም ላይ አስገራሚ መጠን ያለው መረጃ ሊሰጡ ይችላሉ፣ ነገር ግን ታሪካዊ መረጃዎችን እና የፅሁፉን ትክክለኛነት መተርጎምን ለመለየት በጥንቃቄ መነበብ አለባቸው። • ሌሎች መሳሪያዎች በተለይ በመጽሐፉ ላይ ስለ ደራሲው፣ ስለ ተጻፈበት ጊዜ እና ሁኔታ እና አንዳንድ የትርጉም ልዩ ቋንቋ አጠቃቀሞችን እና የምንባብ ጥናት (ምልክት፣ ዘይቤ ፣ ምሳሌያዊ ቋንቋ ፣ ወዘተ) ቅድመ መረጃ ለማግኘት ጠቃሚ ናቸው። እነዚህ መሳሪያዎች የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎችን፣ የጥናት መጽሐፍ ቅዱሶችን እና ሥዕላዊ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ መምሪያዎችን ያካትታሉ። በእንደዚህ አይነት ማመሳከሪያዎች ውስጥ ያሉትን አመለካከቶች ስንመዝን መጠንቀቅ አለብን፣ ሃሳቦቹ የአርታኢዎቹ መግለጫዎች እንጂ የጽሑፉ የራሱ ሃሳቦች እንዳልሆኑ መገንዘብ ያስፈልጋል። • ማብራሪያዎች የአንድን የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ትርጉም ከአንድ መጋቢ፣ ምሁር ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚ እይታ አንጻር ለመተርጎም የሚረዱ ናቸው። ለጥናታችን አጋዥ የሚሆኑ አራት ዋና ዋና የማብራሪያ ዓይነቶች አሉ፡ የጥሞና፣ የአስተምህሮ፣ የምንባብ/ክፍል ጥናት እና የስብከት ዝግጅት (ማለትም፣ ሰባኪዎችና አስተማሪዎች ስብከቶችን እንዲያቀርቡ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን እንዲያዘጋጁ የሚያግዙ)። ማብራሪያዎች ስለ ጽሑፉ ያለንን እውቀት በከፍተኛ ደረጃ ሊያሳድጉ ቢችሉም፣ እኛ በራሳችን ጽሑፉን ለማጥናት የምናደርገውን ጥረት ፈጽሞ መተካት የለባቸውም። • እነዚህን መሰረታዊ እና ተጨማሪ መሳሪያዎች በሁለቱ ዓለማት: በጽሁፉ አለም እና በዘመናዊው አለም፣ መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ እንዲረዱን በትክክል እንጠቀማቸዋለን። የቅዱሳት መጻሕፍትን ምስክርነት የሚክድ ወይም የሚቃረን የማንኛውም አስተርጓሚ ማብራሪያ ወይም መላ ምት ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም። ስለ ክርስቶስ ማንነት እና
4
Made with FlippingBook - Online Brochure Maker