Bible Interpretation, Amharic Student Workbook
/ 2 0 1
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
በትንሽ ቡድን፣ ከጓደኛህ ወይም ከአማካሪህ ጋር፣ ከመጋቢህ ጋር፣ ወይስ በቤተ ክርስቲያን ነው? ቋሚና ትኩረት ያለው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲኖርህ በጊዜ ሰሌዳህ ላይ ምን ዓይነት ለውጦችን ማድረግ ይኖርብሃል? * የጥናትህን ፍሬ የምትመዘግበው እንዴት ነው – በኮምፒውተር፣ በእጅ በተፃፉ ማስታወሻዎች፣ ወይስ በሌላ መንገድ? አንድ ጥናት ከጨረስክ በኋላ ማስታወሻዎችህን እንዴት ለማከማቸት እና ሲያስፈልግህ አውጥተህ ለመጠቀም የሚያስችል ስርዓት አለህ? * ለመረዳት አስቸጋሪ ምንባብ ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሲያጋጥምህ ለመረዳት ወደሚያግዙህ ሌሎች የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍሎች ትሄዳለህ ወይስ ወዲያው ወደ ማብራሪያዎችና ወደ መዝገበ ቃላት ትሄዳለህ? ይህስ ጥሩ ልማድ ነው ወይስ አይደለም? አብራራ። * በግል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትህ ማመሳከሪያዎችን ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመጠቀም ከፈለግህ ልታዳብረው የሚገባህ አንድ ዋና አመለካከት ምንድን ነው? አብራራ። ከገጹ ወደ ፑልፒት (በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ)። በቅርቡ በማደግ ላይ በምትገኝ የከተማ ቤተ ክርስቲያን አንድ መጋቢ ከዋና መጋቢነት ቦታው ተነስቶ ነበር ምክንያቱ ደግሞ እርሱ ስብከቶቹን ምንም አይነት አርትዖት፣ ማጣቀሻ እና ማብራሪያ ሳይጠቀም እንዲሁ እንዳለ ከመጽሐፍ እያወሰደ ይሰብክ ስለነበረ ነው። የሽማግሌዎች ቦርድ በዚህ በጣም ተጨንቆ ስለነበር በቤተ ክርስቲያን የሚያከናውነውን አገልግሎት እንዲያቆም አስፈላጊ ሆኖ ስለተሰማቸው በትምህርታዊ ጉዳዮች ሳይሆን በመንፈሳዊ ጉዳዮች ምክንያት ከአገልግሎት አገዱት። ከጌታ የተቀበለውን ትኩስ፣ ጥሩ እና ትክክለኛ ቃል ለምእመናን እና ለህዝቡ መስጠት ሲገባው ቃል በቃል የሌላን ሰው ሀሳብ እንደራሱ አድርጎ ሲያቀርብ ይህ ስለ መንፈሳዊ መሪነት ምን ይጠቁማል ሲሉ ተከራክረዋል። ስለዚህ ሁኔታ ምን ታስባለህ — በሌሎች ማመሳከሪያዎች እና ሀብቶች ላይ መደገፍ ብዙ ክርስቲያን መሪዎችን ከጌታ ዘንድ አዲስ ቃል ለጉባኤዎቻቸው እንዳያደርሱ ሰነፎች አድርጓቸዋል? ይህ የበርካታ ማመሳከሪያዎች እንደልብ መገኘት ለክርስቲያን መሪዎች የራሳቸውን የጥናት ደረጃ እና መሰጠት ችላ እንዲሉ እና በቀላሉ ከሌሎች ያገኙትን ዓይነት ምግብ የሚያመነዥጉ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል? እውቀት ያስታብያል በሩቅ የሚገኝ ሴሚናሪ ወይም የድህረ ምረቃ ትምህርት ቤት ሳይቀር በደስታ የተቀበለው ውድ፣ ትሁት እና ለጌታ የተቃጠለ፣ ጌታም እርሱን እንደሚጠቀመው ተስፋ የተጣለበት ወጣት ታሪክ ያላጋጠመው ማን አለ? ከአራት ወይም ከአምስት ዓመታት በኋላ ፍጹም በተለየ መንፈስና አጽንዖት ለአገልግሎት ይመለሳሉ። ቀድሞ አጽንዖት ይሰጣቸው ከነበሩ ነገሮች ይልቅ (ለምሳሌ እግዚአብሔርን መውደድ፣ ነፍሳትን መውደድ፣ በአምልኮ ውስጥ የእግዚአብሔርን መገኘት መፈለግ፣ በእግዚአብሔር ቃል ጥልቀት እና ኃይል መደሰት፣ ወዘተ.)፣ አሁን ከባድ ሥነ-መለኮታዊ ጽንሰ-ሐሳቦች ላይ መወያየት ይፈልጋል። በጉባኤው ውስጥ በጣም የተማሩ ሰዎች ብቻ የሚያውቋቸውን ቃላትና ሀረጎች በመጠቀም ትምህርቱ በእንባና እግዚአብሔርን በመናፈቅ የተሞላ ሳይሆን ጥቃቅን እና አስፈላጊ ባልሆኑ የሥነ
ጥናቶች
1
4
2
Made with FlippingBook - Online Brochure Maker