Bible Interpretation, Amharic Student Workbook
2 6 2 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
አባሪ 29 ትረካ (ታሪክ) እንዴት እንደሚተረጎም ዶን ኤል ዴቪስ
ሁሉም ታሪኮች የተለየ ቅርጽ አላቸው እና የታሪኩን እውነት፣ ታሪካዊም ሆነ ምናባዊ፣ ሀይለኛ፣ ፈታኝ እና አዝናኝ በሆነ መልኩ ለመለማመድ የሚያስችሉ በርካታ አካላት አሏቸው።
የትረካ ጥናት አካላት
I. የታሪኩን መቼት በልዩ ጥንቃቄ ልብ ይበሉ።
መ. ቦታ፡- ታሪኩ የሚካሄደው በጂኦግራፊያዊ ሁኔታ የት ነው?
ለ. አካላዊ አካባቢ፡ ዝርዝሮች በአካል ምንድናቸው?
ሐ. ጊዜያዊ (ጊዜ) መቼት፡ የታሪኩ የጊዜ ክፍሎች ምንድናቸው?
መ. የባህል-ታሪካዊ አከባቢዎች፡ ምን አይነት የባህል ወይም የታሪክ ዝርዝሮች ይገኛሉ?
II. የታሪኩን ገጸ ባህሪያት ይለዩ።
ሀ. የታሪኩ ዋና ገፀ-ባህሪያት እነማን ናቸው? “ጀግናው” እና “ወራዳው”?
ለ. የገጸ ባህሪያቱ ድርጊቶች፣ ንግግሮች እና ክስተቶች ትክክለኛ ቅደም ተከተል እና ዝርዝሮችን ልብ ይበሉ።
Made with FlippingBook - Online Brochure Maker