Bible Interpretation, Amharic Student Workbook

/ 5 3

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት

ስለ የመጽሐፍ ቅዱስ አነሳሽነት:- የመጽሐፍ ቅዱስ አመጣጥና ሥልጣን ተጨማሪ ሀሳቦችን ለመከታተል ፍላጎት ካለህ እነዚህን መጻሕፍት መመልከት ይረዳህ ይሆናል: Bacote, Vincent, Laura C. Miguelez, and Dennis L. Okholm. Evangelicals & Scripture: Tradition, Authority and Hermeneutics . Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 2004. Barton, John. People of the Book: The Authority of the Bible in Christianity . Louisville, KY: Westminster John Knox Press, 1989. Bruce, F. F. The Canon of Scripture . Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 1988. ------. The New Testament Documents: Are They Reliable? Grand Rapids: Eerdmans Publishing Company, 2003. የቅዱሳት መጻሕፍት አመጣጥ እና አነሳሽነት አስተምህሮ ለሌሎች በአገልግሎታችን ላይ ወዲያውኑ ተግባራዊ ይሆናል። በእግዚአብሔር ቃል ኃይል ላይ መተማመን አለመቻል በማንኛውም መንገድ ምን እንደምትሰብክ፣ ለማን እንደምትሰብክ እና ከቃሉ አገልግሎት በምትጠብቀው ነገር ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል። በእግዚአብሔር የተተነፈሱ ቅዱሳት መጻሕፍትን በተመለከተ የእነዚህን ጠቃሚ እውነቶች መሻሻሎች አሁን ጊዜ ወስደህ ከምታገለግልበት እና ከምታስተምርበት አካባቢ ጋር ተጨባጭ እና ተግባራዊ የአገልግሎት ግንኙነት ለመፍጠር ሞክር። በዚህ ትምህርት ውስጥ በእነዚህ እውነቶች ላይ ስትወያይ እና ስታሰላስል፣ ምናልባት አንዳንድ ፅንሰ-ሀሳቦች ለራስህ የህይወት ጉዞ እና አገልግሎት ጥልቅ ትርጉም ያላቸውና በዚህ በሚቀጥለው ሳምንት ተጨማሪ ጸሎት፣ ማሰላሰል እና ጥናት የሚያስፈልጋቸው ሆነው አግኝተሃቸው ይሆናል። የቅዱሳት መጻሕፍትን ሥልጣንና አነሳሽነት በተመለከተ መንፈስ ቅዱስ ለአንተ የሚሰጠውን ልዩ መመሪያ፣ የተስፋ ቃሎቹን ስትቀበል፣ ትእዛዛቱን ስትጠብቅ፣ እና ስለ እግዚአብሔር፣ ስለ ልጁ እና ስለ መንግሥቱ ያለውን ሃሳብ ስትመለከት የሚሰጠውን መተማመን መርምር። በመማር ልምምድህ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው ነገር በክፍል ውስጥ ለተማሪዎችህ ግልጽና በትኩረት የተደረገ ምልጃ እና ልመና ማድረግህ መሆን አለበት። በወቅቱ ከተጋራችሁት ልዩ ልዩ እውነቶች፣ ተግዳሮቶች እና ፍላጎቶች አንጻር፣ ለስራ ባልደረቦችህ ፍላጎቶች እና ጉዳዮች በመጸለይ ጊዜህን አሳልፍ። የእግዚአብሔርን እውነት በሕይወታችን ውስጥ ሕያው ለማድረግ የታማኝነት ጸሎት ያለውን ኃይል ፈጽሞ አቅልለህ አትመልከት። በእውነት መለወጥ እና እውነትን የራሳችን ማድረግ የምንችለው መንፈስ ቅዱስ ማስተዋልን እና ጸጋን እንደሰጠን መጠን ብቻ ነው (1ቆሮ. 2.9-16)።

ማጣቀሻዎች

1

የአገልግሎት ግንኙነቶች

ምክርና ጸሎት

Made with FlippingBook - Online Brochure Maker