Bible Interpretation, Amharic Student Workbook
6 4 /
የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-አፈታት
የቪድዮ ሴግመንት 1 ዝርዝር
I. የሶስት ደረጃ ሞዴል የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ዘዴ ትርጉሙ፣ ዓላማው፣ አካላቱና ጥቅሞቹ
ሀ. ትርጓሜ፡- “የመጀመሪያውን ሁኔታ ትርጉም በመረዳት እና በግል ሕይወታችን ውስጥ ሊተገበሩ የሚችሉትን የእውነትን አጠቃላይ መርሆች በመንፈስ ነፃነት ማግኘት” ነው ።
1. የዋናውን ሁኔታ ትርጉም ለመረዳት፡ የመጀመሪያው እርምጃ ጽሑፉ በዋናው አውድ ውስጥ ምን ማለት እንደሆነ በመረዳት ላይ ያተኩራል።
2. የእውነትን አጠቃላይ መርሆዎች እንድናገኝ፤ ሁለተኛው ደረጃ በዛሬው ጊዜ ላሉ አማኞች የሚወሰዱና የሚተገበሩ የመጽሐፍ ቅዱስ መርሆችን ከጽሑፉ ላይ በማውጣት ላይ ያተኩራል።
2
3. ይህ በግለሰባዊ ሕይወታችን ውስጥ በመንፈስ ነፃነት ውስጥ ሊተገበር ይችላል: ሦስተኛው ደረጃ የእውነትን መርህ በግለሰባዊ ሕይወታችን ውስጥ በመንፈስ ኃይል ተግባራዊ ማድረግ ነው.
ለ. ዓላማ
1. ደራሲው በመጀመሪያው ጽሑፍ ውስጥ ምን ማለቱ እንደሆነ ለማወቅ
2. የቅዱሳን መጻሕፍትን ትምህርት የሚያጠቃልሉና ለሁሉም የሚጠቅሙትን የእግዚአብሔርን ጥበብና ማስተዋል የሚገልጹ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶችን መፈለግ
3. እምነታችንንና ልማዶቻችንን መለወጥና ሕይወታችንን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ካሉት እውነቶች ጋር ማስማማት
Made with FlippingBook - Online Brochure Maker