Church PLANT Manual, Amharic Edition
ክፍል 4፥ ሁሉንም ነገር በጋራ ማድረግ (ማቀናጀት) • 101
ትምህርት 11 የራሳችሁን ስልት ማበጀት
ከዚህ ቀደም በነበሩት ትምህርቶች እንደተመለከትነው የኢቫንጄል ትምህርት ቤት የተከላ መርሖችን ቤተ ክርስቲያናችሁ በምታገለግላቸው ማኅበረ ሰቦች ዐውድ ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ነው። በዚህ ትምህርት ደግሞ በወርለድ ኢምፓክት ተግባራዊ የተደረገውን የኢቫንጄል የተከላ ደረጃዎች እንመለከታለን። ይህ የቀረበው እንደ ምሳሌ ሲሆን ዐውዳዊ ስልትን ገላጭ ነው። ከዚህ በታች ያለው ሠንጠረዥ ራሳችሁ ዐውድ ውስጥ በሚያመች መልኩ አስተካክላችሁ ልትተገብሩት የምትችሉት ነው። የእናንተ ተግባር የኢቫንጄል ደረጃዎችንና መርሖችን በመውሰድ የራሳችሁን ልዩ ስልት ማበጀት ነው። በተጨማሪም፣ የኢቫንጄል ሰነድ ሚና እናስተዋውቃችኋለን፣ እናብራራላችኋለንም። በተግባራዊ አገላለጽ ይህ ሰነድ የማሠልጠኛ መምሪያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። ሰነዱ የእናንተን ስልታዊ ዕቅድ ጠቅለል አድርገ በማቅረብ ቡድናችሁን ይመራል። የኢቫንጀል የመስክ አሠልጣኛችሁ በሥልጠናው ወቅት ዕድገታችሁን በመገምገም፣ ድላችሁን በማክበር፣ ፈታኝ የሆኑባችሁን ነገሮች በማማከር፣ እንዲሁም በሂደቱ ውስጥ አስፈላጊ ማስተካከያዎችን እንድታደርጉ በማማከር ይህን ሰነድ እንዴት እንደምትጠቀሙበት ይመራችኋል። በቀላል አገላለጽ ሰነዱ የእናንተ ስልታዊ ዕቅድ ነው። በመሆኑም ቡድናችሁ ሰነዱ ግቦቻቸውንና ስልቶቻቸውን በግልጽ የሚያስይ እንዲሆን በጸሎት ማሳሰብ አለባቸው።.
Made with FlippingBook - Share PDF online