Church PLANT Manual, Amharic Edition
110 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ
ፊልጵስዩስ 4፥2-3፦ በጌታ አንድ ሐሳብ እንዲኖራቸው ኤዎድያንን እለምናለሁ፤ ሲንጤኪንንም እለምናለሁ። አዎን፤ አንተ ታማኝ ባልደረባዬ ሆይ፤ ወንጌልን በማሠራጨት ረገድ ከእኔና ከቀሌምንጦስ ጋራ እንዲሁም ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት ከሌሎች የሥራ ጓደኞቼ ጋራ የተጋደሉትን እነዚህን ሴቶች እንድትረዳቸው እለምንሃለሁ። 1. ይጋጫሉ፦ ጳውሎስና በርናባስ - ሐዋርያት ሥራ 15፥36-40 2. ይሸነፋሉ፦ ዮሐንስ ማርቆስ - ሐዋርያት ሥራ 13፥13 3. ጥለው ይሄዳሉ፦ 2ጢሞቴዎስ 4፥10 • አገልግሎታችሁን ሐንካራና ውጤታማ በሆኑ የቡድን አባላት ዙራየ አጠናክሩ። ሮሜ 12፥4-6፦ እያንዳንዳችን በአንዱ አካላችን ብዙ ብልቶች እንዳሉን፣ እነዚህም ብልቶች አንድ ዐይነት ተግባር እንደሌላቸው ሁሉ፣ እንዲሁም እኛ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን። እያንዳንዳችንም የሌላው ብልት ነን። እንደ ተሰጠን ጸጋ የተለያዩ ስጦታዎች አሉን፤ ለአንዱ የተሰጠው ስጦታ ትንቢት መናገር ከሆነ፣ እንደ እምነቱ መጠን ይናገር። 1. ለጠቅላላው የቡድን አባሎቻችሁ በየዕለቱ የምትጸልዩበት ጊዜ ይኑራችሁ - ኤርምያስ 33፥3 2. ምርጠ የሆኑ ሠራተኞች ወደ ሥራችሁ እንዲቀላቀሉ በትጋት ሥሩ - 2ጢሞቴዎስ 2፥2 3. ታማኝ የሆኑ አባላትን በአገልግሎት ላይ ሹሟቸው። የእናንተ ጥያቄ፦ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ምልመላ፣ ማስታጠቅ ተግባራችን የቤተ ክርስቲያን ተከላ ስልታችንንየሚደግፍ ነው?
Made with FlippingBook - Share PDF online