Church PLANT Manual, Amharic Edition

ክፍል 4፥ ሁሉንም ነገር በጋራ ማድረግ (ማቀናጀት) • 109

ጥያቄያችሁ፥ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድናችን ከፊታችን ለሚጠብቀን ለውጥ ዝግጁ ነውን?

III.የድጋፍ አስፈላጊነት፥ ለመላመድ የተሰጡ አባላትን መመልመል እና ማስተባበር አለብን።

ተሰጥዎ ጨዋታዎችን ያሸንፋል ነገር ግን የቡድን ሥራ እና ብስለት ድልን ያጎናጽፋል።

-ማይክል ጆርዳን

ብዙውን ጊዜ በአገልግሎት ውስጥ የሚገጥሙ ተግዳሮቶች ውስብስብ እና ርስ በርሱ የተደራረቡ ሊኾኑ ይችላሉ። ስለዚህ፥ ብዙ ጊዜ ሌሎች የቡድን አባላት ግባችንን ማሳካት እንድንችል መፍትሒ እንዲያዋጡ ማድረግ ይኖርብናል። • የአገልግሎት ፈተናዎች ለየትኛውም ሰው ውስብስብ ናቸው። ማርቆስ 3፥14 (ዐ.መ.ት.) - ከርሱ ጋራ እንዲሆኑ፣ ለስብከትም እንዲልካቸው ዐሥራ ሁለቱን ሾማቸው፤ ሐዋርያትም ብሎ ጠራቸው 1. የቤተ ክርስቲያናችሁ ችግር ካላችሁ ግለሰባዊ ብርታትና ተመክሮ በፍጥነት ይበልጣል። 2. ስኬታችሁን ከፍ ለማድረግ የቡድን አባሎቻችሁን ስጦታዎች በሚገባ ተጠቀሙ። 3. የቤተ ክርስቲያን አመራር ዕድገት ስጦታው ያላቸውን ሰዎች እንዲሁም ተልእኮውን ማስቀጠል የሚችሉ ሰዎችን መለየትና ማስተባበር ይጠይቃል። • ስጦታው ያላቸው ቡድኖች እንኳ ችግርና መከፋፈል ይገጥማቸዋል።

Made with FlippingBook - Share PDF online