Church PLANT Manual, Amharic Edition

108 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ

• ድራማውን በጉጉት በመጠበቅ ተቀበሉት 1. በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ እጅ አትስጡ፤ ዐዲስ ሐሳብ አፍልቁ! ኤፌሶን 3፥20-21 2. ፈተናን እንደ መልካም አጋጣሚ ውሰዱት፤ ምንም ነገር ለጌታ ከባድ አይደለም በማለት እንኳን ደኅና መጣህ ብላችሁ ተቀበሉት። ኤርምያስ 32፥17። 3. ፈተና ሲገጥማችሁ አትደነቁ፤ ሌሎች ዐብረዋችሁ የሚሠሩ ሁሉ ተመሳሳይ ችግሮችና ፈተናዎች እንደሚገጥሟቸው አስታውሱ፤ 1ጴጥሮስ 5፥9 • ማቀድ በጣም ጠቃሚ ነው ነገር ግን ዕቅዶች ሁልጊዜም መሻሻል ያስፈልጋቸዋል። 1. ዕቅድ ዐዲስ ስሜትን ይፈጥራል ይሁን እንጂ ብዙውን ጊዜ ዕቅዶች ያረጃሉ። 2. ዕቅድ ማቀድ የቀድሞው ውጥኖች ምንም ያህል ጠቃሚ ቢሆኑ ወቅታዊውን ሁኔታ እንንድንቀበል (ይህም ማለት፥ እንደገና እንድንመለከት፣ እንደገና እንድናስብ) ያደርገናል። 3. ዕቅድ ማቀድ ለውይይት በሮችን ይከፍታል ነገር ግን ያለፈ ዕቅድ ላይ የሙጥኝ ማለት ወደ መጥፎ አቅጣጫ ሊመራ አንድ ቦታ ደርቀን እንድንቆም ሊያደርገን ይችላል። • ተለማጭነት (እንደየሁኔታው መለዋወጥ) ስኬታማ አፈጻጸም ያጎናጽፋል። 1. በመንፈስ መመላስ፥ የምታደርጓጨው ነገሮች በሙሉ በመንፈስ ቅሱስ ቃል እና ምሪት እንዲሆኑ ልባችሁን ክፍት አድርጉ፤ ገላትያ 5፥16 2. መንፈስን አታጠፉ፥ በቃሉ ውስጥ ያለውን የመንፈስ ቅዱስን ምሪትና መመሪያ አትግፉ፤ 1 ተሰሎንቄ 5፥19። 3. በመንፈስ ቅዱስ ተመሩ፥ መንፈስ ቅዱስ በነገራችሁ ነገር ላይ ወዲያውኑ እና ሙሉ በሙሉ ርምጃ ውሰዱ፤ (ሮሜ 8፥14)

Made with FlippingBook - Share PDF online