Church PLANT Manual, Amharic Edition

ክፍል 4፥ ሁሉንም ነገር በጋራ ማድረግ (ማቀናጀት) • 107

10. ተማሪዎቻችሁ፣ አማካሪዎቻችሁ፣ በጎ ፈቃደኞች ሊያቋርጡ ይችላሉ። 11. ግራ መጋባት ተጠናውቷችሁ እናንተም ልታቋርጡ ትችላላችሁ።

የሰው ዕድገት ወዲያው የሚሆን ወይም የማይቀር አይደለም። . . . ወደ ፍትሕ ግብ የሚደረግ እያንዳንዱ ርምጃ መሥዋዕት መክፈልን፣ መታገልንማ በመከራ ውስጠ ማለፍን የግድ ይላል፤ ለዚህም ራሳቸውን የሰጡና የማያቋርጥ ጥረት የሚያደርጉ ሰዎችን ይፈልጋል። -ማርቲን ሉተር ኪንግ

• ከሁኔታዎች ጋራ መላመድ ተልእኳችሁን ለመፈጸም በከፍተኛ ስሜት መታገል ነው። መላመድ ሰማያዊ የጦር ዕቃዎችን የግድ ይላል። 1. ተጋላጭ ናችሁ፦ የጦር ዕቃችሁን ታጠቁ (ኤፌሶን 6፥13) 2. ጠላታችሁ ቈርጦ የተነሣ ነው ስለዚህ ሐሳቢን አትሳቱት (2ቆሮንቶስ 2፥11) 3. ጥረታችሁ ይፈለጋል፤ መላመድ ወይም መሸነፍ (ገላትያ 5፥1) ጥያቄያችሁ፦ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድናችሁ ከፊታችሁ የሚገጥሟችሁን ተግዳሮቶች እንዴት ለይቶ ማወቅና ተገቢውን ምላሽ መስጠት ይችላል። II. የለውጥ ርግጥነት፥ በአገልግሎት መድረካችሁ ውስጥ ቋሚ ሆኖ የሚቀር ነገር የለም። የቱንም ያህል ብንጸልይና ብንዘጋጅ ከፊታችን የሚገጥሙንን ለውጦች፣ ተግዳሮቶችና ፈተናዎች ሁሉንም ማወቅ አንችልም። ስለዚህ እያንዳንዱን ርምጃችንን በድፍረት መራመድ ወደ ፊት ለሚጠብቀን ነገር ዝግጁ መሆን አለብን።

Made with FlippingBook - Share PDF online