Church PLANT Manual, Amharic Edition
106 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ
1. ዓለም፥ ከተልእኳችሁና ጥሪያችሁ የሚያዘናጋ ውጫዊ ጠላት ነው፤ 1 ዮሐንስ 2፥15-17። 2. ሥጋ፥ ዐሳባችሁንና መሰጠታችሁን የሚያበላሽ በውስጣችሁ ያለ ከሓዲ ነው፤ ገላትያ 5፥16-24። 3. ዲያብሎስ፥ ለክርስቶስ ልታደርጉ የምትሹትን ሁሉ አሳንሶ የሚያሳይ፣ የሚፈትን፣ የሚከስስ የዚህ ዓለም አምላክ ነው፤ ኤፌሶን 6።10-12 • የምትጋፈጧቸው ተግዳሮቶች እየበዙ ይሄዳሉ፣ ቋሚ ይሆናሉ፣ አእምሮን የሚያውኩና አድካሚ ይሆናሉ (ዮሐንስ 15፥18-21፤ ያዕቆብ 1፥2-3፤ 1 ጴጥሮስ 1፥6-7፣ 5፥8-9)። • ውጤታማ በሆነ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ተግባር ውስጥ የሚገጥሙ የተለመዱ ጉዳዮች፦ 1. ከዕቅዳችሁ በታችና ከሚያስፈልገው የሰው ኀይል በታች ወደ ተግባር እንድትገቡ ልትገደዱ ትችላላችሁ። 2. ተወካይ የሌለው ሥራ በጫንቃችሁ ላይ ሊያርፍ ይችላል። 3. የታመኑ የቡድን አባላት ሊሸሹ ወይም ሊያቋርጡ ይችላሉ። 4. ዕቅዳችሁ ፈጽሞ ካሰባችሁት በተቃራኒው ሊጓዝ ይችላል። 5. አስፈላጊ ግብዓቶች ሊጐድሏችሁ ይችላሉ። 6. የነበሯችሁ ጠቃሚ መሣሪያዎች የት እንደገቡ ልታጧቸው ትችላላችሁ። 7. የገንዘብ፣ የጊዜ፣ የጉልበት ዕጥረት ሊገጥማችሁ ይችላል። 8. እናንተ ወይም የታመኑ የቡድናችሁ ሠራተኞች በጣም በምታስፈልጉበት ሰዓት ልትታመሙ ትችላላችሁ። 9. በገንዘብ፣ በመንፈሳዊ ነገሮችና በሌሎች የግል ጉዳዮች አስፈላጊ ድጋፍ ልታጡ ትችላላችሁ።
Made with FlippingBook - Share PDF online