Church PLANT Manual, Amharic Edition
ክፍል 4፥ ሁሉንም ነገር በጋራ ማድረግ (ማቀናጀት) • 105
ትምህርት 12 ለማሸነፍ መላመድ 1
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ለቤተ ክርስቲያን ተከላ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ፣ ዐሳብ፣ ጸሎት እና ዕቅድ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ተመልክተናል። ማንኛውም ዕቅድ ዐቅዶ የሚያውቅ ሰው እንደሚገነዘበው ዕቅዶች ዕቅድ ብቻ ሆነው እስካልቀሩ ድረስ ታላቅ ናቸው። ብዙ ያልተጠበቁ ፈተናዎች፣ መሰናክሎችና ተግዳሮቶች እንዲሁም ዕቅዳችሁን ማስተካከል እንዳለባችሁ የሚጠቁሙ መልካም አጋጣሚዎችም ሊገጥሟችሁ እንደሚችሉ እንገነዘባለን። ለሁሉም የቤተ ክርስቲያን ተካዮችና ቡድኖቻቸው ቍልፉ ባሕርይ እንደሁኔታው ተለዋዋጭ መሆን ወይም ተለማጭነት ነው። በርግጠኛነት ወደፊት በተጓዛችሁ መጠን ዕቅዶቻችሁን መላመድ መቻል አለባችሁ። ጌታ የሰጣችሁን ይህን ርእይ ተግባራዊ ለማድረግ በምትጓዙበት ጊዜ ዕቅዳችሁን በመላመድ መንፈስ ልትተገብሩ ያሻል። ቀጥሎ የቀረበው ቢጋር ቡድናችሁ በቀጣይነት ሊገጥሙት የሚችሉትን ነገሮች አስቀድሞ ለመጠቆም የተዘጋጀ ነው። ቡድናችሁ ለሚገጥሙት ችግሮች ምላሽ የሚሰጥበትና ፈታኝ ሁኔታዎች በመላመድ የሚያልፍበት መንገድ ስኬታማነቱን ይወስናል። ለማሸነፍ መላመድን በተመለከተ ያሉ እውነታዎችን እንመልከት፦ I. የችግር አይቀሬነት፥ ነገሮች ይበላሻሉ ይህ ዓለም በኀጢአት የወደቀ ዓለም በመሆኑ በሰይጣን ተጽዕኖና ጥቃት ውስጥ ነው። • ሁሉም የቤተ ክርስቲያን ተከላ ተግባራችሁ የጠላትን መስመር አልፋችሁ የምታደርጉት ነው።
1 Adapted from a seminar by Rev. Dr. Don L. Davis in Ripe for Harvest , pp. 443-449.
Made with FlippingBook - Share PDF online