Church PLANT Manual, Amharic Edition
104 • የቤተ ክርስቲያን ተከላ መምሪያ
ሁሉን በጋራ ማቀናጀት 1
I. መመሪያ ሰነድ ምንድን ነው? • በጽሑፍ የሰፈረ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድን ዐላማ ነው። • አመራር ተጠያቂ የሚሆንበትን መንገድ ይሰጣል • በቡድኑ ውስጥ ለውጦች ካሉ ቡድኑ በግልጽ መቀጠል የሚችልበትን ግልጽነት ይሳጠል። • ሥራውን በተገደበ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ያስችላል። II. ለምን በጣም አስፈላጊ ሆነ? • የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድኖች ያለ ምንም ውጤት ብዙ ጊዜ ይቆያሉ ወይም ተስፋ ይቆርጣሉ በዚህም ፈጥናው ለማቆም ይፈልጋሉ። እነዚህ የመምሪያ ሰነዶች ተስፋ ቈርጦ ማቆምን በመቀነስ የጊዜ ውቅርን ይሰጣሉ። • የቤተ ክርስቲያን ተከላ ቡድኖች በየጊዜው ተጠያቂ መሆን ያለባቸው ቢሆንም ጥቃቅን አስተዳደር ግን አያስፈልጋቸውም። ሰነዶች፥ ቡድኑ በተሰጠው መመሪያ መሠረት በነጻነት እንዲንቀሳቀስና እንዲሠራ ስለሚያስችሉት ውጥረትን ይቀንሳሉ። የመምሪያ ሰነዶቹ በጽሑፍ የሰፈሩ ዐላማዎችንና ግቦችን ስለሚሰጡ ለቀረበው ዕቅድ ተጠያቂ መሆን ያስችላሉ። • መመሪያ ሰነዶች ቡድኑ በቀጣዩም ዐመት ጥረቱን ሳያባክን በሥራው ላይ እንዲቆይ ያስችላሉ። • በአንድ አካባቢ የሚተከሉ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ካሉ ይህ የመምሪያ ሰነድ በትኩረት የመንሠራባቸውን አካባቢዎች ስለወስን ከንቱ ልፋትና አላስፈላጊ ውጥረትን ያስወግዳል።
1
Ripe for Harvest , pp. 464-466.
Made with FlippingBook - Share PDF online