Church PLANT Manual, Amharic Edition

ድኅረ ቃል ሬቨረንድ ቴድ ስሚዝ

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ሥራችንን ማከናወን የሚያስችሉን በርካታ ነገሮችን ተመልክተናል። እነዚህ ግብዓቶች እና መረጃዎች በወርልድ ኢምፓክት ኢቫንጄል ቤተ ክርስቲያን ተከላ መጽሐፍ መደርደሪያ ላይ ታገኟቸዋላችሁ (worldimpact.org/cpbookshelf) እንዲሁም በአማዞን ድረ ገጽ ላይ ማግኘት ትችላላችሁ። ከዚህ ቀጥሎ የቀረበው እናንተና ቡድናችሁ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ተግባራችሁን ስትከውኑና የኢቫንጄል የከተማ ቤተ ክርስቲያን ተከላ ትምህርት ቤት ተግባራዊ በምታደርጉ ጊዜ ሊጠቅሟችሁ የሚችሉ እንደ መግቢያ የሚሆኑ ቍልፍ ምንባባት ናቸው።

መከሩን ማጨድ፥ በከተማ ውስጥ ጤናማ ቤተ ክርስቲያን የመትከል መምሪያ

ይህ መምሪያ መጽሐፍ የኢቫንጄል ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ጽሑፍ ሲሆን በአሜሪካ ከተሞች ውስት የሚንጸባረቁ ባህሎችን፣ ከባቢዎችን፣ ማኅበረ ሰቦችንና ኹኔታዎች ውስጥ ቤተ ክርስቲያን የመትከል ሂደትን የያዘ ነው። በከተማ አካባቢ ቤተ ክርስቲያን ለሚተክሉ ቡድኖች በእንቅስቃሴያቸው ወቅት እንዳይወድቁ ወይም ተይዘው እንዳይቀሩ ይህ የተከላ መምሪያ ተግባራዊ ጥበብና መንፈሳዊ ጠቀሜታ ያለው መመሪያን ይሰጣል።

123

Made with FlippingBook - Share PDF online